ሦስቱ የሕዝብ ማስጠንቀቂያዎች (ዲ/ን ዳንኤል ክብረት)

ሕዝብ ለመሪው በሦስት ደረጃ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፡፡ የመጀመሪያው ‹አርም› የሚል ነው፡፡ በዚህ ደረጃ ሕዝቡ ሦስት ነገሮችን አምኗል ማለት ነው፡፡ አንድም መሪው በጎ ኅሊና አለው፤ ለማረም የሚችል ዐቅም አለው፤ ችግሩ የተፈጠረው ከአሠራሩ ላይ ነው ብሏል፡፡ አንድም ደግሞ ሕዝቡ፤ መሪው እንደ ማንኛውም ፍጡር ተሳሳተ እንጂ ራሱ ስሕተት አይደለም፡፡ ስለዚህ ሊያርም ይችላል ብሎ አምኗል። በመጨረሻም ሕዝብ መሪውን ይወዳል፣ ስሕተቱን ግን ይጠላል ማለት ነው፡፡
እዚህ ላይ የደረሰ መሪ የታደለ የሚሆነው ስሕተቶቹን ነቅሶ ‹ሳይርቅ በቅርቡ፣ ሳይደርቅ በርጥቡ› ለማረም ከቻለ ነው፡፡ የሚሳሳት ፈጣሪ እንደሌለ ሁሉ የማይሳሳት መሪ የለም፡፡  መሪዎችን ታላቅና ታናሽ የሚያደርጋቸው ስሕተታቸውን ለማመንና አምነውም ለማረም ያላቸው ዐቅምና ቁርጠኛነት ነው፡፡ መሪ የሕዝቡን ጥቆማ ሰምቶ፣ የሕዝቡንም ልብ አድምጦ ችግሩን በጊዜ ካረመ ስሕተቱ ከሥራ የመጣ እንጂ ከመሪው ጠባይ የመነጨ አይደለም ብሎ ሕዝብ በመሪው እንዲተማመን ያደርገዋል፡፡ ‹ከሰው ስሕተት፣ ከብረት ዝገት አይጠፋም› ብሎ ያልፈዋል፡፡ ሕዝብ የነገረውን ስሕተት ከማረም ይልቅ ‹እኔ ደኅና ነኝ ችግሩ ከአፈጻጸሜ የመጣ ነው› እያለ ችላ ካለው ሕዝብ ወደ ሁለተኛው ደረጃ ይሻገራል፡፡ ጃን ሜዳ ሠፍሮ እያደመ ራስ ተፈሪን ወደ ዙፋን ያመጣው መሐል ሠፋሪ ጦር (ሠራዊቱ) ነበር፡፡ በኋላም አርሙ ቢላቸው አላርም ሲሉ በ1953 መፈንቅለ መንግሥት ያደረገው ይኼው ሠራዊት ነው፡፡
ሁለተኛው የሕዝብ ማስጠንቀቂያ ‹ታረም› የሚል ነው፡፡ ሕዝብ  መሪውን ‹ታረም› ካለ ሁለት ነገሮችን አስቧል፡፡ ‹መሪው ልክ ነበር ነገር ግን  እንደ ማንኛውም ፍጡር ተሳስቷል› የሚለው ሐሳቡን ቀይሯል፡፡ ‹መሪው ስሕተቱን ሊያርም ይችላል› ከሚለው ወጥቷል፡፡ ይህንን ዕድል ላይመለስበት አልፎ መሪው ስሕተት የሚሠራ ሳይሆን ስሑት (የተሳሳተ) መሪ ነው፡፡ ስሕተቱ ከሥራ ሂደት ሳይሆን ከአመራሩ፣ ከአስተሳሰቡና ከአካሄዱ የመጣ ነው፡፡ ተግባሩ እንዲስተካከል መሪው መስተካከል አለበት ብሎ ሕዝቡ አምኗል ማለት ነው፡፡ ከኩርንችት በለስ፣ ከአጋምም ወይን ሊለቀም አይችልም፡፡ ውኃው እንዲስተካከል ምንጩ መስተካከል አለበት ብሎ ሕዝብ ማሰብ ጀምሯል፡፡ እንደዚያም ቢሆን ግን መሪው ራሱን ሊያርም የሚችል መሪ ነው ብሎ አምኗል፡፡
በዚህ እርከን ላይ የደረሰ መሪ ራሱን ፈትሾ፣ መርምሮና አንጥሮ እንደ ወይን ግንድ እየገረዘ ሸለፈቱን መጣል አለበት፡፡ ሌላውን ሰውነት ለማዳን ሲባል ሕመምተኛው የሰውነት አካል እንደሚቆረጠው ሁሉ፣ ሀገርን ለማዳን ሲባል የሚቆረጡ አሠራሮች፣ አስተሳሰቦች፣ አካሄዶች፣ መሪዎች፣ ፖሊሲዎችና መርሖች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ‹ታረም› የተባለ መሪ እነዚህን አርሞ እንደ እባብ ሳይሆን እንደ ንሥር ታድሶ ከመጣ፤ ጥፋቱ ከአፈጻጸሜ የመጣ ነው፣ ሕዝቡ ስላልገባው ነው፣ ስላልተማረ ነው፣ ስላልሠለጠነ ነው፣ እያለ የመሥዋዕት በግ ፍለጋ ካልኳተነ፤ ‹ችግሩ እኔ  ነኝ፤ መፍትሔውም የእኔ መለወጥ ነው› ብሎ ካመነ፤ አምኖም ከሠራ፤ ሠርቶም ከተለወጠ፡፡ ሕዝቡ፡-
