(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
በሽታን ተከላካይ የሆኑ አረንጓዴ ተክል ምግቦች
የአረንጓዴ ተክሎች ለጤና ጠቃሚ መሆን የማያጠራጥር ሲሆን ለዛሬ በጥቂቱ ስለተክሎቹ አይነትና ጥቅሞቻቸዉ ልነግራችሁ ወደድኩኝ፡፡
✔ ብሮኮሊ
ይህ አትክልት በቫይታሚን ሲ እና በፋይበር የበለጸገ ሲሆን በዉስጡ የያዛቸዉ ንጥረ ነገሮች በሽታን የመከላከል አቅማቸዉ ከፍተኛ ነዉ፡፡ የሳንባ እና የካንሰር ህመሞችን የመከላከል አቅም አለዉ፡፡
✔ ጥቅል ጎመን
የተለያዩ አይነት የጎመን ዝርያዎች ያሉ ሲሆን ሁሉም በቫይታሚን ኤ፤ ሲ፤ካልሲየም እና ሌሎች ንጥረ ነገሮች የበለጸጉ ናቸዉ፡፡በአዉስትራሊያ የተሰራ ጥናት እንደሚያመለክተዉ እነዚህን አረንዴ ተክሎች መመገብ ለካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል፡፡
✔ የጀርመን ሰላጣ
የጀርመን ሰላጣ ሠዉነታችንን ካንሰር እንዲዋጋ አቅም የሚሠጥ ሲሆን ከዛም ባለፈ ለብጉር፤የፀጉር መነቀል እና ሌሎችንም ይከላከላል፡፡
✔ ቆስጣ
ቆስጣን መመገብ የጉበት፣ የአንጀት፣ የማህፀን እና የፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ጥናቶች የሚያሳዩ ሲሆን ከነዚህም በተጨማሪ ለጡንቻ መዳበር ጠቃሚነት አለዉ፡፡
✔ የሾርባ ቅጠል
ምግብን ለማጣፈጥ የምንጠቀምበት የሾርባ ቅጠል በዉስጡ ፎሊክ አሲድ፣ቫይታሚን ኤ፣ቢ፣ኬ እና ሌሎች ንጥረ ነገሮችን የያዘ ሲሆን የአጥንት መሳሳትንና የልብ ህመም ተጋላጭነትን እንደሚቀንስም ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
✔ ሠላጣ
ሠላጣን መመገብ ለደም ግፊት ህመምተኞችና ከፍተኛ የሠዉነት ክብደት ላላቸዉ ሠዎች የሚመከር ሲሆን የደም ዉስጥ ስር መጠንንም ይቀንሳል፡፡ ሠላጣ በዉስጡ የያዘዉ ካልሲየምና ፎስፈረስ ለአጥንት ጤናማነት ጠቃሚ ሲሆን ሴሊኒየም የሚባለዉ ንጥረ ነገር ደግሞ የሠዉነታችን ቆዳ ቶሎ እንዳረጅና የአንጀት ካንሠርን የመከላከል አቅም እንዲኖረዉ ያደርጋል፡፡
✔ ጥቁር ጎመን
ጥቁር ጎመን በዉስጡ ቫይታሚን ቢ1፣ቢ2፣ቢ3፣ቢ6 ፣ሲ እና ሌሎች እንደ ፖታሲየም ፣ካልሲየም ፣ፎስፈረስ እና አዮዲንንም ይይዛል፡፡የሠዉነት የበሽታ የመከላከል አቅምን የሚያጠነክርና በሽታንም የሚከላከል የተክል አይነት ነዉ፡፡
ለወዳጅዎ ያካፍሉ
ጤና ይስጥልኝ