የብአዴንና የህወሃት ሰላዮች እየተከታተሉ አስቸገሩኝ!!!

September 8, 2016 More 

(ወልቃይት – ከጎንደር)

ምናልባት ከገደሉኝ በሚል ይሄን መልእክት እንዳስተላልፍ ነፍሴ አዛኛለች።

– አንድ ጠንካራ የአማራ ድርጅት ባስቸኳይ ይመስረት!!!

– ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎ ሸዋ ብሎ መከፋፈል ይቅር። በቃ እኛ አንድ አማራ ነን!!!

– የትግራይ ድንበሩ ተከዜ ነው፤ወሎና መተከልም ባስቸኳይ ይመለሱ!!!

– በ3,000 ታሪካችን ባርነት ውርሳችን አይደለም፤እኛ የወረስነው ርስታችን ነፃነት ነው!!!

– ሞትን መፍራት የለብንም በኖርን ቁጥር እየሞትን እንዳለን ማሰብ አለብን!!!

– የኢትዮጵያዊ መገለጫው ሰማእትነት እንጂ ባርነት አይደለም…so, ለነፃነታችን እስከሞት ድረስ ልንታመን ግድ ይለናል!!!…. በወያኔ ፍፁም ሞት ነፃነታችን ህይወት አግኝታ ነፍሳችን ጋር ትወሃዳለች!!!

በከፍተኛ ሁኔታ ሆዳም የብአዴንና የህወሃት ሰላዮች እየተከታተሉ አስቸገሩኝ። ሁሉም አማራ ሊያውቀው የሚገባ ነገር ብአዴን በፍፁም አማራን አይወክልም ገዱ አንዳርጋቸውን ጨምሮ!!! ትላንትና ዛሬ ፀሓይን አላየሁም አልወጣሁም። ድጋሚ ከታሰርኩኝ በቀላሉ ስለማይለቁኝ ትግላችን ከጫፍ መድረስ አለበት፤ አደራ። በሞቱት ወንድሞቻችን ደምና አጥንት አደራ እላችሗለሁ። በአባቶቻችን አጥንትና ደምም በድጋሚ አደራ እላለሁ። ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎ ሸዋ ብሎ መከፋፈል ይቅር። በቃ እኛ አንድ አማራ ነን!!! በውጭ ያላችሁ አማሮች እባካችሁ በፈሰሰው የወገኖቻችን ደም ይሁንባችሁ አንድ ጠንካራ የአማራ ድርጅት ባስቸኳይ ይመስረት። ይህ ድርጅት ከሌሎች ወገኖቻችን ድርጅት ጋር በመተባበር ህወሃትን መቅበር መቻል አለበት። ለወሬ ሳይሆን በተጨባጭ ልክ እንደቤተ አማራ ህዝብ ውስጥ የሚኖር መሆን መቻል አለበት። የአማራ ብሄርተኝነት ይለምልም፤ አማራ ሳይኖር እንዴት አንዲት ኢትዮጵያ ልትሉ ትችላላችሁ።

እውነት ነው አማራ በደሙ ለመሰረታት ኢትዮጵያ አንድነት ሲል ብዙ መስዋእት ከፍሏል። አሁን ግን ያ ሊያስመሰግነን ሲገባ ጭራሽኑ ብዙ ዋጋ እያስከፈለን እንገኛለን። ዘመኑን መዋጀት አለብን። መጀመሪያ አማራ ይኑር ከዛ ስለኢትዮጵያ ማሰብ እንችላለን። እንደኔ እይታ አማራ ኖረ ማለት ኢትዮጵያ ኖረች ማለት ነው። ልክ የክርስቶስ ሰውነትና አምላክነት ተዋህዶ አይነት ማለት ነው። ክርስቶስ በድንግልና ከሰው ባይወለድ ኖሮ ሰው የሆነ ክርስቶስ ማየት ከባድ ነበር። ይህ “<አይቻልም!>” ነበር። ክርስቶስ አምላክ ባይሆን ኖሮም በድንግልና የተወለደ በስጋ የተገለፀ ዘላለማዊ አምላክ ማየት ከባድ ነበር። ይህ “<አይቻልም!>” ነበር። ነገር ግን ክርስቶስ በድንግልና መለኮቱን አዋህዶ ተወለደ፤ ሰውም አምልካም ሆነ። እንደሰውነቱ ሞተ እንደ አምልካነቱም ተነሳ…..ይህም <<በሚያስደንቅና በሚያስደምም ተዋህዶ>> ነው የተከናወነው። በዚህ ካይምሮ በላይ የሆነው ተዋህዶም እኛም ለመዳን ቻልን።

