ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት            

ሐሙስ ነሐሴ ፲፱ ቀን ፪ሺህ፰  ..              ቅፅ ቁጥር ፳፭

  • ወያኔ አጥፍቶ ለመጥፋት የመጨረሻውን መሰናዶ እያደረገ መሆኑ ግልፅ ሆኗል

Moresh

የትግሬ-ወያኔ ላለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ፣ በተለይም በዐማራው፣ በኦሮሞው፣ በሱማሌው፣ በሐዲያው፣ በአኙዋኩ፣ በኑዌሩ፣ በከፊቾው፣ ወዘተርፈ ላይ የፈጸመው የዘር ፍጅት፣ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ሊፈጸም ቀርቶ ለማሰብ አስቸጋሪ ነው። ግፉ ከገደቡ አልፎ በመትረፍረፉ፣ የዚህ የከፋ የዘር ፍጅት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ሰለባ የሆኑት ነገዶች ተወላጆች፣ በዳያቸው የሆነውን የትግሬ-ወያኔ በቃህ ካሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። ለዚህ ማረጋገጫውም፣ በየአካባቢው በባዶ እጃቸው እስከ አፍንጫው ከታጠቀው ገዳይ ኃይል ፊት በመቆም በተከታታይ የሚያሰሙት የተቃውሞ ድምፅና ሰላማዊ ሰልፍ በግልጽ ያሳያል።

የትግሬ-ወያኔ ትውልድ በምድጃ ዙሪያ ከአያት ቅድመ-አያቶቹ ተግቶት ያደገው የዐማራ ጥላቻ እጅግ የሠፋና ሥር የሰደደ መሆኑ ይታወቃል። ለዚህም ሥር የሰደደ ጥላቻ ዋና ማሳያው፣ ገና የትጥቅ ትግል ሲጀምር፣«የትግራይ ሕዝብ ደመኛ ጠላት ዐማራ ነው!»፣ «ወያኔ ዐማራን ሳያጠፋ አንዳችም እረፍት አይኖረውም!» የሚል »መሪ ሀሳብ» በፕሮግራሙ ነድፎ መንቀሳቀስ የጀመረ መሆኑ ነው። በዚህ ጥላቻ ላይም ተመሥርቶ፣ ዘረኛው አገዛዝ ባለፉት 25 ዓመታት ብቻ  ከ5 ሚሊዮን በላይ ዐማሮችን ከምድረ-ገጽ አጥፍቷል። ሌሎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ዐማሮች ለዘመናት ከኖሩበት አካባቢ ሀብት ንብረታቸውን ነጥቆ በማባረር ለከፍተኛ ችግር ዳርጓቸዋል፤ በቁጥር ከአንድ ሚሊዮን ተኩል የማያንሱትን ዐማሮች ከኢትዮጵያ ምድር አሰድዷል። ይህ በዐማራ ጥላቻ ተወልዶ ያደገና ዐማራን ለማጥፋት የተደራጀ ዘረኛ ቡድን፣ ካለፈው ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ፍትኅ በጠየቁ የዐማራው ተወላጆች ላይ የዘር ፍጅት በመፈጸም ላይ መሆኑን የዓለም የመገናኛ ብዙኃን በሥፋት እየዘገቡት መሆኑ ይታወቃል።

በዚህም መሠረት ከአርባ ዓመታት በላይ የዘር ፍጅት የተፈጸመበት የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ሕዝብ፣ ያነሳው የማንነት ጥያቄ፣ የእኛም ጥያቄ ነው። ወልቃይት ጠገዴ ዐማራ ነው፣ የእነርሱ ድምፅ የእኛምን ነው፣ ብለው በባህር ዳር ከተማ እሑድ ነሐሴ 1 ቀን2008 ዓም በሰላማዊ መንገድ ድምፃቸውን ባሰሙ ንፁሐን ዜጎች ላይ ነፍሰ በላው የአጋዚ ሠራዊት፣ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ስማቸውንና አድራሻቸውን ያገኘውን የ49 (አርባ ዘጠኝ) ሰዎች የስም ዝርዝር ማውጣቱ ይታወሳል። በዚህ መግለጫም ከሐምሌ 5ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ፣ በጎንደር ክፍለ-ሀገር የተለያዩ ቦታዎች በትግሬ-ወያኔ ሰው-በላ ነፍሰ ገዳዮች በተተኮሱ ጥይቶች በጠራራ ፀሐይ ከተገደሉት እና ከቆሰሉት ዐማሮች መካከል፣ የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት መረጃ አሰባሳቢ ቡድን ለማግኘት የቻለውን ዝርዝር በሚከተሉት ሠንጠረዦች አቅርቧል።

