ሰሙኑን ስለ ውራይና መፅሄትና ስለ ነጋ ዘርኡ ዘገባ ትንሽ ለመዳሰስ ሞክሬ ነበር። አሁን ደግሞ ነጋ ዘርኡ በውራይና መፅሄት በገብሩ መፅሐፍ ስለተቸበትና ሌሎች ሰዎች በዚህ መፃፍ ለሚያነሱት ጥያቄ የተወሰነ ማብራርያ ለመስጠት እፈልጋለሁ።

በመጀመሪያ ደረጃ ነጋ ዘርኡ የገብሩን መፅሐፍ ሳያነብ የሰጠውን ትችት ከቁብ አልቆጥረውም። ምክንያቱም “አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል” ብየ ነጋ ላይ ትዝብቴ ሰጥቻለው። ቢሆንም ነጋ ትችቱንና ዱላውን በገብሩ አስራት ላይ የሰነዘረው አሁን በመፅሐፍ ላይ ተንተርእሶ ሳይሆን ከዚህ ቀደም በነበረው ከህወሐት በስወማው አሉባልታዎችና እንዲሁም እራሱ ነጋ የወይን መፅሄት አዘጋጃ ስለነበር ይሆናል። የሆነ ሆኖ በአጠቃላይ ነጋ በውራይና መፅሄት የገብሩን መፅሐፍ ሳይሆን ገብሩ ብቻ ነበር የተቸው። እባካችሁ መፅሄትዋን እንደምንም ብላችሁ አግኝታችሁ ተመለከቱዋት። በአብዛኛው ትችቶቹ ገብሩን እየተቸ ከመፅሃፉ ጋር ለማገናኘት ይሞክራል ልክ እንደ ነጋ ዘርኡ በዙ ሰዎቸ ከዚህ በፊት በህወሓት ተነድፎ በካደሬዎች የተለቀቀው የስም ማጥፋት ዘመቻ ተንተረሰው ገበሩ እንዲህ አደረገ ከዳተኛ እያሉ ሲሰብኩ ነበር። የኔ መነሻ ከሰው ወሬ ተላቀን ከባለ ጉዳዩ መሰማት የሚበጅ ይመሰለኛል። ምክንያቱመ ገበሩ ከበቂ በላይ ማሰረጃዎች ይዞ ብቅ በሏል።

እኔ የገብሩ አስራት መፅሐፍ ገዝቸ ሳነበው ያገኘሁት ጥቅም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያነበው እንደሚገባ በአፅንኦት መናገር እፈልጋለው። በእውነት ገብሩ ትክክለኛ የእውነት ፈርቀዳጅ ጀግና ቢየዋለው። ይህ እንድል ያደረገኝ እስከ አሁን ስለ ህወሐት የሚወጡት መፃህፍት እንትና እንዲህ አደረገ እኔ እንዲህ አላዳረኩም ነበር። የገብሩ አያያዝ ግን እንዲህ አድርገን ተሳስተን ሰርተናል። ይህ ማድረጋችን በወቅቱ ትክክል ቢመስልም ዛሬ ላይ ሁኘ ሳየው ስህተት ነበር ማለቱ በጣም አዋቂነቱና ለዘመኑ ወጣት ትልቅ ትምህርት ነው።

በዉራይና መፅሄት አንዲ ገበሩ የስልጣን ፈላጊ እንደነበር ሲተርክ በሌላ ገፅ ደግሞ ገበሩ እነ ግደይ ዘረአፅዮን፤ አረጋዊ በርሀ ከሀወሓት ሲወጡ ለምን አልተቃወመም ወይም ለመን ያኔ ከነሱጋ ጋር አልወጣም የለናል። እንደገና ተመልሶ ገበሩ እንዴት ስብሐትንና መለስ አንዲሀ እንዲሀ አደረጉ በሎ ይፅፋል? የሚሉና ሌሎቸ በማሰረጃ ያልተደገፉ ጉዳዮችን አነሰቶ በገበሩ ትችቱን ይሰነዝራል።

