የሕውሐቱ አሻንጉሊት ድርጅት ብአዴን፤ በነገራችን ላይ ብአዴንን አሻንጉሊት ብለን ስንል እውነት እንጅ ስም ለማጉደፍ እንዳልሆነ ለማንም ግልጽ ይመስለኛል፡፡ ለዚህ ማረጋገጫውም በለፈው ጊዜ ወያኔ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ ብአዴን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በአማራ ሕዝብ ላይ ለተፈጸሙ ግፎችና ኢሰብአዊ ድርጊቶች ምንም ዓይነት ምላሽ ሰጥቶ ያለማወቁን ከገለጽኩት በተጨማሪ ሌላ ማረጋገጫ መጥቀስ ቢያስፈልግ፦ እስከ የወያኔ የመጀመሪያዎቹ የአገዛዝ ወቅት ድረስ ሥያሜው ኢሕዴን (የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቅ) የነበረው የዛሬው ብአዴን (ብሔር አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) ሥያሜው ትግርኛ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ይህን ሥያሜ አማርኛ እናድርገው ብንል ይሆን የነበረው አሕዴን (የአማራ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) ነበር የሚሆነው፡፡
እናም ይህ ድርጅት ከሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲነት (የእምነተ አሥተዳደር ቡድንነት) ወደ ብሔር (ብሔረሰብ) ተኮር ሲቀየር የክልሉ ተወላጅ ያልሆኑትን ወደየክልላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች መሸኘት ሲኖርባቸው የፌዴራላዊ (የራስ ገዛዊ) አወቃቀርን ሥርዓት መብትንና ግዴታን በቀጥታ በሚጻረር መልኩ የአማራ ተወላጆች እንዳልሆኑ በይፋ የሚታወቁ ግለሰቦችን ይዞ መቀጠሉ (ኦኦ ይቅርታ አማርኛውን ላስተካክለው) የአማራ ተወላጆች ያልሆኑ ግለሰቦችን ይዞ እንዲቀጥል መደረጉ ወይም መገደዱና እነኝህ ግለሰቦችም የብአዴንን ከፍተኛ የወሳኝነት ሥልጣን መያዛቸው የብአዴንን አሻንጉሊትነትና የፌዴራል (የራስ ገዝ) አሥተዳደሩንም የይስሙላነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ጉዳይ ነው፡፡ ድርጅቱ የአማራ ከተባለና ራስ ገዛዊ ከሆነ ሊመራ ሊተዳደር የሚገባው በአማሮችና በአማሮች ብቻ ነበር፡፡ ትግሬም አገውም ሌላም ሊካተት አይችልም፡፡ ይህ የአሐዳዊ መንግሥት አሠራር እንጅ የራስ ገዛዊ አሠራር አይደለምና፡፡
እንከተለዋለን የሚሉት ሥርዓት ራስ ገዛዊ ከሆነ ትግራይ ከአምስት ተከፍላ ኢሮቡም ኩናማውም ሌሎቹም ራስ ገዝ መሆን ይኖርባቸዋል በሌሎች ክልሎች ያሉ ጎሳዎችና ብሔረሰቦችም እንደዚያው፡፡ ይህ ሲሆን ብቻ ነው ሥርዓቱ ፌደራላዊ (ራስ ገዛዊ) ነው ማለት የሚቻለው፡፡
