ትዝብት፡
1. ትብብር፡ በምድረ በኢትዮጵያ የጎደለ ነገር ትብብር ነው፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲያስጠቃ የኖረው የትብብር ጉድለት ነው፤ ትብብርን ኢትዮጵያዊ ባሕርይ እንዳይሆን የአዳፍኔ ሥርዓቶች ሁሉ ተግተው የሠሩበት ነው፤ ተሳክቶላቸዋልም፤ ዛሬ የጎነደር ሕዝብ ይህንን የቆየ አጉል ባሕርይ ሰብሮ ሰው ሁሉ ከየቤቱ እንዳይወጣ ለማድረግ ማስተባበራቸውና መሳካቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ አዲስ የኑሮ ጥበብን እንደፈጠረ የሚቆጠር ነው፤ አንዱና ዋናው የኢትዮጵያውያን ችግር መተባበር አለመቻል ነው፤ ሁሉም የሚቀናው ፉክክርና ጠብ ነው፤ ጎንደር ይህንን ጥበብ ይዞ ካቆየውና ከተጠቀመበት ኢትዮጵያ ተስፋ አላት ማለት ነው፡፡
2. በአንጻሩ ፖሊሶቹ አንዱን ሰው አራትና አምስት እየሆኑ በጭካኔ በዱላ በመደብደብና በጫማ በመርገጥ፣ የወደቀውን ሰው ከሩቅ ድረስ እየሮጡ መጥተው መደብደብ የሚያሳፍርና አንገትን የሚየሰደፋ የአገር ውርደት ነው፤ እነዚህ ፖሊሶች ለሥራ የተሰማሩ አይመስሉም፤ የግል ቂም ለመወጣት ታጥቀው የወጡ ይመስላሉ፤ ልጆችን ለመደብደብና ለማሰቃየት ያላቸው ጉጉትና ደስታ ከሰው የተፈጠሩ አያስመስላቸውም፤
3. የጎንደር ሕዝብ ቆራጥነትም የሚደነቅ ነው፤ ለብዙ ዓመታት ሲንተከተክ የቆየ ስሜት ገንፍሎባቸው ሲነሡ የገነፈለ ስሜታቸውን ለመቆጣጠር ያሳዩት ትእግስትና የትግል ስልት በጣም የሚያስመሰግናቸው ነው፤ ዓላማቸውን ሳይስቱና በፖሊሶቹ የጭካኔ ድብደባ
4. በአንጻሩ በአገዛዙ ባለሥልጣኖች በኩል የሚታየው የቆራጥነት መጥፋትና ከተለመደው የጡንቻ መንገድ መውጣት በፍጹም እንዳቃታቸው ነው፤ አእምሮ ቢሠራ ከጡንቻ ይልቅ መነጋገርን መምረጥ ሕዝቡን ወደተሻለ አቅጣጫ ይመራዋል፤
በአጠቃላይ ስናየው ሕዝቡ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚያሳየው ንቅናቄ አገዛዙንና ደጋፊዎቹን በጣም እንደቀደማቸው ነው፤ አዲሱን የለውጥ መንፈስ በአሜሪካ እርዳታ ተማምኖ ለማገድ መሞከር ቂልነትና አደገኛ ነው፡
http://www.ethiopanorama.com