የህዳሴዉ ግድብ ጉብኝት ተሰናከለ ፤

እምቢ ለመብቴ ያለው የጎጃም ገበሬ የደቡብ ክልል ባለሥልጣናትን የህዳሴ ጉብኝት አከሸፉ

ዳንኤል ሽበሺ

★★★★★★★★★★★★★★★

በደቡብ ክልል ካሉ ወረዳዎች፣ ዞኖችና ከክልሉም መዋቅሮች የተሰባሰቡ ባለሥልጣናት በአራት አውቶብስ ተሳፍረው ለጉዞና ለበረሃ የሚሆን ስንቅ በመያዝ የህዳሰውን ግድብ ለመጎበኘት ወደ ግንባታ ሳይት ያቀኑት ሐሙስ (18/12/08) ከሰዓት በፊት ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ተጓዦች ሳይሳካላቸው እምቢ ለመብቴ ባለ የጎጃም ገበሬ ተገደዉ ወደ መጡበት መመለሳቸውን ከተጓዦቹ መካከል አንድ የቀድሞ ወዳጄ ሹክ ብሎኛል፡፡
….ከስልኬ ጥሪ ቀጥሎ ምነው? ምን ገጠማችሁ? ጥያቄዮን ሰነዘርኩ…ከወዲያ ማዶ ባለ ስልጣኑ “አይ ኃጢዓታችን በዛ መሰለኝ ሳናውቅ በከባድ ጦርነት ውስጥ ዘው ብለን ገባንና ማጠፊያው አጠረን …. ፈጣሪ በቸርነቱ ብዛት አዳነን ቀኝ ኀላ ዙረን ተመለስን”

ቀጠለና “ዳኒ! ዋናዎቹን ተው! ህፃናት እኮ ነፍጥ አንግተዉ ወታደሩን በወኔ ይፋለሙታል፡፡ በቃ! መንግሥት የሚባል ነገር በተጓዘንባቸው አከባቢ የለም፡፡ በየደረስንበት አማራ አከባቢዎች ሁሉ የቀድሞ ልሙጡ የኢትዮጵያ ባንዲራ ሲውለበለብ ነው የምታየው : እንዴት አይነት ጀግና ህዝብ ነው መሰለህ ? በቃ! ጎጃምኮ ነፃ ወቷል በማለት ራሱ የደረሰበትን ድምዳሜንና የህዝቡን ጥንካሬ ሲያደንቅ ሰማሁ፡፡

… ተጓዦቹን የደቡብ ባለሥልጣናት የጎጃም ነፍጠኛ እንዴት ቀኝ ኀላ ሊያዞራቸዉ ቻለ? የህዝብ ዘመን በርግጥ መጥቷል ልበል እንጂ !!!

ምንጭ        _       ሳተናው

Leave a Reply