ገብሩ አሰራት የስልጣን ጥመኛ አልነበረም። ምክንያቱም ከ1971 ዓ/ም ጀመሮ በሀወሐት በተለያዩ ሃላፊነቶች ሰረቷል። በተጨማሪም ከ1983 እሰከ 1993 ዓ/መ ለ10 ዓመታት የትግራይ ክልል አስተዳዳሪም ነበር። ለገበሩ ሃላፊነት ወይም በሰልጣን መቀመጥ አዲሰ ነገር አይደለም። የልቅ ገበሩን ከህወሐት የለየው በአገራዊ አጀንዳና ከዚህ ቀደም በህወሐት ሲፈፀሙ የነበሩት ስህተቶች በማስተዋሉ ነው። ከዚህ በፊት በድርጅቱ የተለያዩ ችግሮቸ ሲፈጠሩና የተለያዩ ታጋዮቸ ትግሉን ጥለው ሲወጡ ገበሩ አብሮ ያለወጣው በወቅቱ የገበሩ አቋምና የድርጅቱ አካሄደ መገንዘብ የግድ የላል። ሌላው ገብሩ በምን ሞራል ነው እነ መለስና ስብሐት የሚተቸው ለሚለው ትችት ብዙ ታጋዮቸ በወጡዋቸው መፃህፍት ሁለቱንም ተችተዋል። ምክንያቱመ በህወሓት ዋና የሴራ ጠንሳሾችና የስልጣን ጥማት የነበራቸው እነሱ ነበሩ። ለዚህም የሰሩትን ሰራ ገብሩ በመፅሃፉ ከነማሰረጃው ስላጋለጠው ሄዶ ማንበብ ይበጃል። ሌላው በጣም የሚገርመኝ ነገር ገብሩ በትግራይ እድገት ችግር እንደፈጠረ ይነገራል። ለምሳሌ ውራይና እንዳለው የአላማጣ ኬላ ቸግር ብዙ ንበረት ከፌደራልና ከክልል ጋር ተገናንቶ ጥቅም ላይ መዋል የነበረበት በገብሩ ትእዛዝ ለችግር እንደተጋለጠ ይናገራል። ሰዎች እባካችሁ የገብሩን መፅሐፍ ከገፅ 211 እስከ 214 ያለውን አንብቡት ስንት ሰሊጥና ቡና ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ ሊገባ ሲል የያዘ እንዲሁም ስንት መሳሪያና ዊሰኪ ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ የያዘ ጀግና መሪ ነበረ። ይህ የሰሊጥ ኮንትሮባንድ አንቀሳቃስ ከነበሩት አንዱ ሰብሐት ነጋ ነበር ለዚህም እኒ ማህደር የአይን ምስክር ነኝ።

