Media source: Professor Tekeste Negash … Undated photo

ኤርትራ ራሷን እያወደመች ነው

የኢትዮጵያ ትምህርት ችግሮች ቋንቋና ያለ እቅደ መስፋፋት ናቸው

ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ በስዊድን አገር በኡፕስላ ዩኒቨርሲቲ የዘመናዊ ታሪክ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ ፕሮፌሰሩ በኢትዮጵያትምህርት ላይ ከፍተኛ ምርምሮችን ያደረጉ፣ በመስኩም የታወቁ ምሁር ሲሆኑ ከከዓምናው ጀምሮ በአዲስ አበባዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል ተጋባዥ ፕሮፌሰር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ .. 1947 በአስመራ ከተማተወልደው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአስመራ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጅማ ተከታትለዋል፡፡የመጀመሪያ ድግሪያቸውን ከአስመራ ዩኒቨርሲቲ በህግ አግኝተዋል፡፡ 1972 እስከ 1974 በአስመራ ዩኒቨርሲቲያስተማሩት ፕሮፌሰር ተከስተ፤ በለንደን ዩኒቨርሰቲ ስኩል ኦፍ ኦሪየንታል ኤንድ አፍሪካ ስተዲስማስተርስ ድግሪያላቸውን ያገኙ ሲሆን ዶክትሬታቸውን ከስዊድን አገር ኡፕስላ ዩኒቨርስቲ በታሪክ ትምህርት ሰርተዋል፡፡

የኤርትራን ወቅታዊ ሁኔታ እንዴት ይገልፁታል?

እኔ የኤርትራን ጉዳይ መከታተል ካቆምኩ አስራ ሶስት አመት ሊሆነኝ ነው፡፡ ምክንያቱም ልለው የምችለውን ሁሉብያለሁ፡፡  “Brothers at war” በሚል ከአንድ የኖርዌይ ተወላጅ ጋር በመሆን በፃፍነው መጽሐፍ፤ የኢትዮጵያናየኤርትራ ጦርትነት የወንድማማችነት ጦርነት ነው፤ ችግሩን ለመፍታት ሁለቱ አገሮች ወንድማማችነታቸውን ማመንአለባቸው ብለን ደምድመናል፡፡ ከዛ በኋላ ምንም ሠላም አልተገኘም፤ በኔ አስተያየት የሚገኝም አይመስለኝም፡፡እስከአሁን በኢትዮጵያም ሆነ በኤርትራ ወንድማማችነቱን ማመን ላይ አልተደረሰም፡፡

የሁለቱ አገራት የወደፊት ግንኙነት ምን የሚሆን ይመስልዎታል?

የኤርትራን ጉዳይ ማጥናት የተውኩት ተገድጄ አይደለም፡፡ በአንድ በኩል በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ያሉ ነገሮች በጣም በጎናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ብዙ ለውጥ እየተካሄደ ነው የሚል አቋም ስላለኝ ሲሆን በሌላ በኩል የኤርትራ ጉዳይ አልቆለታልብዬ ስላመንኩ ነው፡፡ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ኤርትራ ራሷን በራሷ እያወደመች ነው፡፡ ኤርትራ ምንም ተስፋ የላትምብዬ አምናለሁ፡፡  ወደ ጥያቄሽ ስመለስየኤርትራና የኢትዮጵያ ሁኔታ እንዴት ይቀጥላል ለሚለው በኔ አስተያየት ከዚህበኋላ ጦርነት አይካሄድም። ኤርትራ ግን የሶማሊያን አይነት የምትሆንበት፣ በአንድ ልትመራ ወደማትችልበት ደረጃልትደርስ ትችላለች ብዬ አምናለሁ፡፡

ከኢሳያስ አፈወርቂ በኋላ ኤርትራ ሶማሊያን ትሆናለች በሚል የሚሰጡ አስተያየቶችን ይቀበላሉ ማለትነው?

