HE

የትግሬ ወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ላይ ላለፉት 25 ዓመታት ጭኖት የኖረው በዘረኝነት ላይ የተመሠረተው ያንድ ነገድ የበላይነትና የውስጥ ቅኝ አገዛዝ ሥርዓት በሕዝቡ የእንቢተኝነት እንቅስቃሴ ከመኖር ወደ አለመኖር እየተሸጋገረ ነው። የወያኔ አገዛዝ ሲጀመር ጀምሮ ደካማ «መንግሥት» እንደሆነ ይታወቃል። የድክመቱ መገለጫም፣ አንደኛ፣ የአናሳዎች መንግሥት በመሆኑ የአብዛኛውን ሕዝብ ድጋፍ ያገኘ አይደለም። ሁለተኛ፣ የሚገዛው በኃይል በጦር መሣሪያ አስገድዶ እንጂ፣ በሕግ የበላይነት ተወዶና ተፈቅሮ አይደለም። ምንጊዜም በኃይል ሕዝባቸውን የሚገዙ አገዛዞች ደካማዎች እንደሆኑ የፖለቲካ ሣይንስ ሀሁ ይነግረናል። ወያኔም ከአፈጣጠሩ፣ከሚያራምደው የዘር ፖለቲካና ከባሕሪው በሚመነጭ ምክንያት ደካማ ነው። ሦስተኛው ወያኔ ከድክመቱ ብዛት የተነሳ፣ ራሱ እመራበታለሁ ብሎ፣ «በሕዝብ ተሳትፎ አጸደቁት ላለው ሕገ መንግሥት» ተገዥ አለመሆኑ የድክመቱ ሁሉ መገለጫ ነው። ይህም በመሆኑ፣ ሲጀምር ጀምሮ የወያኔ አገዛዝ፣ ደካማ ነው። ደካማ መንግሥት ደግሞ መውደቁ የግድና አይቀሬ ነው።

የደካማ መንግሥታት የመጨረሻ እጣ ፋንታም፣ በኃይል ሥልጣን እንደወጡ፣ በኃይልም ሕዝብን ሲገዙ እንደነበሩ፣ በኃይል ከያዙት ሥልጣን መወገድ ነው። ይህ ነባራዊ ዕውነታ ነው። በወያኔም ላይ እየሆነ ያለው ይኸው ነው። ወያኔ በየትኛውም መልኩ ሕጋዊና ተቀባይነትን አግኝቶ ሕዝብን ያስተዳደረ ቡድን አይደለም። ለ25 ዓመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ተፈናጦ የኖረው፣ በዘር ላይ ባደራጀው የመከላከያ፣ የፀጥታ፣ የፍርድ አካላት፣ በዘራው የዘረኝነት ፕሮፓጋንዳና የስለላ መዋቅር፣ በኢትዮጵያውያን አንድነትና ኅብረት ማጣት ታግዞ መሆኑ እርግጥ ነው። ይሁን እንጂ፣ ሁሉም ነገር የራሱ ወሰንና ገደብ ስላለው፣ ወያኔ ሕዝቡን በነገድ ከፋፍሎ፣ ነጣጥሎና አናክሶ የመግዛቱ፣ ባንድ ዘር ላይ በመተማመን የተገነባው የመከላከያ፣ የፖሊስ፣ የደህንነትና የፍርድ አካላት መዋቅር ከሚገባው በላይ በመለጠጡ፣ የሕዝቡን ግፊትና አመጽ ሊቆጣጠርበት ከማይችለው ደረጃ ላይ አድርሶታል።

