(ኢ.ኤም.ኤፍ) ከሁለት ቀና በፊት የአማራ እና የኦሮሞ ህዝብን  እየተሳደበች ቪዲዮ በመነሳት፤ ራሷን ለህዝብ ይፋ ያደረገችው ወጣት የትግራይ ተወላጅ፤ ከስራ መባረሯን አምናለች። እንድትባረር ያደረጓትን “ቅናተኞች” መሆናቸውን ነው የገለጸችው። በሌላ በኩል ደግሞ አሁን በወር 15 ሺህ ዶላር እየተከፈላት አዲስ ስራ እንደምትጀምር፤ ትራክ የምትገዛ መሆኗንም አብራርታለች። ከአትላንታ እና ከቴክሳስ መጥተው ሊገድሏት ያሰቡ ሰዎች ቢኖሩም፤ እንደማትፈራ ነው በመጨረሻ የተናገረችው። “እንኳንስ ሰው፤ ጅብ አልፈራም” በማለት በልጅነቷ ጅብ በድንጋይ ማባረሯን ጭምር ትነግረናለች።

ንግግሯን እየሰማን፤ ግዜ ወስደን በጽሁፍ ያቀረብንላቹህ ብዙ ቁም ነገር ይኖረዋል በሚል ሳይሆን፤ ሰው በጭንቀት ውስጥ ሲሆን ምን ያህል ሊዋሽ እንደሚችል ለማሳየት ጭምር ነው። አንዳንድ ንግግሯ ያስቃል። አንዳንድ ንግግሯ ደግሞ ህወሃት ያፈራቸው ወጣቶች የአስተሳሰብ ደረጃቸው ምን ያህል ዝቅ ማለቱን እናይበታለን። ከሚያስቀው ውሸቷ እንጀምር። “የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ሴት ልጅ ነኝ የመንግስት ስራ በአሜሪካ ውስጥ ያለኝ።” ትላለች። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን፤ ለዚያም በትላልቅ ሙያ ለአሜሪካ መንግስት የሚሰሩ መኖራቸውን አታውቅም ወይም አእምሮዋ ተነክቷል።

በመቀጠል ከስራ እንድትወጣ የተደረገችው፤ ትግሬ በመሆኗና ሰዎች ስለቀኑባት መሆኑን ትገልጻለች። ሁሉንም ዝርዝር ዘና ብለው በማንበብ፤ የአንዳንድ ሰው አስተሳሰብ ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ይታዘቡ።

መልካም ንባብ።

ከዚህ ቀጥሎ ያለው ንግግር ሄለን ሃይሉ የተባለችው የህወሃት ደጋፊ ወይም አባል የተናገረችው ነው፡ “ እናንተ እዚህ ሰላሳ አርባ አመት አድርጋቹህ ያላገኛችሁትን ስራ ስላገኘሁኝ ቀንታችሁ የነበረኝን ስራ አሳጥታችሁኛል።  እና ልነግራቹህ ብዬ ነው፤ Moving truck ገዝቼ የራሴ አለቃ ልሆን ነው። ልንገራቹህ አሁን ሙቪንግ ትራክ ልገዛ ነበር። ያን ያህል ነው ገንዘብ ያለኝ። በዚያ ላይ ብር ስላለኝ አግዛችኋለሁ። ላሁኑ ግን ዝም እላለሁ። ካሁን በኋላ ፕሮፌሽናል የሆነ የጭንቅላት ስራ ነው የምሰራው።” ካለች በኋላ፤ የተዘበራረቁ ሃሳቦችን መናገር ቀጠለች።

ብዙ ሰው ደወለልኝ። “ስራ ተባረርሽ” ብለው። ዛሬ ይሄን ስራ ካጣሁ፤ ነገ ሌላ ስራ…  እንደውም ነገ ስራ አግኝቻለሁ። ከሱ የተሻለ ስራ በወር 15ሺህ ዶላር የሚከፍል እየተነጋገርኩ ነው። እንደውም ስራውን ልተወው እያሰብኩ ነው። ከአሜሪካ ወጥቼ በወር 15ቪ የሚከፈለው ስራ ልጀምር ነኝ።

ግን እንደናንተ እቃ አጣቢ ስላልሆንኩ፣ እንደናንተ ሽንት ቤት ስላልጠረኩ አመማቹህ። ቀንታቹህ፤ በስራዬ ላይ ችልግር ልትፈጥሩ እንደሞከራቹህ አውቃለሁ። በዚያ ላይ ተሳደበች ነው የሚሉት። እነሱ እንድከሰስ ያደረጉ ሰዎች፤ መረጃ ሰብስቤ በህግ እጠይቃቸዋለሁ።