ሌላው በጣም የሚያሳዝን ትችት በገብሩ ላይ የተሰነዘረው። ገብሩ በኢትዮ-ኤርትራ ግጭት ስልጣን ፈላጊ ስለሆነ አፈነገጠ መባሉ ነው። ይገርማቹዋል ወግያው ሊጀመር ወራቶች እስኪ ቀሩት ደረስ አሁንም በትግራይና አዲስ አበባ ካሉት ትላልቅ ሰዎቸ ሳይቀር አስመራ ድረስ ሄዶ ከኢሳያሰ ጋር ተነጋግሮ በግሉ ተጨማሪ ጥናት አድርጎ የመጣ የበሰለ መሪ ነበር። እንዲሁም ከህዝቡና ከመሰል የትግራይ ክልል ሃላፊዎች ጋር ሆኖ የሰበሰበው መረጃና ማስረጃ ይዞ መለስ ዜናዊ ጋር ቢገናኝም መለሰ አተቀበለውም። ይባስ ብሎ ሻዕቢያ ባድመና ሲይዝ ግንቦት ወር ገበሩ፤ ስየ መለሰ ጋር ገብተው ጉዳዩን ቢነግሩት እምቢ በህወሓት ኮሚቴ እናየዋለን ብሎ ሲያግታቸው ገብሩ ግን በራሱ ፈቃደ ከተወሰኑ ህወሐት መሪዎቸ ተሰማምቶ በድምፂ ወያነ ቀርቦ የመጀመሪያ “አገር ተወራለች ዝመት” በሎ አዋጅ የተናገረ ኢትዮጵያዊ ሃርበኛ ነበር። ከገብሩ በኋላ እነመለስ ጉዳዩ ተቀብለው ወደ ፓርላማና የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚዎች አቅርበዉ አፀደቁት። እዚ ላይ የዉራይና ደራሲ ነጋ ዘርኡ እኔ በግንባር ነበርኩ ሁሉም አውቃለሁ እያለ በቅድመ ግነባር እንደፃፈው አሁን ደግሞ በፌስቡክ የግሉ ገፅ ላይ “ገብሩ ሰኔ 3/1990 ጀነራል ፃድቃን ዛላምበሳ ኮማንድ ፖስት ነበር በሎ ፃፈ። ይህ ውሸት ነው በወቅቱ እኔ ነጋ ዘርኡ ፃድቃን በአዲ አዉዓላ ነበር ያገኘሁት ገብሩ ዋሽቶ ነው የፃፈው” በማለት ገብሩን ይተቻል። ሰዎች እባካችሁ ይህ ጋዜጠኛ መላ በሉት። በገብሩ መፅሐፍ ላይ እንዲህ የሚል ቃል የለም። ይገርማቸሁዋለ በገብሩ መፅሐፍ በገፅ 286 እስከ 287 ሄዳችሁ ተመልከቱት ገብሩ ፃድቃንን በዛላምበሳ አከባቢ በዋና የእዝ ማዕከል ውግያ ይመራ ነበር ያለበት ጥር 1991 ዓ/ም ነበር። እንዲያውም ለተጨማሪ ማብራሪያ ብሎ ገበሩ በገፁ ግርጌ ላይ WALTA INFORMATION CENTER 2001,OP,CIT,P,9. በማያሻማ መልኩን አስቀምጧል። በዛላምበሳ አከባቢ ፈፃ በተባለው ቦታ የእዙ ኮማንድ ፖስት እንደነበር ተጨማሪ ማበራሪያ ከፈለክ ባድመን እንደምክንያት የሚለውን በኮ/ል ተወልደ ገ/ትንሳኤ የተፃፈው መፅሐፍ ገፅ 49 አንብበው።

አየ ነጋ ዘርኡ የዋሸው ገብሩ ሳይሆን አንተ ነህ። አረ ልጨምርልሀ ያንተ ጉድ አሁንም በፌስቡክ ገፅ ላይ እንደፃፍከው “ በሰኔ 3/1990 ዓ/ም የኢትዮጵያ ኮማነዶ ሲመራ የነበረው ኮ/ል ናቃቸው ነበር ብሎ ገብሩ ፅፏል” ስትል ገብሩን ስሙን ለማጥፋት ሞከርክ። በጣም በጣም አዘንኩብህ አለማወቅህ በቻ ሳይሆን የሆነ ተልእኮ እንደተሰጠህ አረጋገጥኩልህ። ይገርማችሁዋል ገብሩ ስለ ኮ/ል ናቃቸው የተናገረው በገፅ 276 ዓንቀፅ 2 ላይ ኮ/ል ናቃቸው አንድ በርጌድ የዞ ተዋግቷል። ከዚህም ብርጌደ እንደነ ቢኮ የተባለው ጀግና የጋምቤላ ተወላጀ ታሪክ ሰርቷል” ሲል አሰቀመጠ እንጂ አንተ እንዳልከው አይደለም። እንዲያውም የገብሩ አባባል የሚደግፍ ከዚሀ በፊት ባድመን እንደምክንያት ብሎ የፃፈው ኮ/ል ተወልደ ገ/ትንሳኤ በገፅ 389 እና በገፅ 129 ኮ/ል ናቃቸው በ31ኛ ክ/ጦር የብርጌድ 2 አዛዥ እንደነበር ፅፏል።

