June 27, 2016

(አምዶም ገብረስላሴ – ከትግራይ) በመቐለ ከነማና ፋሲል ከነማ ክለቦች መካከል በዓዲግራት ስተድየም የተካሄደው የእግር ኳስ ጨዋታ በኣንድ እኩል ውጤት የተፈፀመ ሲሆን ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ የተወሰኑ የወልዋሎ ደጋፊዎች “የፋሲል ተጨዋቾች ኣናስወጣም” ብለው ለማገት ሲሞክሩ ትግራይ ልዩ ሃይል የጥይትና ኣስለቃሽ ጋዝ ተኩስ በመክፈትና ድብደባ በማካሄድ ኣነስተኛ የነበረው ግጭት ወደ “ተመጣጣኝ ጦርነት” ተቀይረዋል።
ትግራይ ልዩ ሃይል
የግጭቱ መነሻ ባለፈው ወር በጎንደር ከተማ “የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች የወልዋሎ ተጨዋቾች ኣግተው ደብድበውብናል” የሚል ሲሆን ልዩ ሃይሉ የተወሰኑ ደጋፊዎች ተቃውሞ ማሰማት ሲጀምሩ በመተኮስ ወዳላስፈላጊ ኣቅጣጫ እንዲሸጋገር ኣድርገዋል።

የትግራይ ልዩ ሃይል የወልዋሎ ደጋፊዎች ላይ የተኩስ እሩምታና ኣስለቃሽ ጭስ የተጠቀመ ሲሆን ከሁለት ሰዓት በላይ ሰፈር ለሰፈር እየዞረ እየተኮሰና እየተደባደበ ማምሸቱ ታውቀዋል።

ዓዲ ግራት በትግራይ ልዩ ሃል የጥይት እሩምታ፣ ኣስለቃሽ ጭስና ደላ ተጠቅሞ ከተማዋ ሲበጠብጥና የጦርነት ግንባር ኣስመስሏት ማምሸቱ ኑዋሪ ህዝቡ ኣስገርሟል።

ትግራይ ልዩ ሃይል2ከሻዕብያ የተደረገው ጦርነት “ተመጣጣኝ እርምጃ ወስጃለው ለወደፊትም የምወስደው እርምጃ ተመጣጣኝ ይሆናል” ብሎ የገለፀው መንግስት በስፖርት ደጋፊዎች ያልተመጣጠነ እርምጃ መውሰዱ ትዝብት ላይ የሚጥለው ይሆናል።

በሃገራችን እየታየ ያለው የስፖርት ደጋፊዎች ግጭትና የወጣቶች ቁጣ ኢህኣዴግ የፈጠረው የኣገዛዝ ምሬት መገለጫ ነው።

ተመጣጣኝ ጦርነት ኣደርጋለው የሚል መንግስት ተመጣጣኝ የፀጥታ ኣፈታት ተግባር መከወን እንዴት ያቅተዋል?

Leave a Reply