እንኳን የሰው ስራ የሰው ህይወት እያጣን ነው። ስራ ስላሳጣችሁኝ አመሰግናለሁ።

በጣም አሳቃችሁኝ። ገርሞኝ አሳቀኝ። እኔ እኮ ስራ አጥቼ አልሞትም። ወጣት ነኝ፤ እውቀት ያለኝ ሰው ነኝ። እንደዛ ያደረጋችሁት አውቃችኋለሁ። በዚያ ላይ ደግሞ አሁንም ትግሬ ነኝ። የኔ ጥያቄ ግን… ሰደበችኝ አላቹህ?

የነሱ ሰዎች በስራ ላይ እያለሁ እየደወሉ አስቸገሩኝ። በስራ ላይ እያለሁኝ እንደዛ ማድረግ አልነበረብኝም። ተሳስቻለሁ። አሁንም ትግሬ በመሆኔ እኮራለሁ። ስራ ካባረሩኝ፤ ማንነቴ አይቀየርም። ብዙ ዘመዶቼን አጥቻለሁ። ብዙዎቹ እያስፈራሩኝ ነው። እናንተ የማታውቁት ግን ቪዲዮ ከማድረጌ በፊት፤ ሲያስፈራሩኝ ነበር።

የኔን ቤተሰቦች ሊገሏቸው ይችላሉ። እኛ ደግሞ “የሚበጠብጡንን እናስወግዳለን” ነው ያልኩት። ሰላም ስለፈለኩ በጣም ይቅርታ። እናንተ ሁከት ትፈልጋላቹህ። እኔ ኢትዮጵያን ወክዬ የመንግስት ስራ ስሰራ መኩራት ሲገባቹህ፤ የቡድን ስራ ሰርታቹህ… ይቅርታ እንደውም የቡዳ ስራ ነው የሰራችሁት። አሁን ከስራ ስለተባረርኩ የምሞት መስሏቹህ ነው፤ ምንም አልሆንም።

አሁን በጣም ሃብታም ልሆን ነኝ። እግዚአብሔር ለኔ የሰጠውን ለናንተ እንዲሰጣቹህ እመኛለሁ። እኔ የምላቹህ ደግሞ፤ ዩኒፎርም አድርጌ መናገሬ ነው ያጠፋሁት። ግን ስራዬን እራሴን እንደለቀቅኩ ነው የምቆጥረው። ግን ተናድጄ ከባህሪዬ ወጥቼ እንደናገር አድርገውኝ ከስራ ተባርሬያለሁ። ቢሆንም እንቅልፍም አላጣሁም። እንደሃብታም ነው የምበላው። የኔን መኪና ብታዩ ምን ትላላቹህ? የኦባማ መኪና ነው ትላላቹህ።

አሁንም አለቃዬ ጋር ማን እንደሄደ አውቃለሁ። አብረውኝ ሲስቁ የነበሩ ጓደኞቼ ናቸው ሄደው የተናገሩት። አሁን ብወድቅም የተሻለ ደረጃ እደርሳለሁ። የተሻለ ደሞዝ ያለው ስራ አገኛለሁ። ግን በዩኒፎርም ሳይሆን፤ በእረፍት ግዜዬ ቀስ ብዬ እነግራችኋለሁ። እንደኔ ያላቹህ ትግሬዎች ደግሞ እናንተም መነሳት አለባቹህ። በኔ ላይ ያደረጉት ነገር ቀላል አይደለም። መታሰር ግን አልታሰርኩም። ሰላም የምትፈልጉ ከሆነ፤ እነዚህ ሰላም የማይፈልጉ ሰዎችን መቃወም አለብን።

እንደኔ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ የደረሰን፤ ጀግና እንደኔ አይነት ሰው ሲያዩ ቀኑብኝ።