ሌላው የኤርትራ መገንጠል ጥያቄ ገብሩንና ሌሎች ከህወሐት የወጡት ነባር ተጋዮች ለመተቸት ብዙ ተሰርቶበታል። በጣም በጣም የሚያሳዝነኝ የኤርትራ የመገንጠል ጥያቄ መልስ የሰጠቹ ህወሓት ገና በጫካ ሳለች ነበር። በዛን ወቅት የኢትዮጵያና ኤርትራ ህዘቦች በማያወቁት መንገድ ቀድሞ የተወሰነ ጉዳይ ነበር። በወቅቱ ህወሓት በታሪክ ያልተደገፈ ኤርትራ በኢትዮጵያ ቀኝ ግዛት እንደተያዘች ስታስተምር የተቃወሙ ደረጅቶቸ እንደነ ኢህአፓ፣ ኢዲዩ፣ መኢሶን፣ አነግ/የአፋር ነፃአውጪ ግንባር፣ እንዲሁም ግገሓት ነበሩ። ይህ ተደፍኖ በህወሐት ማዕከላዊ ኮሚቲ ተይዞ የነበረው እቅድ ኢህዴን/ብአዴን/ መጀመሪያ ቢቃወሙም በኋላ ላይ ግን ተቀብለውታል ኦህዴድ ጭምር ተቀብሎታል። የሚያሳዝነው ነገር የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በፈጠረወ መዘዝ ከድርጀቱ የወጡት ታጋዮች ኤርትራን ለመመለስ አምፀዋል ተብለው ተፈርጀዋል። ይህ ግን እውነት አይደለም ምክንያቱም ጦርነቱ እስከ አስመራ የሚለውን ሃሳባቸውና የነሱ አቋም የነበረው የሻዕቢያ ሃይል ዓቅሙን ሰብሮ በአከባቢው ሰላምና ደህንነት እንዲፈጠር ነበር ፈላጎታቸው። እንዲያውም ሻዕቢያ ከተመታ በኋላ በኤርትራ ለሚኖረው ፖለቲካዊ ሰጋት በነ ፀጋይ በርሄ አሰተባባሪነት የተሰባሰቡ ካደሬዎቸ በኤርትራ ትልቅ ሰራ ለመስራት ተዘጋጅተው ነበር። በወቅቱ በኢሀአዴግ ማእከላይ ኮሚቴ ጉዳዩን ቀርቦ እነ መለሰና ሰብሐት በድምፅ በልጫ ተሸንፈው ጦርነቱ ተጀመሮ ነበር። የሆነ ሆኖ መለስ በዘየደው መነገድ ጦርነቱ ሁሉ አዲቆም ከማድረጉ ባሻገር ከህወሐት አመራሮቸ ጋር ትልቅ ክርክር የጀመረበት ወቅት ነበር። በጣም የሚያሳፍረው የመለሰ የነበረው አቋም ቀድሞ ወደነበርንበት ተመልሰን ድርድር በማድረግ ሰምምነቱን እንፈርም የሚል ነበር። ያሳፍራል በዚህ አሳቡ በስንት መሰዋእትነት የተመለሰችሁ ባድመ መተው የሚል አቋሙ በመድረኩ አቀረበ። እነዚህ ከህወሐት የወጡተ ታጋዮች የመጨረሻ መቋቋም እስኪሳናቸው ነበር የተናደዱት።

