September 5, 2016

ነሐሴ ፳፱ ቀን ፳፻፰ ዓመተ ምህረት

የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በዘገምታ የመቃብር ጉዞውን ጀምሯል። ሕዝቡ በያለበት ትግሉን አጧጡፏል። የውጭ መንግሥታትም ጥቅማቸውን የሚያስጠብቅላቸውን ወገን ለመለየት ጎራ ይዘው እያዳመጡ ነው። በግብግቡ ብዙ ወገናችን እያለቀ ነው። ይህ ሆነ ያ፤ አሁን ባለንበት የፖለቲካ ሀቅ፤ ኳሷ ያለችው በታጋዩ ሕዝብ እጅ ነው።

የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ በመላ ሀገሪቱ መግዛት አቅቶት፤ ሀገራችን ያለ መሪ ልትሆን አንድ ሐሙስ ቀርቷታል። በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል፤ ሕዝቡ ካሁን በኋላ በዚህ ዘረኛ ግንባር ሥር አልኖርም ብሎ አምጿል። ትናንት ኦሮሞዎች ያነሱት የእምቢተኝነት አመጽ፤ የተዳፈነ መስሎ ዓይታይ እንጂ፤ ውስጡ አመቅዞ አርግዟል። ዛሬ በአማራው አሁንስ በዛ! ቆሜ አልታረድም! አጥፊየን ዓይን ዓይኑን እያየሁ ወደ መቃብሬ አልነዳም! ብሎ የሞት ሽረት ትግል ይዟል። የአምባገነኖች መልስ ምን ጊዜም አንድ ነውና፤ ያንኑ መልስ ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር እያገኘን ነው። አሁንም እንደ እስከዛሬው ድረስ በጉልበት የሕዝቡን ጥያቄ ለማፈን እየሞከረ ነው። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አይማርም እንጂ፤ ይህ ሁሉን በጉልበት!” የትም ሀገር አልሠራም። በኛም ሀገር ሊሠራ ችልም። ታጋዩ ሕዝብ ደግሞ፤ ጉልበቱ ከዕለት ዕለት እየጠነከረ ነው። ታዲያ የትግል አቅጣጫ አመልካቹ የሚያመሳየው፤ ሚዛኑ ቀስ በቀስ ወደ ታጋዩ ሕዝብ እያዘነበ መሄዱን ነው። ነገ የታጋዩ ሕዝብ እንጂ፤ የሟቹ የትግሬዎቹ ነፃ አውጪ ግንባር አይደለችም። እናም ወሳኙ ታጋዩ ሕዝብ ነው።

የታጋዩ ሕዝብ ጥያቄ የሀገር ጉዳይ ሆኖ ሳለ፣ የታጋዩ ሕዝብ ጥያቄ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባርን ሥልጣን የሚመለከት ሆኖ ሳለ፣ የታጋዩ ሕዝብ ጥያቄ የሕልውና ጥያቄ ሆኖ ሳለ፣ የታጋዩ ሕዝብ ጥያቄ የዛሬውን እና የነገውን የሀገር ሕልውና ያነሳ ሆኖ ሳለ፤ አንዳንዶች ያለው መንግሥት ይሄን ቢያደርግ ወይንም ያንን ማድረግ አለበት፤ ሽምግልና ነው መፍትሔው ይላሉ። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባርና አጋሮቹ፤ አሁን የሚደረገውን ሕዝባዊ ንቅናቄ፤ አንድም ሕጋዊ አይደለም፣ ሀገር ትበታተናለች፤ ይሉናል። ታጋዩ ሕዝብ በምንም መንገድ ቢሆን፤ በሰላም መንግሥትን መለመን እንጂ፤ በተለይም ትግሬዎችን በሚመለከትምንም ዓይነት የንብረት ጥፋትና ግድያ መፈጸም የለበትም!” አያሉ ይሰብኩናል። በጎን ይህ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የሚያደርገውን ሕዝባዊ ዕልቂት፤ በተለይም አማራን የማጥፋቱን ዘመቻ፤ ሀገር እንዳትፈርስና ሰላምን ለመጠበቅ ነው!” ይሉናል። ምሁራንና ሽማግሌዎች ይሄን መንግሥት ከእስረኞች ይፍታ እስከ ሕዝቡን ያነጋግር እና የሽግግር መንግሥት ያቋቁም ድረስ ሃሳብ አቅርበዋል። ያ ሁሉ ጊዜው አልፏል። አሁን እኮ ባለቤቱ ታጋዩ ሕዝብ እንጂ፤ በሥልጣን ላይ ያለው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አይደለም። ክፍፍሉ እኮ ጠጥሮ ጠንክሮ ፍጹም አይነከስም። ትግሉ ፈንድቷል። ካሁን በኋላ፤ አቤቱታና ድጋፍ ሠጥቶ ሃሳብ ማቅረብ ለታጋዩ ሕዝብ ብቻ ነው።