በስተቀረ ግን በውስጥ ያሉ ጎሳዎችንና ብሔረሰቦችን እንደሌሉ ቆጥሮ ያሉበትንና ሀገራቸውን በአንዱ ብሔረሰብና ጎሳ ስም ብቻ “የትግራይ ክልል” የአንድ ቀበሌ ሰው የማይሞሉትንም በክልል ደረጃ በማዋቀር “የሐረሪ ክልል” እያሉ ማላገጥና ከሐምሳ በላይ ብሔረሰቦችና ጎሳዎችን በአቅጣጫ ሠይሞ “የደቡብ ክልል” ማለት ፈጽሞ የፌዴራል (የራስ ገዝ) አሥተዳደር ሥርዓትን አያሳይም፡፡
“አይ ስለማይመች ነው! የሚቻል ስላልሆነ ነው!” ከተባለ ደግሞ ቋንቋንና የብሔረሰብ ወይም የጎሳ አሠፋፈርን መሠረት ያደረገ የራስ ገዝ ሥርዓት ለሀገራችን አይሆንም ማለት ነውና የፌዴራል (የራስ ገዝ) አወቃቀሩ ከዚህ ውጭ የደርግን ወይም የዐፄ ኃይለሥላሴን ክፍላተ ሀገር ወይም ጠቅላይ ግዛት መውሰድ ይኖርበታል ካለሆነም በሌላ አከፋፈል አሐዳዊ ሥርዓትን መከተል ይኖርብናል ማለት ነው፡፡
በመሆኑም ይህ የብአዴን ውጥንቅጥ የሚያሳየው ዐቢይ ቁምነገር ቢኖር አገዛዙ የራስ ገዝ ሥርዓትን ከሥያሜው በስተቀር የሥርዓቱን ዘይቤ ሊተገብረው ፈጽሞ የማይፈልግና የማይፈቅድ ይሄንን የሥርዓት ዓይነት ለማወናበጃነት ከመጠቀም ውጪ ለሥርዓቱ በፍጹም ታማኝ አለመሆኑን ነው፡፡
በመሆኑም ነው አቶ በረከትን ጨምሮ በርካታ ትግሬዎችን የአማራ ነው በተባለው ድርጅት ሰግስጎ ድርጅቱ እያየነው እንዳለነው የአማራ ሕዝብ ጉዳይ ጨርሶ የማይገደው የማያሳስበው ይልቁንም የወያኔ መሣሪያ በመሆን የአማራን ሕዝብ የሚያጠቃና የሚያስጠቃ ሊሆን የቻለው፡፡
የብአዴን አባላትን የምጠይቀው ጉዳይ ቢኖር እንደሚሉት ድርጅቱ የአማራ ከሆነ ከቀበሌ እስከ ብአዴን ከፍተኛ የሥልጣን ደረጃ ያሉት የትግሬ (የተግሬ) ተወላጆች እነ በረከት ምን ይሠራሉ???
መቸም እናንተ እኮ አታፍሩም! “እኛ አማሮች እራሳችንን ማሥተዳደር ስለማንችልና ብቃት ያለው ሰው ስለሌለን ሊረዱን ነው” ሳትሉ አትቀሩም!

እናም ድርጅቱ እንዲህ በትግሬ ተሞልቶ የአማራን ሕዝብ ሳይሆን የወያኔን (የትግሬን, የተግሬን፤ ከዚህ ቀደም መረጃዎችን ጠቅሸ ዐፄ ካሌብ በተደረገላቸው የድረሱልን ጥሪ የናግራን ክርስቲያኖችን ከአይሁድ ጥቃት ለመታደግ የመን ዘምተው በነበሩበት ጊዜ ከድላቸው በኋላ ለባርነት ወይም ለአገልጋይነት ከየመን ይዘዋቸው የገቡ በመሆናቸው እንደሆነ ተግሬ በጊዜ ሒደት ተቀይሮ ትግሬ የተባሉት ማለቴ ይታወሳል) እናም ብአዴን የነሱ ጥቅም አስጠባቂ ሆኖ ይሄንንም በጸጋ ተቀብላቹህ ከራስ ገዛዊው ሕግና ሥርዓት ውጪ እያስተናገዳቹህ “ብአዴን የራስ ገዛዊው የአማራ ድርጅት ነው” ስትሉ ትንሽ እንኳን አታፍሩም?
