“ትግሬ አይሁድ ፣ አማራ እና ኦሮሞ ናዚ-ሒትለር”
ስዩም መስፍን ያው እንደተለመደው ህወሓት እና ትግራይ የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ገጽታ እንደሆኑ ነግሮናል። ስለዚህ ህወሓትን ተቃወምክ ማለት ትግሬን ተቃወምክ ማለት ነው፣ ህወሓት ይውደም ካልክ ትግሬ ላይ “ናዚ” ሆንክበት ማለት ነው።
ስዩም ስለናዚ ሊያስረዳ ብዙ ደከመ፣ ትግሬን አይሁድ አድርጎ በሕዝብ የሚደረገውን ተቃውሞ የናዚ ሲል ፈረጀው። በእርሱ ቤት ለነፃነቱ የሚታገልውን ሕዝብ ማሸማቀቁ ነው። ህወሓት በትግል 60ሺ ሰው ሰውቶ በእጥፍ አካል ጉዳተኛ ሆኖበት ለስልጣን መብቃቱን አስምሮ ነገረን። 60ሺ ስለተሰዋ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ 60ሺ ዓመት በህወሓት ጫማ ስር ሲረገጥ እንዲኖር ይፈልጋል።
ለምን 6 ሚሊየኑ የትግራይ ሕዝብ አይሰዋም፣ መስዋእትነቱ እኔን አሽከር ለማድረግ ከሆነ ለኔ ከንቱ ነው።ህወሓት ለምን 6 ሚሊየን ሕዝብ ተሰውቶበት አይመጣም ዘረኛው ድርጅት ጌታዬ፣ እኔ ደግሞ ባሪያ ልሆን አልፈቅድለትም።
ዛሬ በየዕለቱ የምትገድሉት ኦሮሞ እና አማራ ነገ ሌላውን ባሪያ ሊያደርጉ ቢታገሉ ከቆሻሻ ገንዳ ጥላቸዋለሁ። ሆኖም እንደእናንተ “አማራውን ላንኮታኩተው፣ ኦርቶዶክስን በካድሬ ቄስና ዲያቆን ልሙላው፣ ኦሮሞና አማራን እሳትና ጭድ አድርጌ የራሴን የበላይነት አስጠብቃለሁ” የሚል አስተሳሰብ ሊኖረው የሚችል ከእንግዲህ ሊፈጠር አይችልም። የህወሓት መርዘኛ ሥርዓት ለኢትዮጵያ ታሪክ መማሪያ ሆኖ ሲኦል ይወርዳል::
ከናንተ በፊት ምርጥ ዘር “Arayan race” “Master race” ብሎ የመጣው ድርጅት Nazi (National Socialist German Workers’ Party)ሲሆን ዋናው አመራር ደግሞ አዶልፍ ሒትለር ነበር።
“ትግሬ ወርቅ ነው፣ ከዚህ ዘር በመወለዴ እኮራለሁ” ያለው መለስ ዜናዊ ሲሆን ህወሓት የሆነ ትግሬ በስልጣንና በኢኮኖሚ የበላይ እንዲሆን ያደረገው ድርጅት ህወሓት ነው።
ሒትለር በታሪክ መዝገብ የጭካኔ ምሳሌ እንደሆነ ፣ መለስ ዜናዊም እንደዚያው ሆኗል። ህወሓትም በናዚ መዝገብ ስር ሊጻፍ ትንሽ ጊዜ ቀርቶታል።
ዛሬ ንፁሐን ኢትዮጵያዊያንን የምትማግዱበት ማዕከላዊ፣ ቃሊቲ ፣ ቂሊንጦ… ልክ እንደሆለከስት ግፋችሁን፣ ነውራችሁን፣ አረመኔነታችሁን ቀጣዩ ትውልድ የሚጎበኝባቸው ሥፍራዎች ይሆናሉ።
ስለዚህ ነፍሰ ገዳዩ አቶ ስዩም መስፍን:-
*በእናንተ መዝገበ ቃላት የህወሓት የበላይነትያብቃ ስል “ናዚነት” ከሆነ አዎ ናዚ ነኝ
*ህወሓት መቃብር እስኪገባ እንቅልፍ አልተኛም። ይህ ማለት ሒትለርነት ከሆነ ሒትለር ነኝ።
ምክንያቱም እውነት የሚገኘው ከናነተ በተቃራኒ ነውና! አቶ ስዩም ያ “ተወሰነልን” ያልከው የባድመ መሬት ከየት ደረሰ?.
ምክንያቱም እውነት የሚገኘው ከናነተ በተቃራኒ ነውና! አቶ ስዩም ያ “ተወሰነልን” ያልከው የባድመ መሬት ከየት ደረሰ?.
Source – Satenaw