img002

 

ወይ-ያኔ! ወይ- ያኔ!

 

 ወራቱ እያጠረ፣ ጊዜው እየመሸ፣
መካሪ ጠፋ እንዴ፤
ተው አንቀላለድ በጦር በጎራዴ።
ወይ-ያኔ! ወይ- ያኔ!
የነፃ አውጩ ጓዴን ምኑ ሰለበብኝ፤
የቀብሩን ማንቆሮ
ባአንገቱ ጠምጥሞ አየሁኝ።
ወያኔን ምከሩ በክረምት አይመካ፤
ተው ጭጭ አትበሉ፣ መሰንጠቁ አይቀርም
ጸሐይ የውጣ ለት፣ የዋልድባ ዋልካ።
ምነው ዝም አላችሁ የህዋት ምስለኔ፤
ክረምት ያለፈ ለት፣ እናንተን አያርገኝ
ወይ-ያኔ! ወይ- ያኔ!
እነማን ነበሩ ሊቀ ሊቅውንቱ፤
ያኔ በውጭ አማካሮች የተባሉት አንቱ።
እስኪ ተናገሩ፣ እነማን ነበሩ፣
ህዋት ሲመሰረት፤
በሽምቅ ሲማማል፣ ኢትዮጵያን ለማጥፋት!
አረ ጉድ ዘንድሮም ያነ አዲስ አበቤ ለንብረቱ ፈርቶ፤
ጭጭ አለ በአድባባይ፣ አንገቱንም ደፍቶ።
ሽማግሌን ጠፋ ከአድዋ እስከ ሐረር፤
እንዲት ያገሪ ልጅ በካድሪወች ጥይት፣
እንደ ውንጮ ቆሉ፣ በመታመስ ይረር?

እሪ ያገር ያለህ፣
እሪ የህግ ያለህ፣
በክረምቱ ወራት ቤቷን አፈራርሶ፣
ጋቢ እንኳን ሳይሰጣት፣
በዚያ አዲስ አበባ፣ ህዋት በገዛበት፤
ልጇን ብቻ ሳይሆን፣ እናትን ጅብ በላት።
ምነው ዝም አላችሁ
የህዋት ምስለኔ፤
ክረምት ያለፈ ለት
እናንተን አያርገኝ
ወይ-ያኔ፣ ወይ- ያኔ!
የነፃ አውጭወች ጓዶች፣
ያነ ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ተናገረው፣
“… አባቴ በአለንጋ ገርፎአችኋል፥
እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ፤” (1 ነግሥት 12:11)
እንዳለው አትሁኑ፣
ተው ተመክሩ ጊዜ ሳለላችሁ።
ወራቱ እያጠረ፣ ጸሐዩ እየገባ፣
በዚያ በጉራንባ ፣
መካሪ ጠፋ እንዴ፤
ተው አንቀላለድ በጦር በጎራዴ።

© ለምለም ፀጋው፣ August 21 2016
የኢትዮጵያን ሕዝብ ድምጽ ለማፈን በጠመንጃም ሆነ በዱላ እየደበደቡ፣ ለሥርና ቤተሰቦቻቸውን ሁሉ
ለርሃብ ለሚዳርጉ ሁሉ ተው አቁሙ፣ ተመከሩ፣ እግዚአብሔርንም ፍሩ ጊዜ ሳለላችሁ ለማለት ተጻፈ።

Leave a Reply