ሠንጠረዥ 1፦ የትግሬ-ወያኔ ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓም ጀምሮ በጎንደር ክፍለ-ሀገር እና በደብረ ማርቆስ ከተማ (ጎጃም) የገደላቸው ወገኖቻችን ዝርዝሩ ከፊል ዝርዝር

ተ.ቁ ስም የተገደሉበት አካባቢ ማብራሪያ
1 ዘሪሁን (ሰሎሜ) ገደብየ፣ የገጠር ቀበሌ ልጆች እና ሚስት ያሉት
2 ባየሁ ቀበሌ 10፣ ጎንደር ከተማ ወጣት እና ከቤተሰቦቹ ጋር ይኖር የነበረ
3 በለጡ መሐመድ ቀበሌ 20 (አዘዞ)፣ ጎንደር ከተማ
4 እንጀራ ባየ ቀበሌ 20 (አዘዞ)፣ ጎንደር ከተማ
5 የቻፖራ ወንድም ጎንደር ከተማ የሚታወቀው የወንድሙ ስም ነው
6 ግርማቸው ከተማ አርባ፣ ላይ አርማጭሆ
7 ሊሻን ከበደ አይምባ የገጠር ቀበሌ
8 መሌ አይምባ የገጠር ቀበሌ
9 አዛነው ደሴ ኩርቢ የገጠር ቀበሌ፣ አርማጭሆ ገበሬ
10 አራጋው መለሰ ኩርቢ የገጠር ቀበሌ፣ አርማጭሆ ገበሬ
11 ሰጠኝ አድማሱ ደልጊ ከተማ
12 ታረቀኝ ተሾመ ደልጊ ከተማ
13 ሔኖክ አታሎ ደልጊ ከተማ
14 ደሴ ደረሰ ሻውራ፣ የገጠር ቀበሌ የ53 ዓመት ጎልማሣ፣ ሚስት እና ልጆች ያሉት
15 ግርማቸው ሞገስ ሻውራ፣ የገጠር ቀበሌ ደከማ እናት አለችው
16 ወርቁ ጣቁሳ፣ የገጠር ቀበሌ
17 ማማየ አንጋው ዳንሻ ከተማ ተደብድቦ የሞተ
18 ፈንታ አህመድ ዳንሻ ከተማ
19 ክንፌ ቸኮል በአከር
20 ዜና ደብረ ማርቆስ ቀበሌ 03 ደካማ እናት ያሉት
21 ሲሳይ ታከለ አርማጭሆ
22 ማዕረግ ብርሃን ደብረ ታቦር ከተማ የቤገምድር ኮሌጅ የ2ኛ ዓመት ተማሪ የነበረ፣ ቤተሰቦቹ ታች ጋይንት ደምበጣ ቀበሌ የሚኖሩ
23 መምህር ተስፋየ ብርሃን ቀበሌ 01፣ ደብረ ታቦር ከተማ ቤተሰብ አለው
24 ይበልጣል ደሴ ቀበሌ 01፣ ደብረ ታቦር ከተማ ቤተሰብ አለው፤ የማስተርስ ፕሮግራም የ2ኛ ዓመት ተማሪ

ማሳሰቢያ፤

  1. በወረታ ከተማ የሞቱት ሦስት ሰዎች ብዛት ሲሆን፣ የአንደኛው ሰው ማንነቱ አልተለየም፤ የሁለቱም ስም እስካሁን ለማወቅ አልተቻለም።
  2. በአዲስ ዘመን እና ይፋግ ከተሞች የተገደሉት ሰዎች ሁለት መሆናቸው ታውቋል። ስማቸውን ግን እስካሁን ለማረጋገጥ አልተቻለም።
  3. በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሞቱት ሦስት ሰዎች  መካከል የአንደኛው ሰው በስም ሲታወቅ የቀሩት ገና አልታወቀም።
  4. በአርማጭሆ ወረዳ የተገደሉት 10 (አሥር) ሰዎች እንደሆኑ ታውቋል።