ወያኔ የአማራን ሕዝብ ካለማመኑና ለመጨቆንና ለመቆጣጠር ካለው ዕኩይና ጽኑ ፍላጎቱ የተነሣ ከመንግሥት መዋቅር ውጪ ያሉ እንደ እድር፣ የሰበካ ጉባኤ፣ ማኅበር የመሳሰሉ በክልሉ ሕዝብ ያሉ የማኅበራዊ መዋቅሮች የአሥተዳደር ቦታዎች እንኳን አይቀሩም በትግሬ እንዲያዙ ሲያደርግ፡፡ ወያኔ ሥነልቡናዊ ወንድነቱ ቆራጥነቱ ወይም ቆፍጣናነቱ የተሰለበ እንደ እንስሳ ሆዱ ብቻ የሚያሳስበው እንደፈለገ የሚያሽከረክረውንና የሚረግጠውን ኅሊናውን የሸጠ ሆዳም መሆኑን ካላረጋገጠ በስተቀር ወያኔ በብአዴን ውስጥ በሥልጣንም ሆነ በአባልነት አንድንም የአማራ ተወላጅ አይቀበልም አያካትትም፡፡
ሰዎች ብአዴን ውስጥ ያሉ ባለሥልጣናትን እየጠቀሱ “አቶ እከሌ ተቆርቋሪ ነው፣ አቶ እከሌ እንደዚህ ነው” ሲሉ እኔ ይገርመኛል! የወያኔን ዘዴ አለማወቃቸው ነው፡፡
ወያኔ ሁሌም የቸገረ ነገር ሲያጋጥመው ሁለት ዓይነት ገጸ ባሕርያትን ይዞ ነው የሚቀርበው፡፡ አንደኛው አጥቂ ሌላኛው ተቆርቋሪ ሆነው ይቀርባሉ፡፡ አጥቂና ግትር አቋም የያዘው አካል የማይሆንለት ከሆነ ተቆርቋሪና ለዘብተኛ መስሎ በቀረበው አካል ያጋጠማቸውን ወይም የተጋፈጡትን ችግር ለመፍታት ለማለዘብ ለማስቀየስ ጥረት ያደርጋሉ፡፡
እስከ አሁን ድረስ “አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለአማራ ለማንነታቸው ተቆርቋሪ ናቸው…” የሚባለውን ነገር ሊያረጋግጥልኝ ሊያሳምነኝ የሚችል አንዳች ነገር ላገኝ አልቻልኩም፡፡
እኔ የሚመስለኝ ሰውየው ተቆርቋሪ መስሎ የሁለተኛውን የወያኔ የአቀራረብ ገጸባሕርይ እየተጫወተ ወይም እየተወነ ያለ ነው የሚመስለኝ፡፡ እንዲህ እንዲያደርግ የተፈለገበት ምክንያትም የአማራ ሕዝብ በብአዴን ተስፋ ቆርጦ ጉዳዩን በራሱ በመወጣት በራሱ ቆራጥ እርምጃ መፍትሔ ወደ መሻት እንዳይሸጋገር ዝም ብሎ ተስፋ እያደረገ እንዲቀመጥ ለማድረግ ነው እንጅ የገቢዎች ሚንስትር የነበረውን አቶ መላኩ ፈንታን ከጉራፈርዳ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን ጉዳይ በብአዴን እንዲታይ በመጠየቁ ከብአዴን ስብሰባ በመመለስ ላይ እንዳለ ቦሌ ከአውሮኘላን (ከበረርት) ሲወርድ ተቀብሎ ወዲያው የፈጠራ ክስ መሥርቶ ወኅኒ የወረወረ አገዛዝ አቶ ገዱ የተወራውን ነገር እያደረጉ ይታገሳል ብሎ ማመን ሲበዛ ቂልነት ነው የሚመስለኝ፡፡
ሲጀመር አቶ ገዱ ይሄንን ያህል ቁርጠኝነቱ ተቆርቋሪነቱና እልሁ ካላቸው በወያኔ አሻንጉሊት ድርጅት ውስጥ ተቀምጠው የወያኔ አገልጋይ የመሆን አቅል ስሜት ፍላጎትና ትዕግሥት ይኖራቸዋል ብየ አልገምትም፡፡
ሲቀጥል አነሧቸው የሚባሉት አቋሞች ብአዴን ውስጥ እንዳልተሠራባቸው እያዩ በአገዛዙ ሕገወጥ ጣልቃገብነት ሲሻሩ እየተመለከቱ ወይ ሥልጣናቸውን በመጠቀም የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ ጥረት ያደርጉ ነበር እንጅ እንዲህ እየሆኑ በሥልጣን መቆየትን ሊሹ የሚፈልጉበት አንዳችም ምክንያት አይታየኝም፡፡