እናንተ ደግሞ የኔ ጓደኞቼ መስላቹህ፤ ወደስራ በመሄድ እንድባረር አደረጋቹህ።

በዚያ ላይ ደግሞ ኦሮሞ እና አማራ ብያለሁ። እኔ በአጠቃላይ ማለቴ አልነበረም። ስንት አማራ አለ ከኛ ጋር የሆነ፤ ስንት ኦሮሞ አለ ከኛ ጋር ያለ። ሁላችሁ አማሮች እና ኦሮሞ ማለቴ አልነበረም። እነዚህ ሰላም የማይፈልጉትን ማለቴ ነበር። ትግሬዎችም እኮ አሉ፤ ወያኔን የማይወዱ አሉ። አሁን ፈርቼ ሳይሆን፤ ቁጭ ብዬ ነው የዋልኩት። ትግሬዎችም አሉ ሰላም የማይፈልጉ። አማራ እና ኦሮሞ ላልኩት፤ ጋምቤላዎችም ይቅርታ ለማለት ነው። ለማለት የፈለኩት፤ ኢትዮጵያ እንዳታድግ ለፈለጉት ነው ማስተላለፍ የፈለኩት። አሁን እኔ ፈርቼ ሳይሆን ወይም ስራ ስለተባረርኩ ሳይሆን፤ የምናገር የነበርኩት ሰላም የማይፈልጉትን ማለቴ ነበር።

helenየኔ አመለካከት ሰላም የማይፈልግ አማራ እና ኦሮሞ ነው የተናገርኩት። ኢትዮጵያዊ ለኢትዮጵያ ክፉ እንዲደርሰው የሚያደርጉ ሰዎች ይኖራሉ ብዬ ግን አልገመትኩም ነበር። አሁን ይሄን ስራ ስላጣሁት ነገ የተሻለ ስራ ነው የማገኘው። በዚያ ላይ እናንተ ወገኖቼ ከረዳችሁኝ ቢዝነስ ልከፍት ነው። አገሬ መግባት ነው የምፈልገው። ለሁላችሁም መልካም በአል።

ሰው ያገኘውን ስራ ለማሳጣት አትሞክሩ። የዚህ አገር ሰዎች What goes around comes around ይላሉ። በተለይ እንደኔ አይነት ማንም ሊያገኝ የማይችለውን የመንግስት ስራ ስለሰራሁ ቀናችሁብኝ።

ሌሎች ትግሬዎች መሳደብ ከፈለጋቹህ እንደኔ ከነዩኒፎርማቹህ አታድርጉ። ከስራ መጥታቹህ፤ የስራ ልብሳችሁን ቀይራቹህ የፈለጋችሁትን ማድረግ ይቻላል።

አሁን ሌላ ስራ ቁጭ ብሎ እየጠበቀኝ ነው። የት እንደሆነ አልነግራቹህም። እዛ ደሞ እንደቡዳ ቁጭ ብላቹህ እንዳትጠብቁኝ ማለት ነው። እዚህ አገር በህግ ከተደረገ የህግ አገር ነው። ደግሞ እናንተም እንገልሻለን ያላችሁትን እለቀዋለሁ። ከዚያ አለም ይፈርዳል።

የሚመስላችሁን ተናገሩ። እኔን እና ቤተሰቦቼን የሚገድል ደግሞ፤ እኔም ራሴን እየጠበኩ ነው። ቤተሰቦቼም ከድሮም እራሳቸውን ይጠብቃሉ። እንደናንተው እህቶች፣ ወንድሞች፣ አያት አለኝ።፡ትልቅ ቤተሰብ አለን። አንድ ጀግና ፋሚሊ አለን። ግን ስለነሱ አልነግራችሁም። ፈሪ በደማችን የለም። ፈሪ ሆነን አናውቅም። አሁን ግን… በህይወቴ ብዙ የሚያስቅ ነገር ነው ያየሁት።

helen2እኔ እኮ አሜሪካ ከገባሁ ዘጠኝ አመቴ ነው። እናንተ እዚህ አርባ እና ሃምሳ አመት ቆይታቹህ እኔ የደረስኩበት ስላልደረሳቹህ ቀናቹህ። የኔን ቀጣይ ኑሮ እግዚአብሔር ያውቃል። ከስራ ብወጣም በፊትም ትግሬ ነኝ፤ አሁንም ትግሬ ነኝ። እኔ ትግሬ ስለሆንኩል ከመንግስት ጋር ጥላቻ ያላቹህ በኔ ላይ መጣቹህ። እናንተ ስትሰድቡን ከስራ አትባረሩም። እኔ ግን ስናገር… ግዴለም እያንዳንዳችሁን እናውቃችኋለን።

