(ኢ.ኤም.ኤፍ) ማሕበረ ቅዱሳን አባላትን በ”አሸባሪነት” የፈረጀው የፓትርያርኩ ቡድን ከተሸነፈበት ምክንያት አንደኛው የማህበሩ አባላት በተግባር የሰሯቸው ተግባራት እንደሆኑ ብዙዎች መስክረዋል:: ማሕበረ ቅዱሳን “የአሸባሪዎች ስብስብ” ተብሎ ከተነቀፈ በኋላ ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ሙሉ ለሙሉ በመቃወም የፓትርያርኩን አቋም ማስቀየሩ የሚታወስ ነው:: ማህበሩ በሌሎች ዘንድ ከበሬታን ሊያገኝ ከቻለባቸው ምክንያቶች መካከል ዋነኞቹ ለሌላ እምነት ተከታዮች የሚሰጠው ሚዛናዊ አስተያየት, የኢትዮጵያ ቅርስ እንዲጠበቅ ማድረጉ, የተረሱ ገዳማት እና አብያተ ክርስቲያናትን መልሶ ማቋቋም መቻሉ እና ረዳት ያጡ አባቶችን መርዳቱ መሆኑን ብዙዎች ይስማሙበታል::

በማህበረ ቅዱሣን የተመራው 80 አውቶቢስ ምዕመናን ይዞ ከአዲስ አበባ ዛሬ ማለዳ ተነስቶ ደብረ ሊባኖስ የደረሰው የሐዊረ ሕይወት ጉባኤ ገፅታ ይህንን ይመስላል

ከዚህም በተጨማሪ የቅርሥ አጠባበቅን በተመለከተ ትምህርታዊ ስልጠናዎችን ያደርጋል:: እንደዛሬው አይነት ጉባኤዎችን እያስተባበረ በማዘጋጀት እውን ያደርጋል:: በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣት አባላቱን በአንድ ግዜ በማስተባበር የገንዘብ ማሰባሰቢያ እያደረገ አብያተ ክርስቲያናት ይገነባል:: በአሁኑ ወቅት ከሚሊዮን አልፎ በቢልዮን የሚቆጠር ቅርስ አፍርቷል:: ይህ አይነቱ እንቅስቃኤ እና አካሄዱ ነው ታዲያ በመንግስትም ሆነ በፓትርያርኩ ዘንድ ያልተወደደው:: የዛሬው የኢ.ኤም.ኤፍ ዘገባ ዋና ምክንያትም ማሕበሩ በመንግስት እና በፓትርያርኩ ደጋፊዎች የደረሰበትን ፈተና አልፎ ለዚህ መብቃቱን ለማብሰር ጭምር ነው::

ከጥቂት ወራት በፊት በፓትርያኩ አማካኝነት እንዲፈርስ ቢጠየቅም ተቃውሞውን ተቋቁሞ ….ካለፈው ውዝግብ በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ ያተባበረው የሐዊረ ህይወት ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን በተለይ ለኢ.ኤም.ኤፍ የደረሰው ዘገባ ያስረዳል:: እንደዘገባው ከሆነ በማሕበረ ቅዱሳን የተመራው እና ዛሬ ታኅሣሥ 12 ቀን 2007 ዓ.ም. በደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም የሚያካሔደውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ በመከናወን ላይ ነው::
ቀደም ሲል የተከናወነው የትኬት ሽያጭ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ 80 አውቶብስ ሙሉ ምእመናን ወደ ደብረ ሊባኖስ ሲያመራ ሁሉም በመንፈሳዊ ዝማሬ ነበር አዲስ አበባን ለቀው ደብረ ሊባኖስ የደረሱት:: የማህበሩ አባላት ስርአተ ቤተ ክርስትያን የሚያዘውን አለባበስ ስለሚከተሉ ሴቱም ሆነ ወንዱ ነጭ ለብሰው ሲታዩ የአካባቢውን ድባብ ልዩ አድርገውታል::

ዛሬ ይህ ታላቅ የሐዊረ ህይወት ጉባኤ በደብረ ሊባኖስ እየተካሄደ ነው:: እንደቀጠለ ነው ጉባአኤው የሚመራው ብፁዕ አብነ ቀውስጦስና በብፁዕ አብነ ማቲያስ የካናዳው ሊቀ ጳጳስ አማካኝነት ነዉ።

Leave a Reply