ሰበር መረጃ — በኮንሶ ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ቀጥሏል፤ # Konso Protest//
ከኮንሶ ከዘጠኝ ወራት በፊት የጀመረው የአከላለልና ማንነት ጥያቄ ጋር የተያያዘው ህዝባዊ ተቃውሞ በአሁኑ ጊዜ ወደ ህዝባዊ ቁጣ ተሸጋግሮ ፣ ህዝቡ በህወኃት/ህአዴግ ደጋፊዎችና ህዝባዊ ትግሉ በተቃራኒ ቆመው ህዝቡን የሚያስጠቁት ላይ የደረሰበትን ተመሳሳይ እርምጃ እየወሰደ ነው፡፡በዚህም በዞኑ ዋና ከተማ ጉማይዴ፣ በኮንሶ–ጂንካ መንገድ ባሉት ጋቶ እና በኮቱ ቀበሌዎች የመንግስት ደጋፊዎች ቤቶች በህዝቡ እየተቃጠሉ ነው፡፡ የዞኑን ዋና ከተማ ለማፍረስ ትግሉ ቀጥሏል፡፡ ከዚሁ የኮንሶ ህዝባዊ እርምጃ ጋር በተያያዘ በደቡብ ኦሞ ዞን በና ኩሌ ወረዳ ቀይአፈር ከተማ አጠገብ በአልዱባ ቀበሌ ከሰፈረው መከላከያ ኃይል 6 አሰይሱዙ መኪና ሠራዊት ወደ ኮንሶ እንደተጓጓዘ ነው፡፡ ይሁንና ሰራዊቱን ጭነው የሄዱት 6ቱ አይሱዙ መኪናዎች በህዝቡ እንደታገቱና ወደቤታቸው መመለስ እንዳልቻሉ ሹፌሮቹ ገልጸዋል፡፡
——————————————— በሌላ ዜና በደቡብ ኦሞ ዞን ዋና ከተማ በጂንካ ከዚህ በፊት በታላቅ ድምቀት ይከበር የነበረው የዘመን መለወጫ በዓል የበዓል ድባብ ሳይታይበት ማለፉንና ጥቂት የማይባሉ የከተማው ነዋሪዎችና በዞኑ የሚንቀሳቀሰው ኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት/ ኦህዲኅ/ የዞን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ጥቁር ለብሰው ማሳለፋቸውን የድርጅቱ ምንጮች አሳውቀዋል፡፡ በተጨማሪ በከተማዋ በመኪና ላይ መትረየስ ጠምደው የሚንቀሳቀሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከተማዋን የጦር ከተማ አስመስለዋት የበዓሉን ድባብ የበለጠ አደብዝዘውታል፡፡ የድርጅቱ አመራሮች ወገን በየቦታው በጥይት በሚቆላበትና በእሳት በሚጋይበት በዓል ማክበርም ሆነ ለውጥ በሌለበት የዘመን ለውጥ ብሎ ነገር በወገን ላይ ከማሾፍ ወይም የወገንን ሥቃይ መካድ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በደቡብ ኦሞ በሃመር ወረዳ በኦሞ ወንዝ አጠገብ በካራና ኛንጋቶም አዋሳኝ አካባቢ በሰሊጥና ጥጥ ምርት የተሰማራው ELSE የሚባል የቱርክ የእርሻ ኩባንያ ከባንክ የተፈቀደለትን ገንዘብ ሊለቀቅለት ባለመቻሉ ለሰራተኞቹ የአንድ ወር ደመወዝ ከፍሎ ከሦስት ወር በኋላ እንዲመለሱ ማሰናበቱንና በአሁኑ ሰዓት የኩባንያው ሥራ ሙሉ በሙሉ የተቋረጠ መሆኑን የኩባንያው ሰራተኞች ገልጸዋል ፡፡