September 2, 2016

(EMF) ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ “ያለምህረት እርምጃ እንዲወሰድ ትእዛዝ ሰጥቻለሁ” ማለቱን ተከትሎ፤ በአማራ ህዝብ ላይ የጅምላ ግድያ እየተፈጸመ ነው። በተለይም በመተማ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች፤ መታወቂያቸውን እያሳዩና ትግሬነታቸውን እያስመሰከሩ፤ በቀረበላቸው ትላልቅ መኪኖች ተጭነው ወደ ሱዳን እንዲሻገሩ ተደርጓል። በዚህ ሁኔታ የመተማን ከተማ ካጸዱ በኋላ የትግራይ (ህወሃት) እና የሱዳን ወታደሮች ያለምንም ምህረት የአማራውን ህዝብ እየጨፈጨፉት ነው። ከትላንት ጀምሮም በአየር በተደገፈ የጀት እና ሄሊኮፕተሮች በመሆን የጅምላ ግድያ ተፈጽሟል።

ይህ ጭፍጨፋ እንደተጀመረ አንዳንድ የአካባቢው ሰዎች ወደ ጫካ ሄደው የተደበቁ ሲሆን፤ በመተማ የተገኙ ህጻናት፣ አዋቂ፣ ቄስ፣ ወጣት ሳይቀር በጅምላ ተጨፍጭፏል። ከሁለት ቀናት በፊት ዜናው በኢሳት ላይ በቀረበበት ወቅት፤ አንድ የአካባቢው ነዋሪ “ምናልባት ወደ 26 ሰው ሞቷል” ብሎ ነበር። አሁን ግን በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ብሔር ተወላጆች እንደተገደሉ ለማወቅ ተችሏል።
አንዳንድ የውስጥ ሰዎች እንደሚሉት ከሆነ፤ “ህወሃት የአማራን ህዝብ ለማጥፋት፤ ያልተፈቀደ የመርዝ ጋዝ ጭምር ሊጠቀም ስለሚችል ገለልተኛ አካላት ወደ አካባቢው ሄደ ማጣራት አለባቸው” ብለዋል። ይህንንም ጥያቄ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት እና አማራውን የሚወክሉ የብአዴን አባላት ማቅረብ እንዳለባቸው ሃሳብ ቀርቧል።
ይህ በ’ንዲህ እንዳለ፤ ከኢህአዴግ ስብሰባ በኋላ የአማራ ክልል ፕሬዘዳንት እና የብአዴን ሊቀ መንበር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በሚዲያም ሆነ፤ በአካል ታይተው ስለማያውቁ “በህወሃት ታስረዋል።” የሚለው ወሬ እየተዛመተ ሲሆን፤ ከትክክለኛ ምንጭ ማረጋገጥ አልተቻለም።

Leave a Reply