የቆሰሉ ሰዎች፦

ተ.ቁ ስም የቆሰለበት አካባቢ ማብራሪያ
1 ሀብቴ ዓለሙ ሻውራ፣ የገጠር ቀበሌ በጸና ታምሞ ለከፍተኛ ሕክምና ወደ አዲስ አበባ ሄዶ እንዲታከም ተብሏል። ሆኖም ጭንቅላቱ በጥይት ስለተመታ የመትረፍ እንድል እንደሌለው ተገልጣል።
2 ይደነቅ ቀበሌ 20 (አዘዞ)፣ ጎንደር ከተማ
3 አይሸሽም ወርቄ ቀበሌ 20 (አዘዞ)፣ ጎንደር ከተማ
4 ምናለ ቀበሌ 20 (አዘዞ)፣ ጎንደር ከተማ
5 ጌታቸው ሞላ ቀበሌ 18፣ ጎንደር ከተማ

ይህ ሕዝባዊ እንቢተኝነት ወያኔ የቆመበትን የሥልጣን መሠረት በማናጋቱ፣ የአገዛዙ ሥርዓት ከመጥፋቱ በፊት ጠላቴ ነው ብሎ በፈረጀው የዐማራው ነገድ ላይ የመጨረሻውን የጥፋት በትር ለማሣረፍ እየተንቀሣቀሰ ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ የደረሰ እና በተግባርም በግልፅ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ሆኗል።  ለዚህ ተግባሩ ማሳያ ሆነው ከሚጠቀሱት ማስረጃዎች መካከለል የሚከተሉት ይገኙበታል።

አንደኛ፦ የአገሪቱን የመከላከያ ተቋሞች ከመሀል ኢትዮጵያ ነቅሎ ወደ ትግራይ ወስዷል፤

ሁለተኛ፦ የአገሪቱን የመረጃ ማዕከል ከአዲስ አበባ ነቅሎ ትግራይ አስገብቷል፤

ሦስተኛ፦ ለምትገነጠለው ትግራይ የኢኮኖሚ መሠረት የሆኑ ፋብሪካዎችን፣ ኢንዱስትሪዎችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ኮሌጆችን፣ መንገዶችን፣ ከተሞችን፣ መገናኛ ተቋሞችን በኢትዮጵያ ሕዝብ አንጡራ ሀብት ገንብቷል፤

አራተኛ፥ ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓም ጀምሮ በጎንደር፣ በጎጃም፣ በወሎ እና በሸዋ እንደሰደድ እሳት የተቀጣጠለው ሕዝባዊ እንቢተኝነት ሕዝቡን በመሰለል ሲያስሩና ሲያስገድሉ በነበሩት በወያኔ አባሎች ላይ በማነጣጠሩ፣ ሽብር ውስጥ የገባው ዘረኛው የትግሬ-ወያኔ ቡድን በጎንደርና በባሕርዳር ይኖሩ የነበሩ የሥርዓቱ አቀንቃኝ የሆኑትን ትግሬዎች ለይቶ በሌሊት ወደ አዲስ አበባና መቀሌ እንዲሄዱ አድርጓል።

አምስተኛ፦ በጎንደርና በጎጃም በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆችን ነጥሎ ወደ ትግራይ እንዲሄዱ አድርጓል።

እነዚህ ድርጊቶች ወያኔ በጎንደርና በጎጃም ነዋሪ በሆነው የዐማራው ነገድ ላይ ጅምላ ጨራሽ የሆነ ፍጅት ለመፈጸም የተዘጋጀ እንደሆነ የሚያመላክቱ ምልክቶች እንደሆኑ ብዙዎች ይስማማሉ። ሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት፣ «ወያኔ ዘሩን በነቂስ ከጎንደር እና ከጎጃም ማስወጣቱ ምን ሊማድረግ አስቦ ነው?» የሚለውን ጥያቄ ለአካባቢው ነዋሪዎች አቅርቦ ነበር። ላቀርብንላቸው ጥያቄዎች የአካባቢው ሰዎች የሰጡን ጠቅለል ያለ መልስ፦ «የትግሬ-ወያኔዎች በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖረውን የዐማራ ነገድ እና ከዐማራው ጋር ተሰባጥረው የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ዘር ጨራሽ በሆኑ ኬሚካሎች እና ባዮሎጂካዊ የሕዝብ መፍጃ ባክቴሪያዎችና ቫይረሶች ለመፍጀት» እንዳቀዱ ድርጊቱ አመላካች እንደሆነ ይስማማሉ። «ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?» ለሚለው ተከታይ ጥያቄ አስተያየት ሰጪዎቹ የሚከተሉን ሊያደርጉ ይችላሉ ብለው እንደሚያስቡ ይገልፃሉ።

