ዳዊት ከበደ ወየሳ

 

(EMF) የደምቢዶሎ አየር ማረፊያ ከድሮም የነበረ ሲሆን፤ በአዲስ መልክ እንዲገነባ ተብሎ ብዙ ሚሊዮን ፈሥሶበት እድሳት ተደርጎለታል። በ’ርግጥ ፋና ሬድዮ 42 ሚሊዮን ብር ወጣበት ሲል፤ ምሽቱን የኢትዮያ ቴሌቪዥን ደግሞ (ጭቃውን አይቶ ነው መሰል)  “33 ሚሊዮን ብር የወጣበት ኤር ፖርት ተመረቀ” ብሏል። እርስ በርሱ የተጣረሰ የገንዘብ ልክ ቢጠቅሱም፤ በ’ኛ በኩል የኮምዩኒኬሽን ሚንስትር መስሪያ ቤት ያወጣውን መረጃ ወስደናል (ዜናውን መጀመሪያ ያሰራጨውም ይኸው መስሪያ ቤት ነው)።ይህ ከኮምዩኒኬሽን መስሪያ ቤቱ የተገኘ ዜና ነው። ከዚህ በመቀጠል ደግሞ የኢትዮጵያ አውሮፕላን ሲያርፍ የነበረውን ሁኔታ በፎቶ አስደግፈን እናቀርብላችኋለን። “ይህ ስራ 73 ሚሊዮን ብር የሚያስወጣ ነው ወይ?” የሚለውን ምላሽ ግን ራሳቹህ ትሰጣላቹህ። በዚህ አጋጣሚ በማህበራዊ ድረ ገጽ (Facebook) ላይ ፤ እነዚህ ፎቶዎች ሲለጠፉ ህዝቡ የሰጠውን ቀልድ አዘል አስተያየቶች እናስነብባቹሃለን።እንደ ሚንስትር መስሪያ ቤቱ መግለጫ ከሆነ አዲስ የተመረቀው የደምቢዶሎ አየር ማረፊያ 73 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት መሆኑን ከገለጸ በኋላ፤ የኦሮሚያ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሙክታር ከደር፣ የትራንስፖርት ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና ሌሎች ባለስልጣናት በተገኙበት የአውሮፕላን ማረፊያው የተመረቀ መሆኑን ፎቶ በማስደገፍ ገልጿል። ዜናው እንዳብራራው ከሆነ …የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ስራ አሰፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ዳዊት፥ …የአውሮፕላን ማረፊያው የሀገር ውስጥ በረራዎችን በተሟላ ደረጃ ለማስኬድ የሚያስችል አደረጃጀት እንዳለው አስገንዝበዋል… ይላል።

በነገራቹህ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ 23 የአውሮፕላን ማረፊያዎች ሲኖሩ፤ 73 ሚሊዮን ብር ወጥቶበት ያላማረበት የደምቢዶሎው አውሮፕላን ማረፊያው ሲሆን፤ የተሰራው መንደርደሪያ አስፋልት 2 ኪሎ ሜትር ወይም 1 ማይል+ ርዝመት ብቻ ያለው መሆኑን ልብ ይሏል።

ትንሽ ፈገግ ካሰኙን አስተያየቶች መካከል አንዱ፤ “አየር መንገዳችን በመስመር ማረስና መዝራት ለግብርና ሚንስቴር እያስተማረ ነው።” ይላል። ሌሎች አስተያየቶችም ይቀጥላሉ።

-የደምቢዶሎው አውሮፕላን አዲስ አበባ አየር ክልል ሲገባ፤ ጎማው በመቆሸሹ ቦሌ እንዳያርፍ ተከለከለ

-73 ሚልየን ብር ለደን ምንጠራ ነው? ሃሃሃ

-ዝናብ ሲዘንብ አውሮፕላኑ ቦቲ ጫማ አድርጎ እንደሚያርፍ ተስፋ እናደርጋለን-እዚህ ላይ አሞራ ራሱ እሺ ብሎ ሚያርፍ አይመስለኝም ክክክ

-ወቼው ጉድ ……! ይሄ ስራስ ባለ ስንት ዲጂት እድገት ያስገኝልን ይሆን ?