ሌላው ዋናውና የመጨረሻው አስገራሚው የውራየና ደራሲ ነጋ ዘርኡ በውራየና መፅሄት ገፅ 15 ላይ ገብሩ ከአንደነት አመራሮቸ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ የተነሳውን ፎቶ ለጥፎ ገብሩን እንደከዳተኛ ይተቻል። ይህ የነጋ አቋም ቀደም ብሎ በ2002 ዓ/መ አገራዊ ምርጫ ላይ ህወሐትና ካደሬዎቹ በሰፋት ፐሮፓጋነዳ የሰሩበት ድራማ ነበር። በወቅቱ ገብሩ አስራትና ስየ ኣብረሃ ለ17 ዓመታት ያደረግነው ትግል ስህተት ነበር ብለው በመስቀል አደባባይ ይቅርታ ጠየቁ ተብሎ ስማቸው ለማጥፋት ዘመቻ ተካሄደ። ይህ አመለካከት እስከ ዛሬ ድረስ ያልገባቸውና እውነት መሰሎዋቸው ይዘውት ያሉት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎቸ አሉ። እውነታው ግን እንደዚህ አይደለም ልክ ገብሩ አሁን በመፃፉ ላየ ገፅ 432 እስከ 433 እንደገለፀው በወቅቱ በመሰቀል አደባባይ የተገኙት ገብሩ አሰራት፣ አለምሰገድ ገ/አመላክ፣ አውዓሎም ወልዱ፣ የውብ ማር አሰፋ እንዲሁም ደ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ነበሩ። በስብሰባው እለት ገብሩ በመድረኩ የተናገረው በኤርትራ ጉዳይ ስለነበረው የተሳሳተ ፖሊሲና አሁንም ኢትዮጵያ ያላትን እድል የሚያሳይ ዝርዝር ነበር። ይቅርታ የጠየቀበት ነገር ደገሞ በኤርትራ ላይ የቀኝ ግዛት የሚለው በህወሐት እያላ ሲከተለው ሰለነበርና የተሳሳተ አመለካከት እንጂ ስለ 17 የትጥቅ ትግል እንዳልነበር ገልፇል። እንዲያውም በወቅቱ የታተሙ ከነበሩት የግል ጋዜጦች አንድዋ የወሰደው ማሰረጃ በመፅሐፉ የመጨረሻ ገፀ 501 እስከ 506 መመልከት የቻላል።

ገብሩን እንዲህ የተቸች ህወሐት በታሪክዋ ጠላቶች ከምትላቸው ድርጅቶች ጋር በዙ ጊዜ ተገናኝታና ተደራድራለቸ እንዲያም ከአንዳነዶቹ ጋር ለተወሰነ ጊዜ ቢሆንም ሰርታለች። ይህ ሂደት እስከ ግለሰቦች ሄዷል። እስቲ በህወሐት ታሪክ የነበሩት ከተቃዋሚ ወይ ጠላት ጋር የነበረ ግንኝነት እንመልከት
1. ከኢህአፓ ጋር ረዘም ላለ ጊዜ ተገናኝተዋል
2. ከኢዲዩ ጋር ሞክረውት ሳይሳካ የቀረ በተለይ በምዕራብ ትግራይ ትላልቅ ሰዎቸ
3. ከደርግ ጋር 3 ጊዜ በ1981 በለንደን/እንግሊዝ/፣ 1982 ሮም /በጣልያን/፣ በ1983 የመጨረሻው በሮም/ጣልያን/
4. ከአነግ /አፋር ነፃ አውጪ ግንባር/ በሱልጣን ዓሊምራሕ የሚመራው 1970 ዓ/ም
5. ከኦነግ /ኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር በ1976 ዓ/ም በክንፈና ሙሉጌታ ገ/ህይወት /ጫልቱ/ የሚመራ አንደ አሃዱ በሱዳን በኩል ዌዴ ወለጋ ገብቶ አብረው ለመስራት ሞክረው ነበር።
6. በስተመጨረሻም በሽግግር መንግስት ወቅት የነበሩት ፓርቲዎችን እናስታውሳለን
እስቲ አሁን ደገሞ በግለሰብ ደረጃ የተወሰኑት ልበል
1. ዛሬ በእስር ላይ የሚገኘው የግንቦት 7 ም/መሪ የያኔው የኢሀአፓ ታጋይ አንዳርጋቸው ፅጌ 1971 ዓ/ም ከህወሐት ጋር በተደረገ ውግያ ቆስሎ ሲማረክ ህወሐት አማራጭ አበጀለት። ይሀውም አማራጭ በዓድዋ አከባቢ መረብ ወንዝ ዳርቻ ዓዲ ፍታው በተባለው ቦታ ድርጅት እንዲመሰርት ነበር። በወቅቱ አንዳርጋቸው ፅጌ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ እንቅሰቃሴ የሚል ድርጅት ቢመሰርትም የህወሐት አላማና ያያዝ በደንብ ከተረዳ ቡኋላ ከተግሉ ወጥቶ በሱዳን አድርጎ ወደ ውጭ ውጣ። ቢሆንም ግን ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ተመልሶ ከኢህዴን/ብአዲን/ ጋር አባል በመሆን በኢህአዲግ ከታቀፈ በኋላ ለተወሰነ ጊዜ የአዲሰ አበባ ከተማ ዋና ፀሃፊ ሆኖ ሰርቷል።
2. ከኦነግ መሪዎቸ አንዱ ሌንጮ ለታ በ1981 ዓ/ም በዋሽንግተን ዲሲ ከመለስ ጋር ተገናኝተዋል። እንዲሁም 1983 ዓ/ም በኤርትራ አማላጅነት በተዘጋጀው የኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት ሰነድ ላይ በህወሓት በኩል መለስ ዜናዊ በኦነግ በኩል ሌንጮ ለታ ታዛቢዎቸ ከኤርትራ ኢሳያስ አፈወርቂ፣ አሊ ሰይድና ስብሐት ኤፍሬም ከነ አማካሪዎቻቸው በተገኙበት በሰንዓፈ ከተማ ተፈራርመዋል።
3. የዛሬው የጉንበት 7 ሊቀመንበር ደ/ር ብርሃኑ ነጋ በ1982 ዓ/ም ከመለስ ዜናዊ ጋረ በዋሽንግተን ዲሲ ተገናኝተዋል።

