Dr Debretsion Gebre Michael

(ኢ.ኤም.ኤፍ) የህወሃት አባል እና ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር የሆኑት ዶ/ር ደብረጽዮን 30 ሚሊዮን ህዝብ ሊደምሰስ የሚችል የመከላከያ ኃይል እንዳለ በእብሪት ገልጸዋል። በማህበራዊ ድረ-ገጽ ያስተላለፉት ሙሉ ቃል ከዚህ የሚከተለው ነው።

“በአማራ ክልል የተከሰተው ረብሻ ከቀን ወደ ቀን አድማሱን እያሰፋ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ መምጣቱን እያየን ነው። ይህ እየሆነ ባለበት ሁኔታ እንኳን ÷ መንግሥት የማረጋጋት ሥራውን በከፍተኛ ጥንቃቄና ትግስት እያከናወነ ይገኛል።ይህ ትግስታችን ግን እንደ ደካማነት በመቆጠሩ ብጥብጡ እጅግ የከፋ ወደሆነ አቅጣጫ እንዲያመራ አድርጎታል። መከላከያችን አመፆች በሚነሡበት ጊዜ ጉዳዩን በትግስት የመቆጣጠር ግዴታ ያለበት በመሆኑ ነው እንጂ፤ እንኳንስ ለ30 ሚሊዮን ሕዝብ አደለም፤ መላው አፍሪካን ለመደምሰስ አቅም እንዳለው የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ያረጋገጡት ሃቅ ነው። ሆኖም በዚህ ኃያል አቅሙ ሳይኩራራ ነገሮችን በብስለትና በትግስት ሲያከናውን ቆይቷል።የእስካሁኑ ትግስታችን ግን ብዙ ጥፋቶች እንዲካሄዱ በር እየከፈተ በመሄዱ የመከላከያ ኃይላችን በሙሉ ትጥቅ በመሆን ብጥብጡ ወደከፋባቸው አካባቢዎች በመሄድ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ እንዲወስድ በጠቅላይ ሚኒስትራችን ታዟል።

ድል ለመከላከያ ሠራዊታችን!”

በማለት በፌስቡክ ገጻቸው ሃሳባቸውን ገልጸዋል።

Leave a Reply