በዚህም የተነሳ፣ በሐምሌ 2008 ዓም መግቢያ ላይ እስራኤል በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተመራው ሕዝባዊ ተቃውሞ፣ በኢየሩሳሌም ገዳም ላይ ይውለበለብ የነበረው፣ ለኢትዮጵያ ነገዶች መከፋፈልና መነጣጠል መሪ የሆነው፣ «የሰይጣን አምላኪዎች ምልክት» የያዘውን፣ በሕዝቡ አጠራር «አምባሻ» ያረፈበትን ሠንደቅ አውርደው፣ የሃይማኖት፣ የጀግንነት፣ የተስፋ፣ የልምላሜና የመስዋዕትነት ልዩ እና ዕንቁ ዕሴቶቻችን መገለጫ በመሆን የሚያንጸባርቀው አረንጓዴ፣ ብጫ እና ቀይ ደማቅ ሠንደቅችን ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ አድርጓል። ይህን ፈለግ በመከተል፣ ጀግናው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ፣ የወልቃይት-ጠገዴ የዐማራነት ጥያቄ ፊታውራሪ በለኮሰው የሕዝባዊ እንቢተኝነት እንቅስቃሴ፣ ጀግኖቹ የጎንደር ወጣቶችና አዛውንት የወያኔ/ብአዴንን እራፊ ጨርቆች አውርደው የኢትዮጵያዊነት፣ የነፃነት ዐምድ ቋሚ መገለጫ፣ ከኢትዮጵያ ድንበር አልፎ፣ የአፍሪካውያን የነፃነት ቀንዲል በመሆን ያገለገለችውን ሠንደቅ በክብር ቦታዋ መልሰው፣ ለ25 ዓመታት እጅግ ለናፈቃት የጎንደር አየር አብቅተዋታል።

በተመሳሳይ ሁኔታ የአይደፈሬው የእነ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ፣ የእነ ፊታውራሪ ነጋሽ በዛብህ ትውልድ የሆነው ጎጃሜ በባሕር ዳርና በደብረ ማርቆስ ከተሞች ባካሄዱት መሬት አንቀጥቅጥ የተቃውሞ ሕዝባዊ አመፅ፣ ሠንደቃችን ከፍ ብላ እንድትውለበለብ አድርገዋል። ይህ ሂደት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየው የወያኔው አገዛዝ ቋሚ መሠረት አድርጎ የሚመራበት «ሕገ መንግሥት» ተብየ በሕዝቡ ድምፅና ነፃ ውሣኔ የተሻረ መሆኑ ነው። ይህን ተከትሎም ወያኔ «ለሕገ-መንግሥቱ እና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ» ቆሜአለሁ እያለ ጧት ማታ ሕዝቡን የሚያደነቁረው፣ ከሕዝቡ ቀድሞ ራሱ ያፈረሰውና ለእርሱም ታማኝነት እንደሌለው ይታወቃል። ሆኖም በሰሞኑ የዐማራ ነገድ ሕዝባዊ እንቢተኝነት የቆመበትን ምድር ርዕደ-መሬት ስላናወጠው፣ ራሱ ያወጣውን ሕግ በመጣስ፣ በራሱ አሻንጉሊቶች ይመራ የነበረውን «የዐማራ ክልል ምክር ቤት» ተብየና በዚሁ ምክር ቤት ተመሠረቱ የተባሉትን ተቋሞች አፍርሶ፣ የዐማራ ክልል የተባለውን በአምስት ቀጣና ወይም የዕዝ ሰንሰለት አዋቅሯል። በምትካቸውም ከዐማራና ከትግሬ፣ ከዐማራና ከኤርትራዊ፣ ከዐማራና ከቅማንት፣ ከዐማራና ከአገው በተወለዱ፣ በፀረ-ዐማራነት ወያኔ ኮትኩቶ ባሳደጋቸው ሰዎች ሕዝቡ እንዲጨፈጨፍ አደራጅቶና ዐማራውን ባሻቸውና በፈለጉት መንገድ እንዲገሉ ገደብ የለሽ ሥልጣን ሰጥቶ አሰማርቷቸዋል።