ለመሆኑ እስከዛሬ ድረስ፤ የሕዝብ ንብረት ተጋፎ ወደ ጥቂት ትግሬዎች እጅ ሲገባና ሕዝቡ በየቦታው ሲታረድ፤ እኒህ አሁን ጥፋት አይድረስ ባዮች የት ነበሩ። ይህ አሁን በታጋዩ ሕዝብ በኩል በመድረስ ላይ ያለው ጥፋት እኮ፤ ታሪካዊ ሂደቱ ግድ ያለውና መደረግና መታለፍ ያለበት የትግል አንድ ደረጃ ነው። ለመውለድ ምጥ እንደሚያስቸግረው፤ ሆኖም የግድ መደረግ ያለበት እንደሆነ ሁሉ፤ ለትግሉ ወደፊት መሄድና በድል መሳካትም፤ ይህ ተደርጎ መታለፍ ያለበት አንድ ግዴታ ነው። በአንዳንድ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ደጋፊዎች ላይ የንብረት ጉዳትና የአካል ጉዳት መከተሉ አይቀሬ ነው። በርግጥ የትግሬዎች ንብረትና ሕይወት ወርቅ ነው ለሚሉት፤ ይህ ላይዋጥላቸው ይችላል። የአማራውና የኦሮሞው ሕይወት ሲሆን አይጥ የዋጠች ድመት መሆንና የትግሬዎች ሕይወት ሲለካ ግን አራስ ነብር ሆኖ መነሳት፤ ለወግ ነው። ታሪክና ሀቅ የተለየ ባለቤት የላቸውም። ያለ ሾፌር በራሳቸው ቅኝት ይጓዛሉ። ማንም ጠምዝዞ መንገድ አያስቀይራቸውም።

በድርድር ችግሮችን መፍታትና ይቅርታ መጠያየቅ ጊዜያቸው አልፏል። ጊዜው እያለው ጊዜውን ያባከነው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ነው። በትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የሚሾፈሩት ጠቅላይ ሚኒስትር እኮ፤ “ሁሉም የጸጥታ ኃይሎች የሕግ የበላይነት እንዲያስከብሩ አዝዣለሁ።” ማንኛውንም እርምጃ እንዲወስዱ ፈቅጃለሁም ብለዋል። ይህን በማለት በሕዝቡ ላይ የጥፋት ጅራፋቸውን ለቀዋል። በኃይል ብቻ መፍትሔ ማግኘት የሚያምነውን ገዥ፤ ሕዝባዊ ትግሉ አርበድብዶታል። በአሁኑ ሰዓት፤ ይህ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ ሕዝቡን ራሱ ከመግደል አልፎ፤ የሱዳን ወታደሮችን ጎንደር ውስጥ አሰማርቶ፤ አማራዎችን እያስጨፈጨፈ ነው። በርግጥ የሱዳን ወታደር፤ የሱዳን መንግሥት በደንበሩ ሊያገኝ የሚችለውን መሬት በማጤን፤ ያለርህራሄ አማራውን መጨፍጨፉ የሚያስገርም አይደለም። የሚያስገርመው ይህ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ምን ያህል ፀረ-ኢትዮጵያ መሆኑን በገሃድ ማሳየቱ ነው። በያዘው ጊዜያዊ አንጻራዊ ወታደራዊ የበላይነት የተኮፈሰው ገዥ ቡድን፤ ከፊቱ አርቆ ማየት አይችልም። ማን ከማን ጋር ነው ድርድር የሚያደርገው? ማን እንዲሰማ ነው ይህን አድርግ የሚባለው? በርግጥ ይህን ስል፤ ይህ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በቀላሉ ይወድቃል የሚል ብዥታ ኖሮኝ አይደለም። ይልቁንም የሚያደርሰው ጥፋት እጅግ ስላሳሰባኝ፤ ለዚህ የሚከተል ጥፋትም ሆነ ከዚያ በኋላ ለሚከተለው የፖለቲካ ሀቅ ኃላፊነቱ የት ላይ እንደሆነ በማመልከት፤ መፍትሔ የመሻቱ ትኩረት የት ላይ መውደቅ እንዳለበት ለመጠቆም ነው። ዛሬ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሕዝብ ወገን የሆኑትን እየገደለ እንደሆነ፤ ነገ በሺዎች የሚቆጠሩ እንደሚገድል ጥርጥር የለኝም። እንዲሆን አልፈልግም፤ ግን አይቀሬ ነው። እስኪ ስለዚህ ፀረ-ኢትዮጵያ ግንባር ይሄን ካልኩ በኋላ፤ በባለጉዳዩ በታጋዩ ሕዝብ መካከል ያለውን ሀቅ እንመልከት።