‹አሁን ወጣች ጀንበር
ተሸሽጋ ነበር› ብሎ ይቀበለዋል፡፡
ይህንን ሁሉ ትቶ መሪው በሕዝቡ ትዕግሥት ላይ ከቀለደ፤ ሕዝብም ለትዕግሥቱ ምላሹ ካለፈው የባሰ፣ ከተስፋው ያነሰ ሲሆንበት፤ ሕዝብ አመለካከቱን ይቀይራል፡፡ አርም፣ ታረም ማለት ዋጋ አልባ መሆኑን ይረዳል፡፡ ሊያርም ሊታረም የሚችል መሪና አመራር የለም ብሎ ያምናል፡፡ ችግሩ መሠረታዊ ነው ብሎ ይረዳል፡፡ በዚህ ጊዜ ሦስተኛውንና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያውን ይሰጣል፡፡ ንጉሥ ኃይለ ሥላሴን ሆ ብሎ ወደ ሥልጣን ያመጣው ወታደር፣ ስሕተቶቻቸውን ማረም ሲያቅታቸው በ1953 መፈንቅለ መንግሥት ያደረገው ወታደር፤ በ1966 ደግሞ ሥልጣናቸውን አሳጣቸው፡፡ የ1953ቱ መፈንቅለ መንግሥት ‹ታረም› የሚል መልእክት እንዳለው ንጉሡ ቢረዱ ኖሮ የ66ቱን ነገር ያስቀሩት ነበር፡፡ ግን አልሆነም፡፡ ‹ታረም› የሚለውን አልረዳ ሲሉ ‹ተወገድ› የሚለው የመጨረሻው ማስጠንቀቂያ መጣ፡፡
ደርግም እንዲህ ነበር፡፡ በ66 አብዮቱ ሲፈነዳ፣ መሬት ላራሹ ሲታወጅ የሕዝብ ድጋፍ ነበረው፡፡ ቆይቶ ስሕተት ሲያበዛ ‹አርም› የሚለው መልእክት ከያቅጣጫው መጣ፡፡ ሰልፎች፣ ወረቀቶች፣ ተቃውሞዎች መጡ፡፡ ከማረም ይልቅ ‹መረምረም› ስለመረጠ የመጀመሪያውን ዕድል አሳለፈው፡፡ ከውስጥና ከውጭ ጠብመንጃ አንሥተው ግራ ቀኝ የወጠሩት ኃይሎች ‹ታረም› ቢሉትም መታረም ትቶ ማውደምን መረጠ፡፡ የ1981 ዓ.ም መፈንቅለ መንግሥት ‹ተወገድ› የሚለውን መለከት ነፋ፡፡ ደርግ የሚተርፍ መስሎት ለፋ፡፡ ግን ተወገድ ከተባለ በኋላ መትረፍ በተአምር ብቻ ነበርና ሊተርፍ አልቻለም፡፡
ይህ ‹ተወገድ› የሚለው ሦስተኛው  ማስጠንቀቂያ የመጨረሻው የሕዝብ ጥያቄ ነው፡፡ መሪው ታምሞ አይደለም፡፡ ራሱ በሽታ ነው፡፡ ተቸግሮ አይደለም። ራሱ ችግር ነው፡፡ ደክሞ አይደለም፡፡ ራሱ ድካም ነው፡፡ ተፈትኖ አይደለም፤ ራሱ ፈተና ነው ብሎ አምኗል፡፡ ስለዚህም መፍትሔው መወገድ ብቻ ነው ብሎ ይቆርጣል፡፡ ቆርጦም ይሠራል፡፡ ሕዝብ እዚህ ደረጃ ከደረሰ በኋላ መመለስ ብዙ ጊዜ ከባድ ነው። ማረምንም መታረምንም ከሚቀበልበት እርከን አልፏልና ቀሪው ዕድል የሚሆነው በሰላም መሰናበት ነው፡፡
የአንድ መሪ ብስለት በሁለት ደረጃ ይለካል፡፡ የመጀመሪያው ሲቻል በፊተኛው፣ ሳይቻል በቀጣዩ ደረጃ ላይ መንቃት፣ ነቅቶም  ተገቢውን ማድረግ። ያም ዘመን ካለፈና ጀንበር ካዘቀዘቀች ደግሞ ራሱንም ሀገሩንም ሳያጠፋ መልካም የወንድ በር ማዘጋጀት ነው፡፡
ዘቦ እዝን ሰሚዐ ለይስማዕ፡፡