አዎ፡፡ ኢሳያስ እስካለ እሱ የፈጠረው ስርዓት ይቀጥላል፡፡ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ አቋም እና የኢትዮጵያ መንግስትየያዙት አቋምም ለዚህ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡ ከኢሳያስ በኋላ ግን የኢኮኖሚ ችግር ብቻ ሳይሆን የብሔር ግጭቶችአሉ፡፡ ቆላማው የኤርትራ ክፍል የራሱ አጀንዳ አለው፤ ደገኞቹ ደግሞ እርስበርሳቸው በጣም የተከፋፈሉ ናቸው፡፡ ይህንመያዝ የሚችለው ኢሳያስ ብቻ ነው፡፡ ከሱ በኋላ አገሪቱን አንድ አድርጐ ወደፊት ሊያራምድ የሚቻል ይመጣል ብዬአላምንም፡፡ የኤርትራ ጥያቄ ለምርጫ በቀረበበት ወቅት ከነበሩ አማራጮች ዋነኞቹ፤ መገንጠል፣ በፌዴሬሽን መቆየት እናአንድነት የሚሉ ነበሩ፡፡ በውድም ይሁን በግድ ሁሉም አማራጮች ተግባራዊ ሆነዋል፡፡ ኤርትራ ከተገነጠለች 23 አመትሊሆናት ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት አንድነት የሚለው አቋም ቅሪት አለ ወይስ ሙሉ በሙሉ ተሸርሽሯል?

የደጋው ኤርትራ ባህል በመሠረቱ ኢትዮጵያዊነቱን እንደያዘ ነው፡፡ ኢሳያስ ስልጣን እንደያዘ በሶስተኛ አመቱ ሆላንድመጥቶ ባደረገው ውይይት፤ እኔም እድሉን አግኝቼ ሰምቼዋለሁ፡፡ እኛ ሠላሳ አመት ሙሉ ታግለን ብዙ ሰው ሞቶብን፣ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ የኤርትራ ህዝብ የከፈልነውን መስዋዕትነት ረስቶ ከኢትዮጵያ ጋር ወዲያ ወዲህ ይላልብሎ ተናገረ፡፡ ኤርትራ ነፃ ከወጣች ጊዜ ጀምሮ እስከ ጦርነቱ ድረስ የኤርትራ ህዝብ ከኢትዮጵያ ተለይተናል የሚል ብዙስሜት አልነበረውም፡፡ ደርግ መሸነፉ ላይ ነበር እንጂ ከኢትዮጵያ ጋር የመለየቱ ብዙ ግንዛቤ አልነበረውም፡፡ ጦርነቱሲጀመር ስሜቱ መቀዛቀዙን መናገር ይችላል፡፡

ሌላው በደጋው ኤርትራ ያለው ትግርኛ ተናጋሪ ከጣሊያን ጊዜ የጀመረ የገዢና የተገዢ ግንኙነት ነበረው፡፡ እኛን ጣልያንነው የገዛን በሚል፣ ትግራይ ያሉትን ትግሪኛ ተናጋሪዎችእናንተ ከአዲግራት፣ ከመቀሌ፣ ከአድዋ የምትመጡ…” የሚልነገር ነበር፡፡ ከጦርነቱ በኋላ የትግራይ ህዝብ የራሱን ማንነት ኢኮኖሚ በማሻሻል ላይ ስለሚገኝ በነዚህ ሁለት ትግሪኛተናጋሪዎች መካከል ያለው ፉክክር ማን ትግሬን ይወክላል የሚል ነው፡፡ ይህ ለጊዜው ችግር ሊፈጥር ይችላል፤ ግን እኔእስከምረዳው ድረስ ኢትዮጵያዊነት ስሜት፣ ባህል፣ አስተሳሰብ አለ የምንል ከሆነ በደጋማው ኤርትራ አሁንም አለ። ከዛደግሞ ከአፋር ጋር ያለውን ትስስር ማየት ይቻላል፡፡ በኤርትራ ያሉ ቢለኖች አገዎች እንደሆኑ አይጠራጠሩም፤ አሁንባለው ሁኔታ ምንም ማድረግ አይችሉም፡፡ ኩናማዎችንም ካየሽ ተመሳሳይ ነው፡፡ ወቅታዊውን የአፍሪካ ቀንድ ሁኔታእንዴት ይገልፁታል? በአፍሪካ ቀንድ የኢትዮጵያ ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ሶማሊያ እና ኢትዮጵያን ካየን፣ ለሁለቱምየሚጠቅማቸው የሶማሊያ አንድ መሆን ነው፡፡ አሁን ያለው ሁለት ሶማሊያ በኔ አስተያየት ረጅም የሚጓዝ አይደለም፡፡ከጥቅም አንፃር ካየነውም፣ ለኢትዮጵያም ሆነ ለሶማሊያ አይጠቅምም፡፡ በኤርትራና በኢትዮጵያ በኩል ስናየው፣ ኤርትራየምትፈልገው ድንበር ሊኖር አይችልም፡፡ ይህን ደግሞ ሁለቱም አገሮች ያውቁታል፡፡

የኤርትራ ሁኔታ ከኢሳያስ በኋላ አዲስ መልክ ይይዛል፡፡ በአዲሱ ሁኔታ የኢትዮጵያ ሚና ምን ሊሆን እንደሚችል በሚገባማጤን ያስፈልጋል፡፡ የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ የኢትዮጵያን ጥቅም ለመጪው ሁለት መቶ ሶስት መቶ አመትሊያራምድ የሚችል ሆኖ መቀረፅ ይገባዋል፡፡

የኢትዮጵያን የፌደራል አወቃቀር እንዴት ያዩታል?