እነዚህ አዲሶቹ የዐማራው ገዳዮችና አስገዳዮች፥ መቀመጫውን ደብረ ማርቆስ ላደረገው የምሥራቅ ጎጃም ገዳይና እስገዳይ  ዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል፣ መቀመጫውን ባሕርዳር ላይ ላደረገው የምዕራብ ጎጃም ገዳይና አስገዳይ፣ ብናልፍ አንዱአለም፤ ለሰሜንና ደቡብ ወሎ ገዳይና አስገዳይ ፣ ዓለምነው መኮንንና ገነት ዘውዴ፣ ለሰሜንና ደቡብ ጎንደር  ገዳይና አስገዳይ ተፈራ ደርበውና አይለኝ ሙሉዓለም መሆናቸው ታውቋል። የእነዚህን የግድያና የአፈና ተግባር በበላይነት የሚመራውና የሚቆጣጠረው፣ በዐማራ ነገድ ጥላቻ ተወልዶ ያደገው የአክሱም ተወላጁ ትግሬው ዐባይ ፀሐዬ እንደሆነ ስንገነዘብ፣ ወያኔ ዐማራውን አጥፍቶ ለመጥፋት ቁርጠኛ ውሣኔ ላይ የደረሰ መሆኑን ለመረዳት የሚከብድ አይሆንም። በተመሳሳይ ሁኔታ፣ የጎንደር ከተማ ሹምና የፀጥታ ኃላፊ የነበሩትን አንስተው በምትካቸው የጎንደር ከተማን ወጣት ባሻቸው መንገድ ሊገድሉ የሚችሉ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች እያሰለጠኑ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ወያኔ ዐማራን አጥፍቶ ለመጥፋት መጠነ ሠፊ ዝግጅት አድርጎ፣ ዝግጅቱን ተግባራዊ እያደረገ ነው። ፀረ-ዐማራ የሆኑ ቡድኖችና ግለሰቦች በፊናቸው፣ ከወያኔ ግድያ የተረፈውን ዐማራ በቃርሚያ ለቀማ መልኩ ለቅመው ለማጥፋት የትብብርና የአንድነት ስምምነቶች እያደረጉ እንደሆነ እየሰማን፣ እያየን ነው። በአንፃሩ «ተማርኩ፣ አውቃለሁ» የሚለው የዐማራው ክፍል፣ አሁንም አባቶቻችን «በሬ ካራጁ ጋር ይውላል» የሚሉት አባባል እውነት ሆኖ፣ ካራጆቻቸው ጋር ለወገኖቻቸው የእርድ ቦታ ሲያዘጋጁ ይስተዋላሉ። የዐማራው ነገድ ወጣትም ሆነ አዛውንት ልብ ሊለው የሚገባው መሠረታዊ ጉዳይ፣ የሚሳሳላት የኢትዮጵያ አንድነት ጉዳይ በዐማራው ነገድ አጠቃላይ ጥፋት ላይ መመሥረት፣ ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያ ሊያደርጋት አለመቻሉን ነው። ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ መሆን የምትችለው ሁሉም ነገድና ጎሣዎቿ፣ በአጠቃላይ ሁሉም ዜጎቿ አንዱም ከቁጥር ሳይጎድል፣ በሕግ የበላይነት፣ በግለሰብ ነፃነት፣ በግል ሀብትና በነፃ ኢኮኖሚ ሕጋዊ ጥበቃነት፣ በሰብአዊና ፖለቲካዎች መብቶችና ነፃነቶች መረጋገገጥ ላይ የተመሠረተ ሥርዓት በመመሥረት እንጂ፣ ታላቁንና ለኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ይህ ቀረው ያልተባለ መስዋዕትነት የከፈለውን፤ ለሕዝቡ አንድነት፣ የሙጫነትና የሲሚንቶነት ባሕሪን በመላበስ ሲያይዝ የኖረውን የዐማራ ነገድ ከምድረ ገጽ በማጥፋት አለመሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ግለሰብ ካልኖረ፣ ቤተሰብ አይኖርም። ቤተሰብ ከሌለ ደግሞ መንግሥት አይታሰብም። በዚህ አመክንዮ፣ ዐማራ ራሱ ሳይኖር፣ የመኖር መብቱ ሳይረጋገጥ፣ ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ማሰብ፣ የህልም ሩጫ ከመሆን አያልፍም።