ምንጭ       _      የዳንኤል እይታዎች

mments on “ሦስቱ የሕዝብ ማስጠንቀቂያዎች (ዲ/ን ዳንኤል ክብረት)”

  1. Wake-UP says:

    ውድ ጥራዝ-ነጠቅ ፖለቲከኞቻችን መጀመሪያ ነገር ፖለቲካ መቼ እንደተጀመረ በትክክል ተረዱ፡፡ከዚያ በኋላ የምትሞነጫጭሩትን ትንተና እና አስተያየት አትኩሮት ሰጥተን እናነባለን፡፡
    መፍትሄ የማያመጣ የበሽታውንም መንስኤ የማይጠቁም ተመሳሳይ አሰልቺ ነገር ማንበብም ሰለቸን እኮ፡፡ፖለቲካ የጀመረው የዛሬ ሃምሳ ዓመት በተማሪዎች ንቅናቄ የሚመስለው የፖለቲካ ህፃን ለዚህች ሀገር መፍትሄ ሊያመጣ አይችልም፡፡እስኪ ስለፖለቲካ ታሪክ ወሳኝ ክስተቶች ትንሽ ፍንጭ እንስጣችሁ፡፡የመጀመሪያው ፖለቲካ የተጀመረው ሉሲፈር በእግዚአብሄር ላይ አመፅ ወይንም አብዮት ያካሄደ ለት ነው፡፡ሁለተኛው ፖለቲካ ሉሲፈር አዳምና ሄዋንን አስቶ ሌላ ሁለተኛ አብዮት አካሂዶ ከገነት ሲያባርራቸው ነው፡፡ከዚያ ቀጥሎ ቃየን አቤልን ሲገድለው ነው፡፡የቃየን ዘር የሚባለው ማነው?የቃየን ዘር በአለም ላይ በሌሎች ዘሮች ላይ የበላይ ሆኖ ሌሎቹን ዘሮች እያሳደደ ለማጥፋት ለምን ተነሳ?የቃየን ዘር ከሌላ ጋር ተዋህዶ ኔፊሊም የተባሉትን የተለዩ ድብልቅ ዘሮች ፈጠረ፡፡በዚህ የተነሳ የጥፋት ውሃ መጣ፡፡ሶስተኛው ዋና ፖለቲካ እግዚአብሄር ክርስቶስ ሰው ሆኖ ወደዚህ ምድር በመምጣት ሰይጣንን በመስቀል ላይ ድል ሲነሳውና በሰይጣን ባርነት ስር ለሚማቅቀው ለአዳም ዘር በሙሉ ነፃነትን ሲያውጅ ነው፡፡የቃየን ዘር እንደሌላው የሰው ዘር በአለም ላይ ተበትኖ ያለ ነው፡፡ይህ የቃየን ዘር ከጥንት ጀምሮ አለም አቀፋዊ ህብረት የፈጠረ ሰይጣናዊ ሃይል ነው፡፡በዓለም ታሪክ ውስጥ ሱመሪያ ባቢሎን ሮም ወዘተ ወሳኝ ታሪካዊ ክስቶች ናቸው፡፡ከዚያ በዓለም ታሪክ ውስጥ እስራኤል(Hebrew) እና ጂው(Jew) የሚለው ስያሜ ወሳኝ ቦታ አለው፡፡እስራኤል(Hebrew) እና ጂው(Jew) የሚለው ስያሜ ብዙ ሰው ስለሚምታታበት የአለም ፖለቲካውም እንደዚሁ ተምታቶበታል፡፡እየሱስ ክርስቶስ ጂው(Jew) እየመሰለው የሚሳሳት ብዙ ሰው ነው፡፡እርግጥ ነው ክርስቶስን የሰቀሉት ጂው(Jew) ናቸው፡፡ጥንት አቤልንም የገደለው ቃየን ነው፡፡ወደድንም ጠላንም ጂው(Jew) የሚለው ነገር የዓለምን ታሪክ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተቆጣጥሮ ያለ ነገር ነው፡፡የእኛም ሀገር የሺህ ዘመን ታሪክና ፖለቲካ ከዚህ ውጪ አይደለም፡፡የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት እየሱስ ክርስቶስ ከሄሮድስና ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠንቀቁ ብሎ ተናግሮ ነበር፡፡እውነት ነው ኢትዮጵያ ሀገራችንን እና መላውን የሰው ዘር በዓለም ላይ እየበጠበጠ ያለው ይኼው ሰይጣናዊ እርሾ ነው፡፡ከሙዚቃ ግጥሞችና ክሊፖች ጀምሮ እስከ ዋና የመንግስት ስልጣን እና የሃይማኖት መሪዎች ድረስ ይህ ሰይጣናዊ እርሾ አለ፡፡ከዚያ ቀጥሎ አዲሱ የዓለም ስርዓት የሚባለው አለ፡፡ይሄም በቅዱስ መፅሀፍ በእየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ የተገለፀ ነው፡፡ሰባት የባቢሎን ኢምፓየሮች አሉ አምስቱ ወድቀዋል ስድስተኛው አሁን ያለው የሮም ኢምፓየር ነው፡፡ሰባተኛው ወደፊት ይመጣል ብሎ እየሱስ ክርስቶስ በዘመኑ ተናግሮ ነበር፡፡ሰባተኛው ባቢሎናዊ ኢምፓየር ወይንም አዲሱ የዓለም ስርዓት የሚባለው 666 እንደሆነ በዮሀንስ ራእይ ተገልጧል፡፡ይህንን ያህል ካልናችሁ የኢትዮጵያን ሁኔታ በዚህ መንገድ ማየት ትችላላችሁ፡፡በአሜሪካ በእንግሊዝ በእስራኤል እና በተቀረው ዓለም ያለው አጠቃላይ ሁኔታ ጂው(Jew) ከሚለው ወሳኝ ነገር ተነጥሎ ሊታይ አይችልም፡፡በእኛም ሀገር ያለውን የወያኔ ምንነት ለማወቅ ጂው(Jew) የሚለውን ጠንቅቃችሁ እወቁ፡፡ከዚያ ሁሉም ነገር ይገለጥላችኋል፡፡ኢዝም(-ism) የሚባሉትን አስተሳሰቦች ሁሉ ጂው(Jew) የፈጠራቸው ናቸው፡፡የፈረንሳይ አብዮት የአሜሪካ አብዮት የሩስያ አብዮት ወዘተ የማን እጅ ነበረበት?የአንደኛው የዓለም ጦርነት የሁለተኛው የዓለም ጦርነት እና ሶስተኛውም የማን ስራ ነው የሚሆነው?በኢትዮጵያችን ከነበረው የተማሪዎች ንቅናቄ እና አብዮት በስተጀርባ ማን ነበረ?አሁንስ እያተራመሰን ያለው የዘር ፖለቲካ ምንጩ ምንድን ነው?በሀገራችን እና በተቀረውም አለም የሚካሄደው ባህልና ታሪክን የመበረዝና የማፍረስ ስራ የማን ተንኮል ነው?ፈፅሞ ማብቂያ የሌለው የማይረካ ቁሳዊ ሀብት ማግበስበስ እና ሌሎችን እየጨቆኑና እየበዘበዙ በሌሎች ላይ የበላይ ሆኖ የመስፋፋት ባህሪ የማን ባህሪ ነው?