August 18, 2016
Welkeit map
ዳንኤል ብርሃኔና አብራሃ ደስታ በወልቃይት ጉዳይ ላይ የጻፉትን የወደቀ ሎጅክ በተመለከተ ትንሽ ነገር ለማለት ፈለኩ
የወደቀው ሎጅክ እንዲህ ይላል ።
“ወልቃት ድሮ ጎንደር ክፍለሀገር ነበርና ይመለስ ከተባለ፣ ዳሎል (ሰሜን አፋር) ትግራይ ክፍለሀገር ስለነበረ መመለስ ሊኖርበት ነው” ይላል ,,,
ስለማንኛውም ህዝብ ፍላጎት መወሰን ያለበት ራሱ የጉዳዩ ባለቤት ህዝብ ብቻ ነው ። የአፋር ህዝብ ከትግሬ ጋ መሆን ከፍለገ መብቱ ነው በህዝቡ ፍላጎት መሰረት ወደ ትግራይ መጨመር ይችላል ። ነገር ግን የአፋር ህዝብ ወደ ትግራይ ልካተት የሚል ጥያቄ ባላነሳበት ሁኔታ ዳሎልን ወደ ትግራይ መጨመር አይቻልም ። የትግራይ ህዝብ ስለ አፋር ህዝብ የመወሰን መብትና ስልጣን የለውምና ። በሌላ በኩል የወልቃይት ህዝብ “አማራ ነኝ ከትግራይ ጋ መሆን አልፈልግም” ብሏል መፍትሄውም ወደ ነበረበት ጎንደር መመለስና እስካሁን ለጠፋው የሰው ህይወት፣ ለተዘረፈው መሬት፣ ሃብት ንብረትና ካሳ መክፈል ብቻ ነው ። ብዙ ባቅማማችሁ ቁጥር ለዘላቂ ትውልድ እዳ እያስቀመጣችሁ መሆኑን አትርሱ ። ገና ያልተከፈ የአምስት ሚሊዮን አማራ ዕዳ አለባችሁ ።
በነገራችን ላይ አብረሃ ደስታ በአንድ ወቅት ዳንኤል ብርሃኔ ወልቃይት ውስጥ ሰፊ መሬት እንደተሰጠው የሚገልጽ መረጃ ፓስት አድርጎ ነበር ። ዳንኤል ብርሃኔ በወልቃይት ጉዳይ ላይ ድርቅና ያበዛው ከደሃ ወገኔ የወረሳትን መሬት ለመጠበቅ መሆኑ ግልጽ ነው ።
ዘመን ተገላብጦ የአብራሃ ደስታና የዳንኤል ብርሃኔ አቋም አንድ አይነት የሆነበት ወቅት ላይ መድረሳችን ይገርማል ።
Ewnet Le Netsanet
ምንጭ _ ሳተናው