September 10, 2016

14 የሚሆኑ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች እና የሲቪክ ማህበራት ለተመድ የጋራ ደብዳቤ ላኩ
14 የሚሆኑ የሰብአዊ መብትና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰባአዊ መብት ኮሚሽን የወያኔ አገዛዝ በኦሮሞና በአማራው አካባቢዎች ያካሄደውን ከፍተኛ ጭፍጨፍና የሰብአዊ መብት ረገጣ በማውገዝ ና መወሰድ የሚገባውን እርምጃ በመጠቆም አንድ የጋራ ግልጽ ደብዳቤ ጳጉሜ 3 ቀን 2008 ዓም. ጽፈው ልከዋል። ደብዳቤው የተጻፈው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከመስከረም 3 እስከ መስከረም 20 በሚያደርገው 33ኛውን መደበኛው ስብሰባ ላይ ጉዳዩን ክብደት ሰጥቶ እንዲወያይበትና ውሳኔ እንዲያሳልፍበት ነው። ድርጅቶቹ በጻፉት ደብዳቤ በኦሮሞም ሆነ በአማራው አካባቢዎች በምን ዓይነት ሁኔታ ሰላማዊ የሕዝብ ተቃውሞ እንደተነሳና የሕዝቡን ተቃውሞ ለማፈን የወያኔ አገዛዝ የጸጥታ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ ከ500 በላይ የሚሆኑ ዜጎችን በግፍ መግደላቸው አጋልጠዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኃላፊ ነጻና ገለልተኛ የሆኑ አጣሪ ቡድን ወደ አገሪቱ እንዲገባ የጠየቁትን ጥያቄ የወያኔ አገዛዝ ውድቅ ከማድረጉም ሌላ በራሱ መንገድ አጣራለሁ ያለው ተግባራዊ እንዳልሆነ እንዲሁም የአፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽንም የተመድ የሰብአዊ ኮሚሽን ያቀረበውን ጥያቄ በድጋሚ መጠየቁን አስታውሰዋል። የተለያዩ የፖሊቲካ ድርጅቶች መሪዎች አባላት፤ ገለልተኛ የሆኑ ሰዎች እንዲሁም በአገዛዙ ላይ ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሲያካሂዱ የነበሩ ዜጎች መታሰራቸውንና አገዛዙ ልዩነትን በውይይት ለመፍታት የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር ፍላጎት የሌለው መሆኑን ገልጸዋል። በመጨረሻም በድርጅቶቹ በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ በተመድ የሰብአዊ መብት መደበኛ ስብሰባ ላይ ተካፋይ የሚሆኑ መልክተኞች የሚከተሉትን እርምጃዋዎች እንዲወሰዱና አስፈላጊውን ተጽእኖና ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
1ኛ/ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን በሚያሰሙ ዜጎች ላይ የወያኔ አገዛዝ የጸጥታ ኅያሎች የሚያካሄዱትን ጭፍጨፋ ባስቸኳይ እንዲያቆሙ
2ኛ/ አገዛዙ በእስር የሚያሰቃያቸውን ጋዜጠኞች፤ የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች የፖሊቲካ መሪዎችና አባላት እንዲሁም በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞች ሲያሰሙ የነበሩ ዜጎች ባስቸኳይ እንዲፈታ
3ኛ/የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የጠየቀው ጥያቄ ተግባራዊ እንዲሆን 4ኛ ግድያውናና የኃይል እርምጃው አስመልክቶ በአለም አቀፍ ደረጃ በተቋቋመ አካል ነጻ፤ ገለልተኛ እና ግልጽነት ያለው ጠለቅ ያለ ምርመራ እንዲደረግ 5/ኛ በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት ጥፋተኞች ለፍርድ እንዲቀርቡና ፍርዳቸውን እንዲያገኙ 6ኛ የዜጎችን ሰብአዊ መብት አስመልክቶ የወያኔ አገዛዝ የዓለም አቀፍ የሲቪክ የፖሊቲካ መብቶች ህጎችን፣ የአፍሪካ የሰብአዊ መብት ቻርተርንና የራሱን ህገ መንግስት እንዲያከብር እንዲደረግ የሚሉ ናቸው።