የዓለምን አጠቃላይ ሀብት ተቆጣጥሮ የያዘው እና ከዚህም በላይ ተጨማሪ ለመቆጣጠር እየጣረ ያለው ማነው?አብዛኛውን በዓለም ያሉትን የየሀገራቱን መንግስታት(አሜሪካንን ጨምሮ) ከበስተጀርባ ተቆጣጥሮ እየዘወረ ያለው ማነው?ከእርሱ ዘር ውጪ ያለውን የአዳም ዘር ሁሉ ለማጥፋት እየጣረ ያለው ማነው?ሌላውን ዘር እርስ በርስ እያናከሰና እያጫረሰ ያለው ማነው?በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ እየተደረጉ ያሉ አውዳሚ ጦርነቶችና ግጭቶች በማን ምክንያት ነው የሚቀጣጠሉት?ከአሸባሪነት ጀርባ ማነው ያለው? የተለያየ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘዴ በመጠቀም የዓለምን ህዝብ ቁጥር ለመቀነስ ከፍተኛ ሰይጣናዊ ጥረት እያደረገ ያለው ማነው? ጂው(Jew) የሚል ስም ለራሱ ያወጣው የቃየን ዘር አይደለም እንዴ?ይህ እራሱን በሀሰት ጂው(Jew) ሳይሆን ጂው(Jew) ነኝ የሚል ዘር በቅዱስ መፅሀፍ ዮሀንስ ራእይ 2፡9 ላይ ተገልጧል፡፡ኢትዮጵያም ዛሬ በዘር ፖለቲካ እየታመሰች ያለችው የዚህ ጂው(Jew) የሚባል ሰይጣናዊ እርሾ መንፈስ በኢትዮጵያ እየተንሰራፋ ስለመጣ ነው፡፡የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የውጪና የሀገር ውስጥ ተብሎ ለሁለት የተከፈለችው ለምን ይመስላችኋል?ቤተ-ክርስቲያኒቷ በሄሮድስና በፈሪሳዊ እርሾ እየተበከለች ስለሆነ ነው፡፡የጂው(Jew) መንፈስ ፀረ-ክርስትና እና ፀረ-ክርስቶስ ስለሆነ ነው፡፡በህግ ጥላ ስር ያለን እስረኛ ከነህይወቱ ማቃጠል ሊያመልጥ ሲል ደግሞ በጥይት መግደል የዚህ የጂው(Jew) ሰይጣናዊ መንፈስ ተግባር ነው፡፡በነገራችን ላይ የጂው(Jew) ሃይማኖት መመሪያው የባቢሎን ታልሙድ ነው፡፡በዚህ የባቢሎን ታልሙድ ህግና እምነት መሰረት ከጂው(Jew) ውጪ ያለው ሰው ጎይም(Goyim) ተብሎ ይጠራል፡፡ጎይም(Goyim) እንደ ሙሉ ሰው አይቆጠርም፡፡ስለዚህ አንድ ጂው(Jew) ሌላውን ጎይም(Goyim) መግደል፣ማታለል፣መስረቅ፣ማፈናቀል፣ማሰደድ፣ሀገር-አልባ ማድረግ፣ ማደህየት፣ማስራብ፣ማሰቃየት፣ህክምና መከልከል፣ፍርድ ማዛባት፣እና ሌላም ብዙ አይነት አ-ሰብዓዊ ተግባር መፈፀም ይቻላል እንደሁኔታውም ይህንንም ማድረግ አለበት፡፡ህገ-መንግስት እና ዲሞክራሲ የሚባለው