የአማራ ብሄርተኝነት ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ግንኙነትም እንዲህ ያለ ነው!!! አማራ ሳይኖር (ዘሩ እየጠፋ ሳለ) ስለኢትዮጵያ አንድነት እንዴት ሊያስብ ይችላል። አሁን ግን ጠጣር ነገር መናገር አለብኝ፤ ካስከፋችሁም ይቅርታ እጠይቃለሁ። እነ ክቡር ታማኝ በየነና ሌሎች አማሮች እኔ ለናንተ ልዩ ክብር አለኝ ነገር ግን ወይ አልገባችሁም ወይም ደግሞ በዚህ ታላቅ ነገድ ስም በመነገድ ለዝናችሁ እየኖራችሁ ነው። ለማንኛውም ደማችን ፈሶ አይቀርም ያም ማለት ቢያንስ ማንነታችን ማስመለስ አለብን። ይህ ከሆነ ከትግሬዎች ጋር በሰላም መኖር እንችላለን ካልሆነ ግን ሁሉም ነገር ወደ አስከፊ ነገር ያመራል። ይህም ማለት ለኛ ከዚህ በላይ የከፋ ነገር አይገጥመንም ቢገጥመንም ያው ነው ለትግሬ ወገኖቻችን ግን ፍፁም ጥፋት ይሆናል። የወልቃይት አማራ ማንነት ጥያቄ ጥያቄ ውስጥ መግባት ያልነበረበት ጉዳይ ነው። የትግራይ ድንበር ተከዜ ነው፤ አለቀ። የትግራይ ህዝብ አስተውል ወያኔ ወደማይሆን ነገር እየመራህ ነው አሁንም አስተውል።

ሌላው መልእክቴ እኛ የአማራ ህዝብ ከኦሮሞ ወገናችን ጋር ከማንም ኢትዮጵያዊ በላይ በደም ተሳስረናል፤አብረንም ለብዙ ዘመናት ኖረናል። በወያኔ ሴራ ብዙ ግፍ ደርሶብናል። አሁንም ቢሆን በወያኔ የጥይት አረር አብረን ተቆልተናል እየተቆላንም ነው። በወያኔ ከፋፋይ ፖሊሲም ሃያ አምስት አመት እንድንከፋፈል በከፍተኛ ሁኔታ ተሰርቷል። ደማችን ግን ተመልሶ አንድ አድርጎናል። ይህ ለወያኔ ግብ አተ መሬት ነው። የ አልሞት ባይ የወያኔ የመጨረሻ ሴራዎች በጋራ መመከት አለብን በዋናነት ደግሞ የኦሮሞ ወገናችን ጥያቄ ካልተመለሰ አማራው አይተኛ፤ የ አማራው ጥያቄ ካልተመለሰም ኦሮሞው አይተኛ። አፋሩ፣ ጋምቤላው፣ቤኒሻንጉሉ፣ ደቡቡ፣ ሃረሩ፣ ሶምሊውና ሌላውም እንዲሁ።

የትግራይ ወገኖቼን ግን ኢትዮጵያዊነታቸውን እስካላሳዩን ድረስ እንደተቀየምኳቸው መሞቴን መርጫለው። ኢትዮጵያን ክዶ ዜጎቿን በጥላቻ ገድሎ ሃብቷን መዝረፍ በፍፁም ሞራላዊ አይደለምና!!! ወያኔን ከምንም በላይ ሴራውን እያወቁ አሜን ብለው መታዘዛቸውና እስትንፋሳቸው የሆነውን ኢትዮጵያዊነታቸው መካዳቸውና ደም ማፍሰሳቸውን ሳስብ ልቤ በበቀል እንዲነድ ምክንያት ሆኖኛል። ቢገነጠሉም እንኳ ከኢትዮጵያ እርቅ እንጂ ጠብ ዋጋ እንደሚያስከፍላቸው አልተረዱም ቢረዱም ደድበዋል። በውጭ ያሉት ትግሬዎች ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊበቀላቸው ይገባል ባይ ነኝ…..ለምን አገር ውስጥ ያለውን ትግሬ ደደብ ያደረጉት እነርሱ ናቸውና። አገር ውስጥ ካሉት ትግሬዎች በላይ ትግሬ ያልሆኑ የወያኔ ባንዳዎች(በዋናነት የአማራና ኦሮሞ ተወላጅ ባንዳዎች ላይ) ላይ በጣም ከፍተኛ የተባለውን እርምጃ ሊወሰድቸው ይገባል እላለሁ።

