ናትናኤል ኣስመላሽ

ከአስመራ ተነስተው የኢትዮጲያን ህዝብ ነጻ ለማውጣት እንታገላለን የሚሉት ማን ቤት ውስጥ ሆኖው ትግሉን እያካሄዱት እንደሆነ አሁም ኣልገባቸውም። ትግርኛ ተናጋሪው የኤርትራን ህዝብ እና የትግራይን ህዝብ አጋሜ እና የአስመራ ህዝብ በማለት ለይተውታል። አለማወቅ ሃጥያት አይደለም ግን ድ ድብና ነው። በተቻለኝ መጠን ማን አጋሜ እንደሆነ ለማስረዳት እሞክራለሁኝ። ሌላው መታወቅ ያለበት ግን እኔው ራሴ አጋሜ ነኝ፣የኤርትራው ፕረዚዳት አቶ ኢሳያስ አፎርቂም አጋሜ ናቸው።

አጋሜ ማለት የቦታ ስም ነው፣ ይህ ቦታ አዲግራት ውስ ጥ ይገኛል። አንድን ሰው አጋሜ ካልከው፣ ለፍቶ አዳሪ፣ ከትን ሽ ስራ ወደ ትልቅ ስራ የሚሸጋገር፣ ዛሬ እንቁላል ሸጦ ነገ ትልቅ ዘመናው የ ደሮ እርባታ የሚከፍት፣ስራ የማይንቅ፣ የገንዘብ አያያዝ ችሎታው ከፍ ያለ ማለት ነው። ለምሳሌ አዲስ አበባ ውስጥ አንድን ሰው ጉራጌ ካልከው ለፍቶ አዳሪ፣ስራ የማይንቅ፣ዛሬ ዝቅ ብሎ ነገ ከፍ ብሎ መታየት የሚፈልግ፣ ዛሬ ሱቅ በደረቴ ሰርቶ ነገ ሱፐር ማርኬት የሚከፍት ማለት ነው። የጉራጌ ማህበረሰብ ተወላጅ ጉራጌ ብትለው ይኮራል እንጂ አያፍርም፣ አንድ የትግራይ ተወላጅም አጋሜ ካልከው ይኮራል እንጂ አያፍርም፣፣ ለምሳሌ እኔ አጋሜ የሚለኝ ሰው ደስ ይለኛል አጋሜ ስ ለሆንኩ።

ከአስመራ ተነስተው የኢትዮጲያን ህዝብ ነጻ ለማውጣት እንታገላለን ፊሽካ ነፍተናል የሚሉ አስመራ ውስጥ ያሉ የኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣናት አጋሜዎች መሆናቸውን እያወቁ አጋሜዎች አይደሉም ይሉናል። ኤርትራ ውስጥ ያሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት 95% አጋሜዎች ናቸው። ለምሳሌ የኤርትራው ፕረዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፎርቂ፣ የኤርትራው ፕረዚዳንት ከፍተኛ አማካሪ አቶ የማነ ገብረ አብ፣ የ ኤርትራ የቁጠባ ሃላፊ አቶ ሓጎስ ክሻ፣ የኤርትራ መንግስት ቃል አቀባይ የማነ ገብረመስቀል በሙሉ አጋሜዎች ናቸው። ግምቦት ሰባትን የሚያሽከረክሩም እነዚህ ከፍተኛ የኤርትራ ባለስልጣናት ናቸው። በኤርትራ የሚገኘው የጸጥታ ቢሮ ሴኩሪትይ ኦፊስ በትግርኛ ሃገራዊ ድሕነት ይባላል፣ በዚህ ቢሮ የሚቀጠሩ በሙሉ አጋሜዎች ናቸው፣ አጋሜ ካልሆንክ የመቀጠር እድልህ የመነመነ ነው። በባለስልጣናት ደረጃ ወደታች በወረድክ ቁጥር ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎች ያሉት አጋሜዎች ናቸው።

የኤርትራው ፕረዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፎርቂ አጋሜ ናቸው፣ አመጣጣቸው ከተምቤን እና አድዋ ነው። አያታቸው ከትግራይ ወደ አስመራ ሲሄዱ ምንም ነገር ስላልነበራቸው አስመራ ውስጥ ጠላ በመሸጥ ነበር የሚተዳደሩት። እንግዲህ አጋሜ ማለት ስራ የማይንቅ የነገን ትልቅ ምስል የሚያይ ነው ብለናል። የኤርትራው ፕረዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፎርቂ ሴር አያት ወሮ መድህን በራድ ይባላሉ፣ በራድ ማለት ለሻይ ማፍያ የምንጠቀምበት ማለት ነው፣ በራድ የተባሉበት ዋናው ምክን ያት ጠላ ሻጭ ስለነበሩ እና ዋንጫ ላይ ጠላን ለመቅዳት የሚጠቀሙበት እቃ የሻይ ማፍያው በራድ ስለነበር ነው። የኤርትራው ፕረዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፎርቂ እድገታቸው በብዛት ከ አያታቸው ጋር ነበር፣ አያታቸው ከትግራይ መጥተው አስመራ ውስ ጥ ጠላ ሻጭ ሆነው ነው የኤርትራው ፕረዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፎርቂን አባት አቶ አፎርቂንያሳደጉት፣ከዚህም አልፎ ኢሳያስ አፎርቂንም ጠላ እየሸጡ ነው ያሳደጉት። እናማ እነእንትና አጋሜ ማን መሆኑን ሳታቁ አት ጻፉ፣ የናንተው ጌታ የኤርትራው ፕረዚዳንትም አጋሜ ነው።