ለማጠቃለል ያህል ሰው ከዚህ በነበረበት አመለካከት ሳይሆን አሁን ባለው ሁኔታ ተመዝኖ ቢታይ መልካም ነበር። ትላንት የደርግ ኢሰፓ አባላት ነበሩ የትግራይ ህዝብ ጠላቶች ናቸው እየተባለ የሚሰራ ፐሮፓጋንዳ የሚረባ አይደለም። ዛሬ ለኢትዮጵያ ባላቸው ራእይና የፖለቲካ በቃት ሁኔታ ቢመዘኑ አይከፋም። ህወሐት እኮ የደርግና ኢህአፓ ታጋዮችን የዛ ነበር ኢህአዴግን የመሰረተች።

ኢህዴን/ብአዴን ከዚህ በፊት የኢህአፓ ኣባሎች ህወሐትን ሲፋለሙ የነበሩ

ያሬድ ጥበቡ /ጀቤሳ/ ሕላዊ ዮሴፍ ገ/ሰላሴ
ያሬድ ከበደ ታደሰ ካሳ /ጥንቅሹ/ ሃይሌ ጥላሁን
ታምራት ላይኔ ተፈራ ዋልዋ
ደውድ በረከት ሰምዖን
ምትኩ አሸብር አዲሱ ለገሰ

ኦህዴድ እነዚህም በሙሉ በኤርትራ የተማረኩ የደርግ ወታደሮቸ የነበሩ ሲሆን ገሚሶቹ በሻዕቢያ ተገደው መንገድ እይጠረጉ ሲዉሉ የነበሩ ናቸው። ተወሰኑ ደግሞ በህወሐት የተማረኩ ይገኙባቸዋለ

ኩማ ደመቅሳ /ታዬ/
አብራሂመ መልካ
አባዱላ ገመዳ
ባጫ ደበሌ

በስተመጨረሻ ደግሞ የደርግ ሰራዊት የነበሩ በህወሐት ተማርከው የራሳቸው አደረጃጀት አድርግው እንዲቀሳቀሱ በህወሐት ሰር የነበሩ የኢትዮጵያ ዲሞከራሲያዊ መኮንኖች አብዮታዊ ንቅናቄ የሚባሉ በጀነራል አለምሸት ደግፌ የሚመሩ 1983 ዓ/ም ከህወሐት ክ/ጦሮች ሁነው ደርግን ተፋልመዋል።

ሰለዚህ በትናንትና ዛሬ ሰው መገምገም በጣም ከባድ ነውና አሉባልታዎችን ትተን ለኢትዮጵያ አገራችንን የሚበጀን ዛሬ መርጠን መያዝ አለብን። በተረፈ ከመዋሸት ትንሽ ብትሆንም ታሪክ መስራት ጠቃሚ ነው እላለው። በፐሮፓጋንዳና በወሬ አንጠመድ

ማህደር ነኝ

Leave a Reply