ከመሳፍንት ባዘዘው

ኮለኔል ደመቀ ዘውዱን ከጎንደር እስር ቤት አፍኖ የመውሰዱ የህወሓት ሙከራ በእስር ቤቱ ፖሊሶች፣ በእስረኞች እና በጎንደር ህዝብ ነቅቶ ጥበቃ ሳይሳካ ቀርቷል ። በተለይ የጎንደር ማረሚያ ቤት ታራሚዎች በታላቅ ቁጣ ነበር ለድርጊቱ ምላሽ የሰጡት ። ድርጊታቸው የተነቃባቸው የህወሓት ፖሊሶች “እኛ የመጣነው ደሞዝ ለመክፈል ነው” በማለት ለማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች መልስ ሲሰጡ ነበር ። የማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች “ደሞዝ ከዚህ አይከፈልም ” በማለት አካባቢውን ለቀው እንዲሄዱ አስገድደዋቸዋል ። ህዝቡም በብዛት ወደ አካባቢው በመሄድ ለኮሎኔል ደመቀ ያለውን አጋርነት አሳይቷል። የታጠቁ አማሮች አሁንም ድረስ አካባቢዉን በቅርብ ርቀት በጥንቃቄ እዬጠበቁ ነው ተብሏል ።

ፍኖተ ሰላም

ፍኖተ ሰላም

ጎንደር ዛሬ ሌላ በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ አድርጋ ውላለች ። አድማው ነገም ይቀጥላል ተብሏል።

የአማራ ተጋድሎ ዛሬ ጎጃም ዳሞት ፍኖተሰላም ላይ ሲንቦገቦግ ውሏል ። ቋሪት ላይ ህዝቡ ከህወሓት መንግስት እራሱን ነፃ አውጥቷል ተብሏል። የፍኖተሰላሙ የአማራ ተጋድሎ ጠንካራ እና አማራዊ አይበገሬነት የታዬበት ነው። አካባቢው በአሁኑ ሰአት በሕወሓት ጦር ተከቦ እንደሚገኝ ከስፍራው የቤተ አማራ ምንጮች ገልፀውልንል።

አለፋ ጣቁሳ እና ደንቢያ እስከ አሁንም ድረስ መንግሥት አልባ ቀጠናዎች እንደሆኑ ነው። የህወሓት ካብኔ አባላት አካባቢውን ለቀው ከወጡ ሳምንታት ተቆጥሯል ። ህዝቡ ራሱን በራሱ እያስተዳደረ ይገኛል።

ሸዋ ማጀቴ አካባቢ አሁንም አማራዊ ተጋድሎው እንደቀጠለ ነው። የሸዋ አማራ በተደጋጋሚ የወልቃይት አማራነት ጥያቄ በቀጥታ እንደሚመለከተው ጮክ ብሎ እየተናገረ ነው።

ወሎ በተለያዩ ቦታዎች የአማራ ልጆችን አፍኖ የመውሰድ ህወሃታዊ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።ትልልቅ ከተሞች የወታደራዊ ቀጠና እስኪመስሉ ድረስ በሕወሓት ጦር ተወረዋል። ያ መስመር የህወሓት ትልቅ የደም ስር ስለሆነ ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ጥበቃ እዬተደረገለት ነው። ይህን ሁሉ አፈና ተቋቁሞ የወሎ አማራ አሁንም ቢሆን አማራዊ ተጋድሎውን አላቆመም ። በተለያዩ መንገዶች ተቃውሞውን እያሰማ ነው። ከወሎ ምድር ተቆርሶ የተወሰደው የራያ የቆቦ አማራዊ ክፍል ቁጭት ከመቸውም ጊዜ በበለጠ በህዝቡ ዘንድ የጋለበት ሰአት አሁን ነው ተብሏል።

በተያያዘ ዜና አዲስ አበባ ውስጥ ንዋሪ የሆኑ የህወሓት አባላት እና ደጋፊዎች ከፍተኛ የሆነ የሞራል ቀውስ ውስጥ እንደገቡ ምንጮቻችን ገልፀውልናል ። ህዝቡ በማንኛውም ሰአት ግልብጥ ብሎ ወጥቶ በእነሱ ላይ ርምጃ ሊወስድ ይችላል በሚል ፍራቻ የተነሳ የሰቀቀን ኑሮ እዬኖሩ እንዳለ ተገልጿል ። ይህን ፍራቻ መቋቋም ካቃታቸው የህወሓት ልጆች በተለያዩ የትግራይ ከተማዎች ግዜያዊ መጠለያ ካምፕ እዬተዘጋጀላቸው መሆኑን ለመረዳት ችለናል። እስከ አሁን ከጎንደር እና ከባህርዳር ብዛት ያላቸው የህወሓት የቁርጥ ቀን ልጆች ወደ ትግራይ ሄደዋል።

Posted by:

Leave a Reply