-በቅርቡ የታንክ ወይም የትራክተር ጎማ የሚገጠምለት መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መንግስት ገለጸ

-አሜሪካ በውሃ ላይ የሚያርፍ አውሮፕላን ሰራች፤ ኢትዮጵያም በጭቃ ላይ የሚያርፍ ፈለሰፈች።

-ጭቃ ማርሽ የሌለው አውሮፕላን ደምቢ ዶሎ መብረር የለበትም።

-ቀልድ ነው አይደል? በማርያም እኔ እልገባኝም ንገሩኝ

-የእብድ ቀን አይመሽ አለች እማማ. . . ሳሩን ለማሳጨድ ነው 73 ሚሊዩን የተከፈለው?

-በ73ሚሊየን.. አንድ አውሮፕላን ቢገዙበት አሪፍ ነበር፤ ከጎደለ እንሞላላቸዋለን።

 

-ኧረ ክረምት ነው… ፕሌኑ እንዳይሰምጥና ሳይደላኝ መሳቅ አልፈልግም።dembidolo2

-የእርሻ አውሮፕላን ነው? እያረሰ ነው እሚመስለው’ኮ።

-ኣውሮፕላኑ ችግር ገጥሞት የሆነ እርሻ ውስጥ ያረፈ ነው ሚመሰለው!

-አውሮፕላን ጭቃ ላይም ያርፋል እንዴ!?

-ማ ነበረ “ከጥይትና ከርሀብ የተረፈውን ህዝብ በሳቅ እየፈጁት” ነው ያለው?

-አስፓልቱ እኮ ከስር ነው ያለ። እንዳይጎዳ ነው ከላይ ጭቃ የቀቡት…. እንዳይበላሽ!!!

-ለማስመረቅ ያህል… ምናለበት በኮብል ስቶን ሸፈን ቢያረጉት?

-ኧረ እነዚህ ሰዎች ወደ ፃድቃኔ ማርያም ሄደው፤ ሁለት ሰባት ጸበል ከፍልጥ ጋር፤ ሳያስፈልጋቸው አይቀርም፨

-ምንድነው ነገሩ? ክረምት ክረምት የት ሊያርፍ ነው?

-“የደምቢ ዶሎ ኤርፖርት ለትግራይ ህዝብ ምኑ ነው?” ሟቹ ጠ/ሚ በኮፒራይት እላይ ስሄድ እንዳይከሰኝdembidolo

-ይሄን ሚሊዩን የሰው ስም አደረጉት እኮ! ወይ ነዶ

-አውሮፕላን በአፈር ላይ ማብረር ተጀመረ እንዴ? እኛኮ ሁሌ አንደኛ ነኝ ታድለን።

-ታዲያ ለምንድነው ህዝብ ቢጠላቸው የሚደንቃቸው?

-ፓይለቱ…. ዶዘር ኦፕሬተር ነበር አደንቀዋለሁ።

-ግብርና መር — አውሮፕላን ማረፊያችን።

-የኦሮሚያ ባለስልጣኖች ብሩን ቃም አደረጉት አይደል? አድናቂያቸው ነኝ።

ህዝቡ እየሰጠ ያለው አስተያየት በጣም ብዙ ነው። ከላይ የገለጽናቸው እና ለህትመት ያበቃነው በጣም ጥቂቱን ነው። ለስንብት ያህል አንድ እንመርቅና እንሰነባበት።

በቅርብ ቀን… የበረራ አስተናጋጇ እንዲህ ትላለች ተብሎ ይጠበቃል። “ክቡራን የደምቢዶሎ ተሳፋሪዎች አዉሮፕላኑ በጭቃ ስለተቀረቀረ፤ እባካቹህ አንዴ ወርደን እንግፋዉ”

በኛ በኩል አበቃን። የደምቢዶሎን ኤርፖርት ሰራተኞች እና ፓይለቱን እናደንቃለን። ፎቶ አንሺ እና አስተያየት ሰጪዎችንም ከልብ እናመሰግናለን።

dembidolo7-300x225

ባለስልጣኖቹ.. አቶ ሙክታር እና አቶ ወርቅነህ ከአውሮፕላኑ ሲወርዱ።

dembidolo3-150x150

ህዝቡ 73 ሚሊዮን ብር ያወጣው ኤርፖርት ላይ በመገኘት ጉብኝት ሲያደርግ

dembidolo5-300x225

አረሱት

Leave a Reply