ነገር ዝም ብሎ ማታለያ ነው፡፡የጂው(Jew) ዘር በብዛት ጥቂት ቢሆንም የራሱን ህቡእ አለም አቀፍ ኔትወርክ በመፍጠር አለም አቀፍ አሊያንስ ወይንም ትብብር አለው፡፡ጎይም(Goyim) የሚባለው አብዝሃው ቁጥር ግን ይህንን ለማድረግ ስላልቻለ በጥቂቶቹ በጂው(Jew) ሰይጣናዊ ተንኮል እየተጠቃና እየተሰቃየ ነው፡፡የሚገርመው ነገር ጂው(Jew) ተቀናቃኙን ጎይም(Goyim) ለማጥቃት በዋናነት እየተጠቀመ ያለው እራሱን ጎይም(Goyim) ነው፡፡ወያኔዎች የሚያደርጉት የዚህን ግልባጭ ነው፡፡የዓለም ፖለቲካ ኢኮኖሚና ሌላውም አጠቃላይ ስርዓት በዚህ ተፅእኖ ስር እየወደቀ ነው ያለው፡፡በኢትዮጵያ ከዛሬ 1100 ዓመት በፊት የነበረውን የዮዲት ጉዲትን ዘመን የሚያስታውስ ካለ መረዳት ያለበት ወያኔ የዘመናችን ዳግማዊ ዮዲት ጉዲት እንደሆነ ነው፡፡ከላይ በአጭሩ በጠቀስቁት መንፈሳዊ እይታ ስትመሩ ፖለቲካውና ሌላውም ይገባችኋል፡፡ሁለ-ገብ ትግሉ ዛለቂና አስተማማኝ ውጤት የሚኖረው ሁኔታውን በዚህ መንገድ ጭምር ስንረዳው ነው፡፡የዛሬ 120 ዓመት አፄ ምኒሊክ አድዋ ሲዘምቱ ታቦት ይዘው የሄዱት የሚዋጉትን ሰይጣናዊ ሃይል ምንነት ጠንቅቀው ስለተረዱ ነው፡፡ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመውረር የመጣችው ከበስተጀርባ በሮም ቫቲካን ተገፋፍታ ነው፡፡ሮም ቫቲካን ደግሞ ማን እንደሆነች የሚያውቅ ያውቃታል፡፡የዘመኑ ትውልድ ከአያት ቅድመ-አያቶቹ ብዙ መማር ሲችል እንደዚህ መሆኑ ግን በጣም ያሳዝናል፡፡ለነገሩ ኢትዮጵያ አዲስ ምእራፍ ችግር ውስጥ መግባት የጀመረችው የኢትዮጵያ ምሁር መፅሀፍ ቅዱስን ወርውሮ ሲያበቃ ከቆየው የቤተ-ክርስቲያን አስተምህሮት ጋር ተለያይቶ በምትኩ የማርክስን ዳስ-ካፒታል እና ሌላውንም አለማዊ እውቀት እንደ መፅሀፍ ቅዱስ መቀበልና ማመን ሲጀምር ነው፡፡የመንፈሳዊውን ዓለም እውቀት ከአለማዊ እውቀት እና ስልጣኔ ጋር አስተባብሮና አስማምቶ ለማየት ቢቻል እንደ ሀገር አሁን ያለንበት ምስቅልቅል ውስጥ ላንገባ እንችል ነበር ብዬ አስባለሁ፡፡ፖለቲከኞቻችን ለማንኛውም ቅዱስ-መፅሀፍን ልትተኙ ስትሉ እንኳን ትንሽ ገልበጥ እያደረጋችሁ አንብቡት፡፡ያለበለዚያ አሁን እየሄዳችሁበት ባለው አካሄድ ለሀገራችን ትርጉምና ፋይዳ ያለው መፍትሄ ልታመጡ አትችሉም፡፡
    ቸር እንሰንብት፡፡

