ሻአቢያ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሆኖ አያውቅም


une 23, 2016

ኤርሚያስ ቶኩማ
ግንቦት 7 ከኤርትራ ሊለቅ ይችላል ተብሎ የተፃፈውን የኖአሚን በጋሻውን ፅሁፍ አነበብኩት። ይህንን ፅሁፍ እንዳነበብኩኝ ቀጥታ የአበበ በለውን ድህረ ገጽ ከፍቼ አበበ በለው ከአቶ ከግንቦት 7 አመራር ጋር ያደረገውን ቃለመጠይቅ ሰማሁት። አቶ ንአመን ሻአቢያን በመደገፍ ፒቲሽን እንድንፈርም ጠይቀዋል። ኤርትራ ውስጥ ማህበራዊ ፍትህ አለ የሰብአዊ መብት ጥሰት ደግሞ ኤርትራ ብቻ ሳይሆን አሜሪካም አለ ብለውናል እዚህ ጋር ረሐብ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን አሜሪካ ውስጥም አለ ያሉትን የቀድሞ የወያኔ መሪ መለስ ዜናዊን አስታወሱኝ። ህፃናት እና አዛውንትም ሳዋ ማሰልጠኛ የሚገቡት በፍላጎታቸው ነው ብለውናል። የኤርትራ መሪዎች በህዝባቸው ላይ አይፈነጭም፤ ከፈለክ ፕሮፌሰር መስፍንን ጠይቀው ብለዋል አቶ ንአመን።
አቶ ንአመን Neamin Zelekeየሻአቢያን አመራር ውብ አድርገው ስለው አቅርበውልናል። የሻአቢያ እና የወያኔ ፀረ ዴሞክራሲያዊነት ለሁሉም በግልጽ የሚታይ ሆኖ ሳለ አቶ ንአመን ለምን የሻአቢያን ውብነት ለምን መግለፅ እንደፈለጉ ሊገባኝ አልቻለም። የኢሳያስና የወያኔ ሰዎች ሰው በላነት የጥቁር ህዝብ ያፈረበት በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ላይ መፃፍ አልፈልግም እኔ ማሳየት የፈለግኩት የሻአቢያን ፀረ ኢትዮጵያዊነት ነው። በዚህም ዙሪያ ስለሻእቢያ ፀረ ኢትዮጵያዊነት ፌስቡክ ላይ የፃፍኩትን ደግሜ ላስነብባቹህ።
አንዳንድ ወዳጆቼ ሻአቢያ የኢትዮጵያ ወዳጅ እንደሆነ ለማሳየት ሲሞክሩ በተደጋጋሚ አያለው ሆኖም የሻአቢያን ተፈጥሯዊ ባህሪና ድርጊት ለተመለከተ ሰው ሻአቢያ የኢትዮጵያ ወዳጅ የሚሆንበት ምንም ምክንያት የለውም ለዚህም ማስረጃዎችን ላቅርብ
ደራሲው “ሻዕቢያ” ወይም “ህዝባዊ ግምባር” ተብሎ በሚጠራው የኤርትራ ነፃ አውጪ ድርጅት ውስጥ ከ1974 ዓ.ም ታጋይ የነበረው ግለሰብ “ትልሚ ንዘርኢ ክርዳድ” ብሎ በፃፈው መፅሀፍ ላይ ስለአማርኛ ቋንቋ የሻአቢያ አመራሮች የነበራቸውን ጥላቻ ፅፎታል በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ ሰማይ ብሎግ አዘጋጁ ጌታቸው ረዳ ወደአማርኛ ተርጉሞት በመፅሀፉ ውስጥ ደራሲው ስለአማርኛ ቋንቋ የገለፀውን እንዲህ አስቀምጦት ነበር።
“ኤርትራ ውስጥ የአማርኛ ሙዚቃ እንዳይደመጥ በሕግ ተከልክሎ ነበር። በየሙዚቃ መሸጫ መደብሮች ውስጥ የነበሩ የአማርኛ ሙዚቃ ካሴቶች፤ሲዲዎች እና ቪዲዮዎች በዘመቻ እንዲሰበሰቡ ተደረገ። አማርኛ ሙዚቃን ያዳመጠ ወይንም ያዳመጠች ከባድ ቅጣት እንደሚደርስባት ማስጠንቀቂያ ተላለፈ።” ይላል የሻአቢያ አባል የነበረው ደራሲ