አቶ የማነ ገብርአብ የኤርትራው ፕረዚዳንት ከፍተኛ አማካሪ ናቸው። አቶ የማነ ማለት ባለፈው ሳምንት ኢሳት ውስጥ የቀረቡ ናቸው፣ ቢቀርቡስ ይገርማል እንዴ ኢሳትም እኮ የአጋሜዎች ነው ለዛው የአጎቴ የማነ ገብርአብ። የማነ ገብርአብ እ ናቱ ከ አክሱም ተነስተው አስመራ ገብተው ወፍጮ ቤት ይሰሩ እንደነበር ይነገራል። እኝህ እናት ናቸው እንግዲህ ዝቅ ብለው ስራ ሰርተው እና ልጃቸውን ለዚ ህ ያደረሱ። አቶ የማነ ገብረ አብ ሻእብያ በረሃ በነበረበት ወቅት ውጭ አገር ውስጥ የፖለቲካ ሃላፊ ሆነው ያገለግሉ ነበር፣ ሻእብያ ኣስመራ ከመቆጣጠሩ በፊት ወደ በረሃም ወርደው ነበር። አሁን የ አቶ አኢሳያስ አፎርቂ ከፍተኛ አማካሪ ናቸው።

አቶ ሓጎስ ክሻ የአራት አመት ህጻን ልጅ እያሉ ከናታቸው ጋር ከትግራይ ተምቤን አውራጃ ወደ አስመራ ተሰደው፣አስመራ ውስጥ አድገው ተምረው ነው አሁን ለዚህ ስልጣን የደረሱ። የ አቶ ሓጎስ እናትም እንደማንኛው ከትግራይ የመጣ ሰው ስራን ሳይንቁ ዝቅ ብለው ሰርተው ለዚህ በቁ። በእውነቱ የ አቶ ሓጎስ ክሻ እናት ስራ ምን እንደነበር አላቅም፣የምታቁ ካላቹ ንገሩን፣ ግን ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አያት የተለየ ስራ ይሰራሉ ብየ አልገምትም ምክንያቱም ሁሉም ነገር ከዜሮ ነው የሚጀመረው።አቶ ሓጎስ ኪሻ የ ኤርትራ የቁጠባ ሃላፊ ናቸው፣ ሻእብያ በረሃ በነበረበት ጊዜ በ አውሮፓ በተለይም በጣልያን ሆነው የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ያካሂዱ ነበር። ለትግሉ የሚፈለግ ማንኛው ገንዘብ ሰብስበው መድሃኒት እና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች ገዝተው በረሃ ድረስ ይልኩ ነበር። አሁን በስማቸው ብዙ ገንዘብ እንዳለ ይታወቃል። ከድል ቦሃላም ኤርትራ ውስጥ የሚደረገው ማንኛው ንግድ በብባልይ በመምራት እና በመንግስት ሽፋን ንግድ በማካሄድ ሌላው ነጋዴ ከጨዋታ ውጭ አድርገዋል። አሁን እነ እንትና የሚሰበስቡትን እቁብ በቀጥታ አቶ ሓጎስ ክሻ እጅ ውስጥ ይገባል። እነ እንትና ጥይት እንዳይተኩሱ ብቻ ሳይሆን ገንዘብም እንደፈለጉ እንዳያንቀሳቅሱ ታግደዋል፣ ከ አቶ ሓጎስ ክሻ ትእዛዝ ውጭ ግም ሰባቶች ዱዲ ማንቀሳቀስ አይችሉም።

አቶ የማነ ገብረመስቀል የኤርትራው ፕረዚዳንት የቢሮ ሃላፊ እና ቃል አቀባይም ናቸው። እሳቸው እንደማንኛውም የኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣን አጋሜ ናቸው። ወላጆቻቸው ከትግራይ አስመራ ሄደው ዝቅ ብለው ስራ ሰርተው ነው ለዚህ የበቁት። እነዚህ አራት የኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸው አስመራ ቁጭ ብለው ግም ሰባትን የሚያሽከረክሩ። ደስ የሚለው ደግሞ ኣራቱም አጋሜዎች ናቸው። ወላጆቻቸው አስመራ ሲመጡ ዝቅ ብለው ሰርተው አሁን ከማንም በላይ ከፍ ብለው የሚታዩት። አጋሜ ማለት ዛሬ ላይ ሆኖ የነገን ትልቅ ህልም የሚያይ ማለት ነው። የስብሃት ነጋ እህትም እዚህ ቢሮ ውስጥ ይሰራሉ ለማስታወስ ያህል ነው።እናንተ ጥዋት እና ማታ አራት ኪሎ ብቻ ስለሚታያቹ ትረሳላቹ ብየ ነው።