    • Tizebt tesfaye says:

      you have a point, very few understood this. and Deacon Daniel kibret articulation is perfect and it is based on the reality. it shows the voice of the people will be heard one way or another. but better to choose wisely the incumbent regime for its own sake…if not it is inevitable to be get rid of for good.

  2. SEYFU says:

    Daniel kibret

    ante tesleklaki zendo weyane

    asmesay banda !! ye weyane ashker ,dirashih yetfa

    ande metetegna Debtera

    be Afiliho ena awde negest eyetebetebik

    raskin temeramare kkkkkk ye betekiresteyan tebebit

    tawaki tomare eyalk teshomale ,,

    ye mender teret teret selchitonal

    yemender Debreta Miqegna telalaki !!!

  3. tizibt says:

    what ever it is. Daniel Kibret’s view and looking is perfect. Seyfu what is ur problem? are u normal? unless why u insulted him. there must be some thing wrong with u. as daniel said this thives and killers and haters are given all the advise including the last one “leave the power.” but they don’t leason. so, they (u) will go by force.

  4. HI EPHREM TESFAYE says:

    Daniel kibret’s notions is correct . halo seyfu are you normal ?

  5. Tigisworku says:

    egziabherkefyadergh

  6. gremewu says:

    ሰዎች አደብ እንግዛ እንጅ ዲያቆነ ዳነኤል በግንዛቤዉ እዉቀትን ሰጠን በቅጡ የማያነብ ትችትን ምን አመጣዉ?

  7. ትግራይ ሪፐብሊክ says:

    ግዜው የብሶት ዘመን ነው።

  8. Angile says:

    የህዝብ ጥያቄ ስልጣን በአንድ አንስተኛ ጠባብ እጅ ስለወደቀ እኩል ተካፍለን አገራችን በጋራ እናስተዳድር ነው። የ 100 ሚሊዮን ህዝብ አገር በጥቂቶች መተዳደር ይብቃ። የአደራ መንግስት ሁሉንም ያካተተ ይቋቋም ነው ያለው ህዝቡ። ጥገና ሳይሆን ለውጥ። ሰው መቀያየር ሳይሆን የስርዐት ለውጥ። አባ ድላን አንስቶ ተሾመ ቶጋን መተካት ሳይሆን ምሁራንን የአገር ሽማግሌዎችን ተቃዋሚዎችን ያካተተ የአደራ መንግስት በአስቸኳይ ይቋቋም ነው ጥያቄው መልሱም እሱ ብቻ ነው። ወያኔ መሽቶብሃል ቶሎ ፍጠን ሳትበላ።

  9. ፍቅርተ ማርያም says:

    ዲያቆን ዳኒ , የስማዕታት ኣምላክ ይጠብቅህ ኣሜን. በርታ ዋጋህን መድሃኒያለም ይከፍልሀል.ምነው የሃይማኖት ኣባቶቻቾን ዝም ኣሉ? ኣቤቱ የራሔልን እንባ ዝም ያላልክ ኣምላክ ኣቤቱ የኢትዬጵያን እናቶች ኣሥባቸው.የምህረት ጊዜ ኣሁን ይሁን.ኣሜ

:)

 

Leave a Reply