በእርግጥ የወያኔ ቅጥ ያጣና መረን የለቀቀ ስድብ ንቀት ዘለፋ ግፍና ጥቃት ያስቆጫቸውና ያንገበገባቸው ከዚህም የተነሣ በወያኔ ላይ ፊታቸውን ያዞሩ ማንነታቸውን ወደማሰብ ለሕዝባቸው ወደመቆርቆሮ የተመለሱ አንዳንድ የብአዴን አካላትን አውቃለሁ፡፡ ይሁንና አቶ ገዱ ግን ከእነኝህ ውስጥ አንዱ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥልኝ መረጃ አላገኘሁም፡፡ ስለሆነም የሚባለውን ነገር ለማመን እቸገራለሁ፡፡
ወደቀደመው ነገራችን እንመለስና የአማራ ሕዝብ ድርጅት ነኝ ባዩ የወያኔ አሻንጉሊት ድርጅት ብአዴን ትናንት 25,11,2008 ዓ.ም. በሁለት ባለሥልጣናቱ በኩል ከአሜሪካ ራዲዮ (ነጋሪተ ወግ) የአማርኛ ድምፅ አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት “ምንም እንኳ ሰልፉ ዕውቅና የሌለው ሕገወጥና የጥፋት መልዕክት የተላለፈበት ቢሆንም ሰላማዊ ስለነበር ለዚህ ዕውቅና እንሰጣለን” በማለት ብአዴን አቋሙን እንደገለጸው ጎንደር ከተማና በጎንደር የተለያዩ ወረዳዎች በ24,11,2008ዓ.ም. የተደረጉትን ደማቅ የአማራ ሕዝብ የተቃውሞን ሰልፍ እንዲያ በማለት ፈርጇል፡፡
እስኪ መጀመሪያ “ዕውቅና የሌለው ሕገወጥ” የሚለውን እንይ፦ ብአዴን ወይም ወያኔ ይሄንን ሰልፍ “ዕውቅና የሌለው ሕገወጥ!” ሲል ሊጠራው በፍጹም አይችልም፡፡ ምክንያቱም አንድን የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የአገዛዙ ፈቃድ እንደሚያስፈልግ የሚያዝ ወይም የሚጠይቅ ወይም የደነገገ ሕግ በሀገራችን የለምና ነው፡፡ ሕገ መንግሥታቸው የሚለው “አስታውቅ” ነው፡፡ የማሳወቁ አስፈላጊነትም አገዛዙ ዕውቅና ሰጥቸዋለሁ ሰልፉን አድርጉ ፣ አልሰጠሁትም አታድርጉ እንዲል ሳይሆን ሥነሥርዓት የሚያስከብሩ የጸጥታ አካላትን እንዲመድብ፣ ሰላማዊ ሰልፉ ሊደረግ በታሰበበት ቦታ ላይ በተመሳሳይ ቀን ተመሳሳይ ሌሎች ኩነቶች ለማድረግ እንዳይታቀድና የኩነቶች መደራረብ ችግር እንዳይፈጠር ሥርዓት ማስያዝ እንዲችል ለማድረግ ብቻ ነው፡፡
በዚህም መሠረት ሰልፉ እንደሚደረግ እንዲያውቁ ተደርጓል፡፡ ነገር ግን ሰልፉ እንዲደረግ በፍጹም ፈቃደኛ አልነበሩም፡፡ ሰልፉ እንደሚደረግ ስላወቁማ ነው በነሱ አማርኛ ሰልፉን ከመደረጉ ከሳምንት በፊት ጀምረው ሕገ ወጥ እንደሆነ ሲለፍፉ የሰነበቱት፡፡ ይሄ ልፈፋቸው ሰልፉ እንደሚደረግ ማወቃቸውን ያረጋግጣል፡፡
ያለው ሀቅ እንዲህ በሆነበት ሁኔታ ወያኔ በምንም ተአምር ሰልፉን “ዕውቅና የሌለው” ስለዚህም “ሕገወጥ” ሊል የሚችልበት አንድም ዓይነት ሕግና አሠራር የለም፡፡ በገለጽኩት መልኩ ሕጉን ተከትሎ የተከናወነን የተቃውሞ ሰልፍን “ሕገወጥ” ካሉ ሕገወጦቹ በሕግ መሠረት የማይሠሩት እነሱ እንጅ ሕዝብ አይደለም፡፡
ሕዝብማ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረግ ብቻም አይደለም በተቃውሞ ሰልፉ እንዲስተካከሉ እንዲፈጸሙ የጠየቃቸው ጉዳዮች በአፋጣኝ ካልተፈጸሙና ካልታረሙ አንባገነን አገዛዙን በዐመፅ የማስወገድ መብት ኃላፊነትና ግዴታም አለው እናደርገዋለንም፡፡
