ባህር ዳር ከተማ የቤት ውስጥ አመፁን እና የስራ ማቆም አድማውን በተሳካ ሁኔታ ለሁለተኛ ቀን እያስኬደችው ነው።ዛሬ ይሄን የስራ ማቆም አድማ ተላልፎ የተገኘ አንዳ ባጃጅን ወርውረው አባይ ወንዝ ውስጥ ገፍተው ጨምረውታል ።በባህርዳርና አካባቢው ህዝብ የቤት ውስጥ አመፅና የስራ ማቆም አድማ ግራ የተጋባውና የጨነቀው የክልሉ መንግስት በአማራ FM ጣቢያ ” ከቤት ውስጥ ውጡ ። ወደ ስራችሁም ግቡ ካለበለዚያ ትቀጣላችሁ! ” እያለ በተደጋጋሚ በመጮህ ላይ ይገኛል።