07 Sep, 2016
ለዓመታት መንግሥትን በኃይል ለመፋለምና ለመጣል ሲንቀሳቀስ የቆየው የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር ትጥቅ በመፍታት በሰላማዊ መንገድ ከመንግሥት ጋር ለመነጋገር መወሰኑ ተሰማ፡፡
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንደዘገበው፣ የግንባሩ የጦር ዋና አዛዥና ቶት ፓልቾይ አስታውቀዋል በማለት ኮርፖሬሽኑ እንደዘገበው፣ ግንባሩ ‹‹ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ በማክበር ልዩነቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት፤›› መስማማቱን ዘገባው አትቷል፡፡
የግንባሩ ጦር አዛዥም ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ጋር ትናንትና ጳጉሜን 1 ቀን 2008 ዓ.ም. መወያየታቸው ታውቋል፡፡ ግንባሩ ለዚህ ውሳኔ ከደረሰባቸው ነጥቦች መካከል በተለያዩ አካላት መጠቀሚያ ሆኗል የሚለው አንዱ መነሻ መሆኑን የጦር አዛዡ መናገራቸው ተጠቅሷል፡፡
በአገሪቱ በተለያዩ ጠረፋማ ቦታዎች ሸምቆ የትጥቅ ትግል ሲያደርግ የቆየው የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር፣ በተለይም በኤርትራና በሱዳን ድንበር የሚገኙ የግንባሩን ተዋጊ አባላት ወደ አገር ቤት ለማስገባት እንቅስቃሴ መጀመሩ ተዘግቧል፡፡
Source – Ethiopian Reporter