ከዚህ ደራሲ ውጭ የሻአቢያን ፀረ ኢትዮጵያዊነት ያጋለጡት የጀብሃ ታጋይ በሗላ ድርጅቱን ከድተው በሰላም ወደ አገራቸው በመመለስ በኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በማጋለጥ የታሪክ ባለውለታ የሆኑት ኤርትራዊው አቶ ተስፋሚካል ጆርጆ በወቅቱ ስለሻእቢያ ፀረ ኢትዮጵያዊነት በሰፊው ገልጸውታል። ይህ መረጃ ይፋ በማድረጋቸውም በኢሳያስ ትዕዛዝ አገሬ ብለው ሰላምና መረጋጋት አለ ብለው ያለስጋት እኖራለሁ ብለው አዲስ አበባ ይኖሩ በነበሩበትት ወቅት ኢህአዴግ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ በሗላ እቤታቸው ድረስ ስልክ ተደውሎ ትፈለጋለህ ተብለው ከቤታቸው ሲወጡ በነብሰ ገዳዮች ጥይት አዲስ አበባ ውስጥ ተገድለዋል።
ስለሻእቢያ ሲወራ ሻአቢያ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ላይ በየጊዜው የሚፈፅመው በደልም መነሳት አለበት ሁላችንም ልናውቀው የሚገባው በትግራይ ወገኖቻችን ላይ በሻእቢያ የሚፈፀመው ግፍ እንደኢትዮጵያዊ ሊያመን ይገባል የትግራይ ገበሬዎችን እያፈነ ኢትዮጵያን እወዳለሁ የሚል የሻአቢያ መሪ ካለ ገደል ይግባ። በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያዊያን ላይ ምንም አይነት ጥቃት የሚፈጽም የኢትዮጵያ ጠላት ነው በኢትዮጵያ ልንደራደር አይገባም አንጋፋው ፖለቲከኛ አሰገደ ገብረሥላሴም በቅርቡ በፃፈው መፅሀፍ ላይ ስለጉዳዩ ሲገልጽ
“በሰሜኑ (ትግራይ) አገራችን የሚኖሩ ዜጎቻችን ከሚኖሩባቸው ገጠሮች ደንቅ ደፈጣ እየተደረገባቸው እየታፈሱ በሺዎቹ የሚቆጠሩ በሻዕቢያ ታፍሰው በሳሕል በረሃዎች በ15ኛው ክፍለዘመን የሰው ፍጡር “ጊላ/ባርያ” እየተባለ ግፍ ሲፈጸምበት አንደነበረው ዓይነት አያያዝ የተያዙ ዜጎቻችን አሉ።” ይላል ሻአቢያ ያፈነው የትግራይ ወገኖቻችንን ብቻ አይደለም ከአንጋፋው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ እስከ ወጣቱ ተስፋሁን አለምነህ ድረስ በሻእቢያ ደብዛቸው ጠፍቷል።
ኢሳያስ አፈወርቂ ሲፈልግ የኢትዮጵያ ታሪክ ተንታኝ መሆን ይፈልጋል በ2013 የአዲስ አመት መግለጫ ለኤርትራውያን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ‹‹ኢትዮጵያ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተፈጠረች አገር ነች›› በማለት መናገሩ ይታወሣል ይህንን መሀይም ሠው ነው የኢትዮጵያ ጠላት አይደለም የምትሉት? የኢትዮጵያ ታሪክ እንደሱ ባሉ መሀይም የኢትዮጵያ ጠላቶች የሚነገር አይደለም ስለኢትዮጵያ ማወቅ የፈለገ the martyr Dom of Man የተሰኘ በ1850ዎቹ የተፃፈ በግብጾች ካለበት እየተሰበሰበ ይቃጠል የነበረን መጽሐፍ ያንብብ መጽሐፉን ለማታገኙ በቅርቡ በፒዲኤፍ ጀባ እላችኋለሁ
በመጨረሻም ኢሣያስ አፈወርቂ የአባቱን ስም ከአፈወርቅ ወደአፈወርቂ የእናቱን ስም ከአዳነች ወደአድሀኖት የቀየረው ለአማርኛ ያለውን ጥላቻ ሲገልጽ መሆኑን እንኳን ልንረዳ ይገባል። በተረፈ እኔ ስለኢሳያስ ጸረ ኢትዮጵያዊነት እንደፃፍኩት ሁሉ ኢሣያስ አፍቃሪ ኢትዮጵያ ነው የምትሉ ሰዎች ማስረጃ ብትሰጡኝ ደስ ይለኛል።
ኢትዮጵያዊነት ይለምልም ሞት ለፀረ ኢትዮጵያ ሐይሎች በሙሉ
ermiastokuma@yahoo.com
‪#‎ኤርሚያስ_ቶኩማ‬

 

:)

Leave a Reply