1       በውኃ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች እና ጉድጓዶች መርዝ ሊጨምሩ ይችላሉ፤

2       ሕዝብን በገፍ የሚጨርሱ ተዛማች በሽታዎችን ሆን ብለው ሊያራቡ ይችላሉ። ለዚህ እንደማሳያ የሚሰጡት ሰሞኑን በባሕርዳር፣ በደብረታቦር እና በሌሎችም የዐማራ ከተሞች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ከውኃ ጋር በተያያዘ ጤንነቱ የታወከ እንደሆን ይገልጻሉ። አገዛዙም ይህን አጣዳፊ በሽታ«አተት»፣ ማለትም፦ «አጣዳፊ ተቅማጥና ትውክት» ብሎ እንደሚጠራው፣ እውነቱ ግን ይህ ኮሌራ በአገሪቱ በስፋት ሆን ተብሎ እንዲዛመት መደረጉን በቁጭት ያስረዳሉ።

3       ሌላው ሊያደርጉት የሚችሉት፣ ላለፉት 25 ዓመታትም አጥብቀው ሲሠሩበት የኖሩት፣ የወያኔ ትውልድ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ቁንጮ ላይ ካልቆየ፣ አገሪቱን በነገድ ከፍፋሎ እርስ በርሳቸው በማናከስ፣ እነርሱ የአገሪቱን ሀብት ዘርፈው ጠቅለው ትግራይ በመግባት የትግራይን ረፐብሊክ መመሥረት የሚለውን የቆየ ዓላማቸውን ዕውን ማድረግ የሚለው ነው። ለዚህ ዓላማ ተግባራዊነትም የሕገመንግሥቱ አንቀጽ 39 ለዚሁ ተግባር ሲባል የተቀመመ አጥፊ ቅመም እንደሆነ ይታመናል። ይህ አንቀጽ ሆን ተብሎ የተሰነቀረው፣ ወያኔ «ለብሔር/ብሔረሰቦች» ዕኩልነት አስቦና ተጨንቆ ሳይሆን፣ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ቁንጮ ላይ መቆየት ካልቻለ፣ ወያኔ በአገር ክሕደት ተከሳሽ መሆኑን ስለሚያውቅ፣ ከዚህ ማምለጫው ብቸኛ መንገድ ትግራይ ገንጥሎ መሄድ የሚለው በመሆኑ ብቻ ነው። አንቀጹም የተቀመጠው ለዚህ እንጂ፣ ለሌሎቹ አለመሆኑን የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች ያሳያሉ። እነዚያን ቅድመ ሁኔታዎች ባንድ ቀን ጀምበር ማሟላት የሚችለው ወያኔ ብቻ ነው።

4       ወያኔ ከነአጥፊ ኃይሉ ወደ በቀለበት ትግራይ ምድር ተጠቃሎ መግባቱን ሲያረጋግጥ፣ ሌሎች ነገዶች ኃይላቸውን አስተባብረው የጭቃ እሾህ እንዳይሆኑበት፣ በራሳቸው ችግሮች እንዲወጠሩ ማድረግ የሚችል አጥፊ ሥራዎችን ይሠራል። ሊያደርጋቸው ከሚችሉ የጥፋት እርምጃዎች መካከል የኃይል ማመንጫዎችን ማውደም፣ ድልድዮችን ማፈራረስ፣ የመገናኛ አውታሮችን መበጣጠስ፣ የአገሪቱን ሀብት አሟጦ መውሰድ፣ ሕዝብ ይከተላቸዋል ብሎ የሚያስባቸውን ሰዎች በገፍ መግደል፣ የኢኮኖሚ ተቋሞችን መውሰድ የማይችላቸውን ማውደም፣ በታላላቅ ከተሞች በተቀነባበረ ሁኔታ ፈንጂ በማፈንዳት ሕዝብ መጨረስ እና ድርጊቱን «በተቃዋሚ አሸባሪነት» በሚፈርጃቸው ክፍሎች (በተለይም በዐማራው) ላይ ማላከክ፣ ወዘተርፈ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይታሰባል። ይህን ደግሞ ወያኔ አያደርገውም አይባልም። «ውሻን በምን ፈራኸው» ሲሉት በአጥንት እንዳለው፣ በገዛ ወገኖቻቸው ላይ የሐውዜንን ወንጀል የፈጸሙ ሰዎች በሌሎች ነገዶች ላይ አይፈጽሙም ብሎ ለማሰብ ያስቸግራል።

