September 20, 2016

(ኢ.ኤም.ኤፍ) በዋሺንግተን ዲሲ በጣም ደማቅ የሆነ ሰልፍ መደረጉን ለማወቅ ችለናል። ሰልፉ ጠዋት ላይ ከስቴት ዲፓርትመንት ጀምሮ እስከ ኮንግረስ ድረስ፤ ብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያንን ያካተተ እንደነበር በሰልፉ ላይ የተገኙ ምንጮቻችን ገልጸዋል። ሰልፉ ጠዋት 10፡00 ላይ ተጀምሮ ከሰአት በኋላ እስከ 1፡30 ድረስ የዘለቀ ሲሆን፤ ኢትዮጵያውያኑ የኮንስቲትዩሽን ጎዳናን አጨናንቀው ነበር የዋሉት።

(የሰልፉ አዘጋጆች ከሰልፉ በፊትም ሆነ በኋላ ለዝግጅት ክፍላችን የላኩልን መግለጫ ባለመኖሩ ለማቅረብ አልቻልንም። ነገር ግን በዚህ አይነት አገራዊ ጉዳዮች ላይ ለበርካታ አመታት በመሳተፍ የሚታወቀው ቴዎድሮስ መክብብ፤ የሰላማዊ ሰልፉን ይዘት የሚያሳዩ በርካታ ፎቶዎች ልኮልናል። ፎቶ አንሺ ቴዎድሮስ ከልብ በማመስገን፤ ከዚህ በታች አቅርበናል።)

Leave a Reply