ከላይ እንደገለጽኩት አሻንጉሊቱ ብአዴን ሰልፉን “… የጥፋት መልዕክት የተላለፈበት” ሲል ጠርቶታል፡፡ ለመሆኑ የትኛው መልዕክት ነው የጥፋት መልዕክት? የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄው ነው የጥፋት መልዕክት?፣ የወያኔ ሀገርና ሕዝብ በታታኝነት መወገዙ ነው?፣ ወያኔ በአማራ በኦሮሞና በሌሎችም የሚፈጽመው ግፍና በደል እንዲቆም መጠየቁ ነው? የቱ ነው የጥፋት መልዕክት? የጥፋት መልዕክት ማለትስ ራሱ ምን ማለት ነው? ሕዝብ ከተጨባጭ እውነቱና ሕይዎቱ ተመሥርቶ ያንጸባረቀውን ሐሳብ ወይም አስተሳሰብስ የጥፋት መልዕክት ማለት ይቻላል ወይ? ብአዴን እወክለዋለሁ የሚለውን የአማራን ሕዝብ ሐሳብ፣ ጩኸትና ጥያቄ ሳይጋራ፣ ሳያንጸባርቅ፣ ሳያራምድ፣ ሳይይዝ ተቀጣሪ ወይም አሻንጉሊት እንጅ “የአማራ ሕዝብ ድርጅት ነኝ” ሊል ይችላል ወይ??? በሚሉ ጥያቄዎች ብአዴንን ብንመረምረው ብንፈትሸው ብንሞግተው በኢትዮጵያ ውስጥ ግፈኛው ወያኔ ብቻ እንጅ ብአዴን ምንትስ የሚባል ከነአካቴው እንደሌለ ልናረጋግጥ እንችላለን፡፡
ከሰልፉ ቅር ያሰኙ ጉዳዮችን ሳነሣ፦ ሰልፉ የራሱን አጀንዳ (ርእሰ ጉዳይ) ይዞ የተጠራ ሰልፍ ቢሆንም ማዕከላዊነትን በጠበቀ መልኩ የተደራጀ ሰልፍ ስላልነበረ በዚህ ክፍተት ምክንያት ከፊሎቹ በራሳቸው ተነሣሽነት የእነ አቶ በቀለና የአቶ ሀብታሙ ጉዳይ በሰልፉ መነሣቱ የአማራ ሕዝብ የዜጎች ሰብአዊ መብቶች እንዲከበር ካለው ጽኑ ፍላጎት አኳያ ነው እንጅ አቶ በቀለና ጓዶቻቸው እያራመዱት ላለው ዘውግን መሠረት ላደረገው ፖለቲካዊ አስተሳሰባቸው ድጋፍ ለመስጠት ወይም ደግሞ ሰውየው ከዚህ ቀደም የአማራን ሕዝብ በተመለከተ “የአማራ ሕዝብ ቀድሞ ገዥዎች ለፈጸሙብን በደል ይቅርታ ሊጠይቀን፣ ካሳ ሊከፍለን ይገባል! ካልሆነ ግን አብሮ ለመኖር ይቸግረናል!” በማለት ለመሠረተው የፈጠራ ክስና ላስተላለፈው የተሳሳተ ኦነጋዊ የጥፋት አስተሳሰቡ ሰውየው እራሱ ይቅርታ ሳይጠይቅና ሳይታረም እኛ ይቅርታ አድርገንለታል ለማለትም አይደለም፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዳለ ሰቆቃ በሚያይባት ሀገር ወያኔ በአቶ ሀብታሙ ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ ነጥሎ አውጥቶ ማንጸባረቁም በዚሁ ወቅት በተለያዩ ቦታዎች ተመሳሳይና ከዚህም የከፋ ግፍና በደል እየተፈጸመባቸው ያሉ ወገኖችን ዋጋ ማሳነስና እንደሌሉ መቁጠር፣ ከሩቅ ለሚያይ ታዛቢም በዚህ ወቅት ወያኔ የፈጸመው ግፍ ይህ የሀብታሙ ብቻ እንደሆነ ስለሚያስመስል በመሆኑ የሀብታሙ ጉዳይ ተነጥሎ መውጣቱም ትክክል አልነበረም፡፡
በተረፈ በመጪዎቹ ቀናትና ሳምንታት በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሊደረጉ በታቀዱ የተቃውሞ ሰልፎች በነቂስ በመውጣትና ለወያኔ ሕገወጥ ፍረጃ ባለመበገር የመጨረሻውን ሕዝባዊ ማስጠንቂያችንን እንድናሰማ ወንድማዊ መልዕክቴን ማስተላለፍ እወዳለሁ፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

Amsalu Gebrekidan Argaw's photo.

Leave a Reply