ወያኔ አጥፍቶን ከመጥፋቱ በፊት ተቃዋሚው ኃይል የሚከተሉትን ተግባሮች በተቀናጀ መንገድ መወጣት ቢችል ጥፋቱን ፈጽሞ እንኳን ማስቆም ባይቻል መቀነስ ይቻላል።

  1. ሕዝቡ በቡድን ተደራጅቶ፣ የውኃ ማከማቻ ጋኖችን በፈረቃ በስውር እና በግልጽ መጠበቅ እና ከብክለት መከላከል፤
  2. ሕዝቡ ነቅቶ የትግሬ-ወያኔን የማፍረስ እንቅስቃሴ እንዲገታ የተቀነባበረና ተደጋጋፊ ቅስቀሳ መሥራት፤
  3. በትግሬ-ወያኔን የስለላ መዋቅር ውስጥ ያሉ ሰዎችን ምንነት እና እንቅስቃሴ ነቅቶ መጠበቅ እና ተግባራቸውን በተከታታይ ማጋለጥ፤
  4. የትግሬ-ወያኔን ሕዝብ የማጥፋት ዓላማ በተጠናከረ እና ወጥነት ባለው መልኩ ለዓለም ማኅበረሰብ ሳይሰለቹ ማሳወቅ፤
  5. በፀረ-ወያኔው ጎራ ለጊዜውም ቢሆን፣ የጎንዮሽ መጎሻሸም ትቶ፣ ሙሉ አቅሙን በትግሬ-ወያኔ ላይ በማሳረፍ፣ ኢትዮጵያ እንደ አገር ልትቀጥል የምትችልበትን መንገድ መከተል። የትግሬ-ወያኔ ክፉኛ የሚሞተው ኢትዮጵያውያን በነገድ በመከፋፈላችን ሳይሆን፣ በአንድነት በመቆማችን ስለሆነ፣ ለአንድነቱ የምንችለውን ሁሉ በቀና መንፈስ ማድረግ፤

ከእነዚህ በተጓዳኝ የወያኔን አገዛዝ ዕድሜ ለማራዘም በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ፣ ወያኔ አጥፊ ቡድን ነው ብለን የምናምን የሚከተሉትን ለሦስት ተከታታይ ወሮች ላለማድረግ ለራሳችን ቃል እንግባ።

አንደኛ፦ በኢትዮጵያ ኢየር መንገድ አለመጓጓዝ፣

ሁለተኛ፦ ከኢትዮጵያ የሚመጣውን እንጀራ አለመግዛት፣

ሦስተኛ፦ ወደ አገር ቤት ገንዘብ አለመላክ፣

አራት፦ ከወያኔ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው ከሚጠረጠሩ ሰዎች ጋር ያለንን ማኅበራዊ ግንኙነት ማቋረጥ፣

እነዚህን ካደረግን አገር ቤት አፈሙዝ ተደግኖባቸው ሕዝባዊ እንቢተኝነቱን ለሚያጧጡፉት ወገኖቻችን ከፍተኛ የሞራል ድጋፍ ከማድረጉም በላይ የወያኔን ኢኮኖሚያዊ አቅም ስለሚያዳክምበት፣ አሳሪውና ገዳዩ ኃይል ከሕዝብ ጎን እንዲሰለፍ ያግዛል።

በማጠቃለያም፦ በእነዚህ ወገኖቻችን ስም ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በውጭ በስደት ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ የሚያስተላልፈው ጥብቅ መልዕክት ይኖራል፥ ቢያንስ ከላይ የተጠቀሱትን አራት ተግባሮች ከመስከረም 1 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ  እስከ ኅዳር 30 ቀን2009 ዓም ድረስ ተግባራዊ እንድናደርግ ለራሳችን ቃል እንድንገባ በአክብሮት ይጠይቃል።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃል-ኪዳን ነው!

ድሉ የሠፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው!

ሞት ለትግሬ-ወያኔና ለአጋሮቹ!

ምንጭ          ሳተናው

Leave a Reply