በኢትዮጵያ ውስጥ በደልና ግፍ እየተሠራ ያለው በአማራው ክልልና በኦሮሞው ክልል ብቻ አይደለም። በማንኛውም የሀገሪቱ ክፍል፤ ከአንዳንድ ግለሰብ ሆድ አደሮች በስተቀር፤ ሕዝቡ በኑሮ ምጥና የሰሚ ያለህ በማለት አቤቱታ ላይ ነው። በርግጥ እነዚህ ሁለቱ፤ ማለትም አማራውና ኦሮሞው ግልጽ በሆነ መንገድ ተነስተው እምቢ ብለዋል። ባሁኑ ሰዓት ታጋዩ ሕዝብ አንዳንድ ቦታዎችን፤ በተለይም በአማራው ክፍል፤ ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር እያስለቀቀ ራሱ ራሱን ማስተዳደር ጀምሯል። በተለይ በአማራው፤ ከተፈረደበት የዘር ጥፋት እርምጃ ራሱን ለመከላከል ጉድብ አበጅቶ፤ መልስ መሥጠት ጀምሯል። ጥፋ ሲባል አልጠፋም የማይል እንኳን ሰው እንሰሳም አይገኝም። አሁን ባለንበት በዚህ በፖለቲካ ዓለማችን ሂደት ውስጥ፤ አንድ ግልጽ የሆነ ሀቅ ተከስቷል። ይህ ገሃድ የሆነው የፖለቲካ ሀቅ፤ በሃያ አምስት ዓመቱ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የዘር ፖለቲካ ቅንቀና ሲሆን፤ በተጨማሪ ደግሞ በታጋዩ ሕዝብ መካከል ባሉ ሥልጣን ናፋቂ ግለሰቦችና ድርጅቶቻቸው አራጋቢነትም ጭምር ነው። ሀቁ፤ በማይካድ ደረጃ የፖለቲካ አማራ” እና የፖለቲካ ኦሮሞ” መፈጠራቸው ነው። ለአንድ ኢትዮጵያ የሚደረገው ትግል ከመቼውም በላይ ተዳክሟል። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት እንደገና የመተርጎማቸው ሀቅ፤ ከትግሉ ጋር ግዴታው ፈጦ መጥቷል።