ሞትን መፍራት የለብንም በኖርን ቁጥር እየሞትን እንዳለን ማሰብ አለብን፤ ስለዚህ የኢትዮጵያዊ መገለጫው ሰማእትነት እንጂ ባርነት አይደለምና በሞት አፋፍ በሚገኝ ህውሃት እርምጃ ምክንያት ተስፋ ቆርጠን ለባርነት እጃችን መስጠት የለብንም። በ3,000 ታሪካችን ባርነት ውርሳችን አይደለም፤እኛ የወረስነው ርስታችን ነፃነት ነው!!!….ሌሎች ኢትዮጵያውያን በዋናነት ያዲስባ ህዝብ ግዜው ሳይረፍድ ትግሉን በፍጥነት ተቀላልቀል። ያዲስባ ህዝብ የቆምክባት ምድር ያባቶችህ አጥንት ባንተና በትውልድህ ውስጥ እሾክ ሆኖ በባርነት እንዳያሰቃይህ አባቶችህ የከፈሉት መስዋእት በተለይ ደግሞ ባንድ ቀን የረገፉት የ30,000 ሺ የጀግኖች ወላጆችህ አጽም በማሰብ ፈጣሪህን አስቀድመህ ተነሳ….የወገንህ ደም ሲፈስ ያንተም ደም አብሮ እየፈሰሰ ነው ያለው…..የመጣኸው ከዚህ ህዝብ እንጂ ከዚያ እንደእንጨት በቅለህ እንዳልሆነ በሚገባ የተረዳህ ይመስልኛል። ስለዚህ ሙስሊም ክርስቲያኑ ባንድ ላይ ተነስ!!!

ያማራው ጥያቄ ሳይመለስ ኦሮሞው የኦሮሞ ጥያቄ ሳይመለስ አማራው መተኛት የለበትም። የሙስሊሙ ጥይቄ ሳይመለስ ክርስቲያኑ የክርስቲያኑ ጥያቄ ሳይመለስ ሙስሊሙ መተኛት የለበትም። አንዱ አካላችን በስብሶ መኖር የሚቻለው ገላ የለንምና። በግልፅ ቋንቋ ጥያቄዎች ሳመለሱ ማለትም ወያኔ ሳይወገድ ሁሉም አይተኛ ማለቴ ነው። ይህ እንዲሆን በቆምንባት ምድር ቃል ይሁንብን!!!

ባለቃልኪዳኗ ኢትዮጵያ አሁን ከገጠመን እጅግ የሚበልጡ ብዙ ፈታናዎችን አሳልፋ ይሄው አለች ለወደፊትም ትኖራለች። በዚህ ጥርጣሬ አይግባችሁ። ስለዚህ መታገሉ ለራስ ክብርና ለታሪክ ነው እንጂ ኢትዮጵያ የምትፈርስ አገር አይደለችም። በ አለም ያለች ባለቃልኪዳን አገር ኢትዮጵያ ብቻ ነች። ስለዚህ በዚህ ደስ ብሏችሁ አገር በቀል የሆነ የሴጣን ፋሽስታዊ ድርጅት (ወያኔ) ባስቸኳይ ማስወገድ አለብነ!!!

ድል ለመላው ጭቁኑና በግፍ ለሚገድለው የአማራና ኦሮሞ ህዝብ እንዲሁም እንዲሁም የጋንቤላ፣ አፋር፣ ቤኒሻንጉል ሶማሊ በጠቅላላም ለመላ የኢትዮጵያ ህዝብ ይሁን፤ ሞት ደግሞ ለህወሃትና ዘረኛ ደጋፊዎቹ ይሁን።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፤ ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር።

እናሸንፋለን!!!

SOURCE       –      WELKAIT.COM

Leave a Reply