ደብዳቤውን የጻፉት ድርጅቶች
አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤
አሶሺየንስ ፎር ሂውማን ራይትስ ኢን ኢትዮጵያ፤
ሲቪከስ- ዎርልድ አሊያንስ ፎር ሲትዝን ፓርቲሲፔሽን፤
ሲቪል ራይትስ ዲፌንደርስ፤
ኢትዮፒያንስ ሂውማን ራይትስ ፕሮጀክት፤
ኢንተርናሽናል ፌዴሬሽን ፎር ሂውማን ራይትስ፤
ፋውንዴሽን ፎር ሂውማን ራይትስ ኢንሼየቲቭ፤
ፍሪደም ሃውስ፤
ፍሮንት ላይን ዲፌንደርስ፤
ግሎባል ሴንተር ፎር ሬስፖንሲፒሊቲ ቱ ፕሮቴክት፤
ሂውማን ራይትስ ዎች፤
ኢንተርናሽናል ሰርቪስ ፎር ሂውማን ራይትስ፤
ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ፤
ዎርልድ ኦርጋናይዜሽን አጌንስት ቶርቸር፤ ናቸው።

በተለያዩ ከተሞች የሚደረገው የገበያ ማዕቀብና የቤት ውስጥ አድማ ቀጥሏል

በተለያዩ ከተሞች የሚደረገው የገበያ ማዕቀብና የቤት ውስጥ አድማ ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን ከሚደርሱት ዜናዎች ማወቅ ተችሏል። በአንዳንድ ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠ ሲሆን በብዙ ቦታዎች የወያኔ የጸጥታ ኃይሎች ተሰማርተው ከፍተኛ ፍተሻዎች እያደረጉ ከመሆናቸውም ሌላ ቤት ለቤት እየገቡ ነጋዴዎች ወጥተው ሱቃቸውን እንዲከፍቱ ሲያስገድዱ ታይተዋል። ከባንክ ገንዘብ የማውጣቱ ተግባርም በተለያዩ ቦታዎች እንደቀጠለ መሆኑ ይሰማል። በርካታ የሙዚቃ አርቲስቶች በዘመን መለወጫ በዓል ለማካሄድ ያቀዱትን የሙዚቃ ዝግጅቶች ሰርዘዋል፤ ሌሎችም መሰረዛቸውን ያስታውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በቅሊንጦ እስር ቤት ያሉትና ወደ ሌሎች እስር ቤቶች የተዛወሩ እስረኞች ስም ዝርዝር ወጣ
የወያኔ አገዛዝ ባለስልጣኖች በቅሊንጦ እስር ቤት የሚገኙትንና ወደ ሌሎች እስር ቤቶች የተወሰዱ እስረኞች የስም ዝርዝር በእስር ቤቱ የማስታወቂያ ሰለዳ ላይ የለጠፉ መሆናቸውን ከአካባቢው የተገኙ መረጃዎች ይገልጻሉ። የተለጠፈው የስም ዝርዝር አሁን በህይወት ያሉትን እስረኞች ስም እንጅ የሞቱትን ወይም ቆስለው በህክምና ላይ የሚገኙት እስረኞች ስም አያጠቃልልም። በወያኔ 21 ብቻ ተብሎ በይፋ የተገለጸው የሟቾች ቁጥር በአንዳንድ ዜጎች ግምት እስከመቶ መድረሱ ይታወቃል። የሞቱትም ሆነ የቆሰሉት እስረኞች የስም ዝርዝር በይፋ አለመነገሩ ትክክለኛው ቁጥር የወያኔ አገዛዝ ከሰጠው ቁጥር እንደሚበልጥ አመላካች ነው ተብሏል። በተያያዘ ዜና በእሳቱ ቃጥሎ የሞቱት ሁለት ብቻ እንደሆነና ሌሎቹ ሁሉም በጥይት ተደብደበው የሞቱ መሆናቸው ሲገለጽ ከተገደሉት ውስጥ በርከት ያሉት በካቲና ታስረው ለማምለጥ በማይችሉበት ደረጃ እንደነበሩ ይሰማል።
ምንጭ: ፍኖተ ዲሞክራሲ

 

Leave a Reply