በመጨረሻ ግም ሰባቶች አጋሜን ዲፋይን ሲያደርጉ እንዲህ ይላሉ።
“ምሳሌ እንጥቀስ አስመራ ዉስጥ አንድን ተራ ስራ ማለትም ቆሻሻ ለመጥረግ የተዘጋን የቆሻሻ ቱቦ ለመጎርጎር ማለት የስራ አስፀያፊ ነገር ባይኖርም ቅሉ አይ አልነካዉም የሚሉት ስራ ሲኖር የአስመራ ሰዎች ምን ይላሉ ለምን በአጋሜ አታሰራዉም ይላሉ ለዚህም ነዉ ለእንዲህ አይነት የወረደ ስራ የጉልበት ሰራተኛ ሲጠሩ አጋሜ አጋሜ እያሉ የሚጠሩት በተጨማሪም አንድ ሰዉ እየለመነ ካገኙት አጋሜ ነዉ ብለዉ ነዉ የሚደመድሙት”(ምንጭ ሰሎሞን ከግምቦት ሰባት).

እንግዲህ ከላይ እንዳየነው የፕረዚዳንቱ አያት ጠላ ሻጭ ነበሩ፣ የኤርትራው ፕረዚዳንት አማካሪ እናት ወፍጮ ቤት ተቀጥረው ይሰሩ ነበር፣ ባጠቃላይ የግም ሰባቶች አለቆች ስራ ግም ሰባቶች ያሉት ነው። አሁን ግን አጋሜዎች ይህንን ሁሉ አልፈው ኤርትራን ማስተዳደር ብቻ ሳይሆን ኤርትራ በረሃ ተነስተው አራት ኪሎ ለመግባት የሚያስቡትንም ጭምር እያስተዳደሩ ይገኛሉ። እናማ ግም ሰባቶች አለቆቻቹን በደምብ እወቁዋቸው!!! አለቆቻቹ አጋሜዎች ናቸው።

ፕሬዚዳንት ኢሰያስ አፎርቂ መጠጥ በጠጡ ጊዜ ሁሌ አጠገባቸው ላሉ ኤርትራውያን ነን ባዮች “ተደብቃቹ አጋሜ እንደምትሉኝ አውቃለሁኝ” በማለት በተደጋጋሚ ተናግረዋል፣ ይህ አባባላቸው ዓንደብርሃን በተባለ ጸሃፊ ተጽፎ ለታሪክ መጽሃፍ ላይ ተቀምጠዋል። ግም ሰባት እንግዲህ አስመራ ውስጥ ቁጭ ብለው የሚያሽከረክሩህ ከተምቤን፣ከአድዋ፣ከአክሱም የመጡ አጋሜዎች ናቸው።አንተ እንዳልከው አስመራ ውስጥ የጉልበት ስራ ሲሰሩ የነበሩ፣ ጠላ ሲሸጡ የነበሩ፣ሽንትቤት ሲጠርጉ የነበሩ ልክ አንተ አሜሪካ እና ካናዳ መጥተህ ሽንትቤት እንደምትጠርገው ማለት ነው ሲሰሩ የነበሩ ማለት ነው።
ስለዚህ አንተ በሻእብያ ሳምባ እስከተነፈስክ ድረስ፣ ፊሽካውን ሻእብያ እስከነፋው ድረስ ካለህበት አንድም እርምጃ ንቅንቅ እንደማትል እወቅ!!! ከድሃው ዳያስፖራ እየሰበሰብክ ለሻእብያ የምት ሰጠው ዶላር አገር ቤት ላሉ የፖለቲካ እስረኞች ብት ሰጥ ይሻላል። አገር ቤት ውስጥ ህገ መንግስቱን አክብረው ስለታገሉ ብቻ ከስራ ተባረው ምንም ገቢ የሌላቸው እንደ ከማል ገልቹ ወርቅ የሆኑ ኢትዮጲያውያን አሉ እና እነሱን እርዳቸው። ከዚህ በተረፈ ግን በሻእብያ ትንፋሽ የተነፋው ፊሽካ እንካንስ የኢትዮጲያ ድምበር ሊያልፍ የአስመራን ድምበርም ኣያልፍም!!!ፊሽካው ግን የት ደረሰ ወይስ ፊሽካው ከሻእብያ ከንፈር እስክትቀበሉ ድረስ እንጠብቅ።

Natnael Asmelash's photo.
Natnael Asmelash's photo.
Natnael Asmelash's photo.
Natnael Asmelash's photo.

Leave a Reply