ይሄን መተርጎም የሚችለውና በትክክለኛው መንገድ የማድረግም ኃላፊነት ያለበት፤ በሥልጣን ላይ ያለው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ሳይሆን፤ ታጋዩ ሕዝብ ነው። በዚህ ሂደት፤ ላስምርበትና፤ የታጋዩ ክፍል ትልቅ ኃላፊነት አለበት። አድበስብሶ በድፍን ለአንድ ኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት እንታገል ማለቱ፤ ምንም እንኳ ያደግሁበት፣ የምፈልገውና የምመኘው ቢሆንም፤ የትናንት እና የየዋህ ሰዎች ሕልም ሆኗል። በዚህ እቀጥላልሁ ባይ፤ የዕለቱን የፖለቲካ ሀቅ አለመቀበልና የትናንት ወይንም የሕልም ታጋይ መሆን ነው። በተቃራኒውም የኦሮሞ ትግል፣ የአማራ ትግል ማለቱ፤ መግቻ ልጓም የሌለው አስፈሪ ሂደት ነው። ፈርቶ መሸሽ ግን አይቻልም። ነገን አለማወቅ፤ ሊያስወግዱት የማይችሉት የኑሮ ትልቁ ሾፌር ነው። ከአማራውና ከኦሮሞው ሌላ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ያሰኙ ሌሎች አካሎች አሉ። እኒህን ከትግሉ ውጪ ማድረግ ወይንም ያለነሱ ወደፊት መሄድ አይቻልም። ሆኖም ግን፤ በትግሉ መካከል ጎላ ብለው የሚታዩት እኒህ ሁለቱ ክፍሎች ናቸው። ይህ የዘር ፖለቲካው የፈጠረው “የፖለቲካ አማራ” እና “የፖለቲካ ኦሮሞ” ሀቅ፤ ከትግሉ ጋር ተያይዞ መፍትሔ ይሠጠው ዘንድ፤ የነገን በጎ ለምንመኝ ሁሉ፤ የዛሬ ግዴታችን ነው። ትግሉን ከዚህ ጥያቄ መፍትሔ ማግኘት የነጠለ አድርጎ መግፋት፤ ችግርን ያበዛል። ዛሬ ይሄን በደንብ አስቦበት መፍትሄ መፈለጉ ለነገ አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል።

በነገራችን ላይ፤ አሁን በሕዝባዊ ንቅናቄው ዋጥ ያሉ ወጣቶች፤ እስከሚችሉት ድረስ ከፍተኛ መስዋዕትነትን እየከፈሉ፤ ትግሉ ሕዝባዊነቱን እንዳያጣ እያደረጉ ነው። በሌላ በኩል፤እስከዛሬ ድረስ በትግሉ ሜዳ ተሰማርተው የነብሩና ያሉት ድርጅቶች በሙሉ፤ ምንም እኝኳ የሕዝብ ነን እያሉ ቢደነፉም፤ አንዳቸውም ሕዝቡን አይወክሉም። ሕዝቡን ተክተው ለድርድር መቅረብ አይችሉም። የዛሬን ሀቅና የዛሬን የትግል ንዝረት አያውቁትም። ለዚህ ትግልም መፍትሔ አሰባሳቢ ሊሆኑ አይችሉም። ከጃቸው ካመለጠ ቆየ። ዛሬ የተነሳው ሕዝብ ራሱን እየመራ ነው። ትግሉ የሕዝቡ ነው። ሕዝቡ ድርድር የሚቀርብ አካል ባሁኑ ሰዓት የለውም። በርግጥ ከላይ ታች የሚሯሯጡት እኒህ ጀግኖች፤ ኢትዮጵያን ታድገዋታል። በኒህ ጉልበት ለመወጣጣት ድርጅቶች ራሳቸውን ከፍ ከፍ ማድረግና የመሪዎቻቸውን ምስል ለማስለመድ በየፌስቡኩ መለጣጠፍ ይዘዋል። ይህ የሀገር ነፃነቱ በድርጅቶች ሳይሆን በራሱ በሕዝቡ እየተካሄደ ነው። ለሕዝቡ እንገዛ። ይልቁንስ በተለይ በውጪ ያለነው፤ በአንድነት በመሰባሰብ ከሕዝቡ ጎን እንሰለፍ። ውይይቶችንና እናድርግ፤ የድጋፍ መሰመሮችን እናብጅ። ይህ ሁሉ ኢትዮጵያን ከማዳን አኳያ ነው።

Leave a Reply