ይህም በመሆኑ፣ በዐማራ ስም ተደራጅታችሁ የምትንቀሳቀሱም ሆነ፣ በየቤታችሁ ሆናችው ስለዐማራ ነገድ ዕልቂትና እርሱንም ለመጨረስ የታቀደው የነገዱ የፈጽሞ ጥፋት የሚያስጨንቃችሁ ወገኖች፣ ያለ የሌለ ኃይላችሁን አሰባስባችሁ፣ ከእሳና ከይሉኝታ ተርታ ወጥተን፣ ነባራዊ ሁኔታውን በግልጽ ልንጋፈጠው ግድ ከሚለን ወቅት ላይ መሆናችንን አውቀን፣ ከወያኔ ውድቀት በኋላ ለሚመሠረተው መንግሥት፣ የዐማራውን ድምፅ በሚገባ ሊወክል የሚችል ፖለቲካዊ ኃይል በአስቸኳይ ሊፈጠር በሚችልበት ጉዳይ ላይ ተወያይቶ አንድ አቋምና ውሳኔ ላይ መድረስ ግድ ይላል።

ይህን በተመለከተ፣ ይህ ጉዳይ ጉዳያችን ነው፣ ሁላችንም ያገባናል፣ የዐማራው ጉዳይ የእኔም ጉዳይ ነው የምንል ወገኖች ባሉት የመገናኛ ዘዴዎች ሁሉ ተጠቅመን ባስቸኳይ በመገናኘት ለጉዳይ አጥጋቢ ዕልባት እንድንሰጠው ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ጥሪውን ያቀርባል። ሞረሽ ወገኔ ይህን ጥያቄ ሲያቀርብ ይህ የመጀመሪው እንዳልሆነ ሁሉ፣ የመጨረሻውም አይሆንም። ምክንያቱን ሞረሽ ወገኔ የዐማራው ኅልውና መጠበቅ ለኢትዮጵያ አንድነት ዋስትና ነው ብሎ ከልብ ስለሚያምን፣ ለኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት የሚቆረቆር ሁሉ፣ ለዐማራው ኅልውናና ምንነት መቀጠል መቆምና መቆርቆር አለበት ብለን እናምናለን።

ይህም በመሆኑ፣ የዐማራውን ኅልውና አጽንተን፣ ኢትዮጵያነትን ለመታደግ ሳንሰለች፣ የአንድነት ጥሪ ማቅረብ ከሥራዎቻችን ሁሉ ቀዳሚውን ቦታ የሚይዝ ነው። ለዚህ ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ ያላችሁ ወገኖች መልሳችሁን moreshsecretary@gmail.com  እንድታሳውቁን በአክብሮት እንጠይቃለን።

የዚህ ጥያቄአችን መሠረት የፉክክር ቤት የሚፈርስ እንጂ፣ የሚገነባ አለመሆንን ስለምንገነዘብ ነው። ስለሆነም የዐማራው ልጆች በተናጠል የሚያደርጉት ጉዞ፣ ከመመካከርና ከመወያየት ወጥቶ፣ ወደ ፉክክር ከገባ፣ ለዐማራው ጥፋት ተጠያቂው ወያኔና መሰሎቹ ብቻ ሳይሆኑ፣ እኛም የአንበሣውን ድርሻ የምንወስድ መሆናችንን ልንገነዘበው ይገባል።

ዐማራን ከፈፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

በዐማራዊ ማንነትና ኅብረት ኢትዮጵያዊነት ይለመልማል!