The “x” symbol is used by in protests against the Ethiopian government attempts to reallocate land A crowd-funding campaign has raised more than $40,000 (£30,000) to help Ethiopia’s Olympic marathon silver medallist Feyisa Lilesa seek asylum. EPA
አትሌት ፈይሳ ሊሌሳ “የኢትዮጵያ ጀግና ነው!” ሲል የወያኔው አፈቀላጤ ጌታቸው ረዳ ለአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ተናገረ። በማራቶን ፍጻሜ ላይ እጆቹን መማጣመር ተቃውሞውን በማሰማቱ ምክንያት ሊፈራ አይገባውም ሲል ጌታቸው ረዳ ለCNN ሲ.ኤን.ኤን. ቴሌቭዥን የገለጸ ሲሆን አትሌቱ ወደ አኢትዮጵያ ቢመለስ ምንም እንዳማይሆን ቃል እገባለሁ። እንዲያውም የጀግና አቀባበል ይጠብቀዋል ብሏል።
ይህ በንዲህ ላይ እንዳለ የእንግሊዙ ዘኢንዲፔንደንት ጋዜጣ በዛሬው እትሙ በአቶ ጌታቸው ረዳ ቁጥጥር ስር ያለው ብሄራዊ ቴሌቭዥ አትሌት ፈይሳ ሊሌሳ የማራቶን ውድድሩን ሲጨርስ እንዳይታይ ማድረጉን አስነብቧል። የወያኔ ቴሌቭዥን በዜና እወጃው የዚህን ማራቶን ፍጻሜ ሲያሳይ አንደኛ የወጣውን የኬንያ አትሌት ኢሉዲ ኪፕችጌ ምስል ካሳየ በኋላ ቀጥታ አራተኛ የወጣውን ኤርትራዊ አትሌት ግርማይ ገብረስላሴን ነበር ለህዝብ ያሳየው።
Independent ዜናን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።
አቶ ጌታቸው ይህንን ከማለታቸው በፊት የኦህዴድ አሽክሮቻቸው አትሌት ፈይሳ ሊሌሳ ጸረ-ሰላም እና ሽብርተኛ ነው ሲሉ መክሰሳቸውን ድረ-ገጻቸው ላይ አስነብበውናል። የአለም ትኩረት የሳበው የአትሌቱ ጀግንነት ባያሳስባቸው ነበር የሚደንቀው።
በሰላማዊ መንገድ የሚቃወሙትን ከሺህ በላይ ያስገደሉት ጌታቸው ረዳ አትሌት ፈይሳ ሊሌሳ ቢመለስ በእርግጥ ያጠፉታል።
አትሌት ፈይሳ ሊሌሳ በትላንትናው እለት ያደረገው ታሪካዊ ክንውን በአለም ዙርያ መነጋገርያ ከመሆኑም አልፎ ታፍኖ የነበረውን የህወሃት የዘር ማጥፋት ወንጀል በአለም መገናኛ ብዙሃን እንዲጋለጥ አድርጓል።
BBC ማምሻውን ሰለ ጀግናው አንድ አዲስ ዘገባ ይዟል። በሰአታት 40 ሺህ ዶላር በላይ አትሌት ፈይሳ ሊሌሳ ተሰበሰበ የሚለው የ BBC ዘገባ የወያኔን ሰብአዊ መብት ረገጣ በሰፊው ዘርዝሮታል። ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።