September 19, 2016

bereket-and-hilawi

 

 

 

 

 

በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ባለው የብአዴን የኮር አመራሮች ስብሰባ ካሳ ተ/ብርሀን በብአዴን ከፍተኛ አመራሮች እንደታገደ ታውቋል።

ስብሰባው በነ በረከት ስምኦን፣ በነ ተፈራ ዋልዋ፣ በነ ህላዌ ዮሴም ፣ በነ ገዱ አንዳርጋቸው ፣ በነ ደመቀ መኮነን እና ሌሎችም የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ ሲሆን ተሰብሳቢዎች ከስልክ ጀምሮ ምንም አይነት የቴክኖሎጅ ውጤቶችን መጠቀም እንደማይቻሉ እና ሦስት ጊዜ ተፈትሸው እንደሚገቡ ተናግረዋል።

ስብሰባው በወልቃይት ጉዳይና በህዝቡ እምቢተኝነት ዙሪያ ከሚነገረው መልስ ጋር ተያይዞ ከኮር አመራሮች ጋር አለመግባባት በመፈጠሩ ከመስከረም 3 – 7  2009  ዓ.ም ሊጠናቀቅ የነበረው ስብሰባ ተራዝሞ ዛሬም በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የክልሉ ስቢል ሰርቢስ ም/ሀላፊ የሆኑት አቶ ሻምበል በመረጃና ማስረጃ የህዝቡን ጥያቴ በማቅረባቸው ምክንያት አንተ ግንቦት ሰባት ነህ እስከመባል ደርሰዋል። “ህዝቡ ተጨቁኖ ቆይቷል። አሁን ግን በየቦታው ተነስቶብናል። ሊበላን ነው ምን ምላሽ እንስጥ?” ብለው ለጠየቁት ጥያቄ አቶ በረከት አርፈህ ተቀመጥ” አንተን የሚመለከትህ የሲቪል ሰርቢስ ሪፖርት ነው “በማለት መመለሱን ተከትሎ “የተሰበሰብነው በወልቃይት ጉዳይ መሰለኝ። እንጂማ አንተ የምትመራውን ኢፈርትንማ ብናነሳ ኑሮ ከነ ድርጅትህ መግማትህን እንሰማ ነበር “በማለት አቶ ሻንበል ለሰጡት የአፀፋ መልስ ከተሰብሳቢው የድጋፍ ጭብጨባ ተደርጎላቸዋል።

አቶ ገዱ ከአመራሮች ሁሉ “ወልቃይት የትግራይ ነው” ብለው በድፍረት ያልተናገሩ ሲሆን “እርስ በርስ መተላለቃችን አይቀርም” በማለት አሳስበዋል። “ስብሰባው ከህወሃት ተልኮ የፀዳ አይደለም። በረከት ህወሃት ነህ” የሚል አስተያየት እንደሚበዛ ተሰብሳቢዎች ተናግረዋል።

ዘሐበሻ

Leave a Reply