ከቴክሳስ እና ከአትላንታ መጥተን እንገድልሻለን ያሉኝ አሉ። ካሊፎርንያም አሉ። ምን ትርጉም አለው ሰው መግደል? ሰው ስላለፈለት ቀንተው ነው። በፊኒክስ ሆነ በአሪዞና ማን አለ የመንግስት ስራ የሚሰራ? እስኪ የመንግስት ስራ የሚሰራ ካለ ንገሩኝ… የለም። ከስራዬ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም። አሁን ማናጀሮቼ የሚሉኝ “ስራ ላይ ሆኜ ስላደረኩት ነው።”

እኔ ለሰው ክፉ አላስብም። እናንተም ክፉ አታስቡ። የማውቃቸው ሰዎች ናቸው እንደዛ ያደረጉት። የማሳያቹህ ግን ሌላ የተሻለ እንደማገኝ ቃል እየገባሁላቹህ ነው። ትንሽ ግዜ ስጡኝ። ብር ካለ በሰማይ ገንዘብ አለ” ከታገስክ ህልም ክለህ ይሳካል። I have a dream.  I am still happy… በሚዲያ ላይ ከስራ ተባረረች ያላችሁ። ይሄ የሰው አገር ነውና እግዜር በሰጣቸው ይስሩ። ኦነግም ይሁን ጋምቤላም ይሁን ሰርተው ይለወጡ። አሁን እናንተ ያደረጋችሁት በናንተ ቢመጣ አስቡት እስኪ።

ካልሰራህ ገንዘብ የለም። ገንዘብ ከሌለ ቤተሰብህን አትረዳም ማለት ነው። አይበላም፤ አያበላም። ለሰው ክፉ አታስቡ። እናንተ ማሰብ ያለባቹህ… ሰው ስለቀናብኝ ከስራ ስባረር፤ የቤት ኪራይ እንዴት ነው የምከፍለው? መኪና በክሬዲት እንዴት ይከፈላል? ቤተሰብስ እንዴት ይረዳል? እዚያ በአንድ ሰው የሚተማመን አስር ኢትዮጵያዊ ካለ፤ በረሃብ ሞተ ማለት ነው። እኔ ግን እንደአህያ እሰራለሁ፤ ጉልበት አለኝ። ቢሆንም እኔ ከስራ ብባረርም ባልባረርም፤ ሌላ ስራ ባገኝም አልቀየርም።

እናንተም በናታቹህ የማትወዱት ፓርቲ ስላልደገፈ በስራቸው አትምጡባቸው ነው… የኔ መልእክት። ከዚህ በኋላ ነይ ነይ የሚለኝ ብዙ ነው። ሶሻል ሚዲያም አያስፈልግም። እንገልሻለን ላላችሁት፤ ሊገደል ቆሞ የሚጠብቅ ሰው የለም።

እኔን የሚሰድብ ስንት አለ? ትግሬን የሚሰድብ ስንት አለ? አንድም ትግሬ ግን ወደ ስራቹህ ቦታ ሄዶ፤ እኔም ሆንኩ ሌላው ትግሬ ወደስራቹህ ሄደን ጸብ መፍጠር አላቃተንም። ግን እንደዚያ አይነት ባህሪ የለንም። ለዚያ ነው እንጂ የት እንደምትሰሩ፣ የት እንደምታድሩ፤ የት እንደምትኖሩ እናውቃለን። እነማን እንደሆናቹሁ እናውቃለን። ግን የጃችሁን ይስጣቹህ። ለምታስፈራሩኝ አልፈራም። ለሊትና ቀን እንቀሳቀሳለሁ። ፈርቼ አላውቅም። የሚገርማቹሁ የአያቴ ፍየሎች፤ ለሊት ጅቦች ሊበሉብን ሲመጡ… እኔና አያቴ ለሊት ተነስተን ፤ ሌላም አልነበረንም በድንጋይ ከጅቦች ጋር ስንጣላ እናድር ነበር። ውሾቹን አስነስተን ከጅቦች ስናጣላ እናድራለን። አያቴን መንግስተ ሰማያት ያድርሳት። ህጻን ሆኜ ጅብ ያልፈራሁ፤ ለምን ሰው እፈራለሁ። አልፈራም። ከአትላንታ እና ከቴክሳስ መጥታቹህ ልትገሉኝ የምትፈልጉ እኔ ምንም አልፈራም እንዳልኳቹህ።

አትጥፉኣ! ርሑስ አውዳመት! እንኳዕ አብጻህኩ! አብጉነይ ኽኑ። ገና ዒዩ። አትፍርዑ!

ለዚህ ሁሉ ውዝግብ ያበቃት ቪዲዮ ተቀንጭቦ ከዚህ በታች ቀርቧል

 

Leave a Reply