አወቃቀሩ በፌደራል መሆኑ ጥሩ ነው፡፡ በብሔር መሆኑ ግን መጥፎ ነው፡፡ የኢህአዴግ መንግስት ያደረገው ትልቁስህተት ነው፡፡ ፌደራል ስርአት በፊትም የነበረ ነው፡፡ የኢትዮጵያን የኋላ ታሪክ ካየሽ የፌደራል አወቃቀር አዲስአይደለም፡፡ ንጉሠ ነገስት ስንል እኮ ንጉሶች አሉ፡፡ ከበላያቸው ንጉሠነገስት አለ ማለት ነው፡፡ አካባቢያዊ ፌደራሊዝምነበር፡፡

የኤርትራ ህዝብ አሁን ያሉበትን የነፃነት ሁኔታ ከቀድሞው ጋር ሲያስተያዩት ምን ትርጉም ይሰጥዎታል?

እኔ እኮ በመጀመሪያም ኤርትራውያኖች ከማን ነው የሚገነጠሉት የሚል አቋም ነው ያለኝ። ማነው ከማን የሚገነጠለው?የደቡብ ወይም የኦሮሞ ህዝቦች እንገነጠላለን ቢሉ ኖሮ ምክንያት ነበራቸው፡፡ የኤርትራ የነፃነት ጥያቄ በተነሳበት ወቅትኤርትራውያኑና ከላይ የጠቀስኳቸው ህዝቦች በኢትዮጵያ ውስጥ ያገኙትን እድል (Comparative advantage) ስናይ፣ኤርትራውያኑ በጣም ተጠቃሚ ነበሩ፡፡ (በጣሊያን፣ በእንግሊዝ፣ በፌዴሬሽኑ ዘመን) 1960ዎቹ የአዲስ አበባሀብታሞቹ እነሱ ነበሩ። በትምህርት መስክ ሃያ አምስት በመቶ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተማሪዎች ኤርትራውያንነበሩ። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችንም ካየሽ 25 በመቶ የሚሆኑት ኤርትራውያን ነበሩ፡፡ ከተማረው ሰላሳ አምስትበመቶው ክፍል ኤርትራውያን ነበሩ፡፡

ይህን እድል ያገኙ ሰዎች ከኢትዮጵያ እንገነጠላለን ሲሉ ምክንያቱን ለማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡ ምንም ምክንያትአልነበራቸው፡፡ ለነፃነት የተደረገው እንቅስቃሴ 30 አመት ቢፈጅም ስልሳ ሺህ ሰው ቢሞትም በቂ ምክንያትአልነበረውም። የኔ ጥናት የጣልያን ቅኝ አገዛዝ በኤርትራ የሚል ነው። እንዲገባኝ ሞክሬያለሁ፡፡ ኤርትራ ከኢትዮጵያመገንጠል እንዳለበት የሚያሳይ ምንም ነጥብ አላገኘሁም፡፡ ነፃ ወጣን አሉ፡፡ ሁለት አመት ሳይቆዩ እኛ የታገልነውለነፃነት ብቻ አይደለም፤ የኛ ዕድል ከኢትዮጵያ ጋር ነው ማለት ጀመሩ፡፡ ይህን የሚሉት ተገደው ነው፤ ምክንያቱምየኤርትራ ኢኮኖሚ ከኢትዮጵያ ተገንጥሎ በራሱ ሊቆም የሚችል አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ልዩ አገር ነች፤ ነፃነቷን ጠብቃየቆየች አገር ናት፡፡

የኤርትራ ቴሌቪዥን በቅርቡ “Ancient Eritreans” (የጥንት ኤርትራውያን) የሚል ዶክመንተሪ አቅርቦነበር፡፡ አይተውታል?

(ረጅም ሳቅ) አላየሁትም፡፡ ግን ምንም አዲስ ነገር አይፈጥርም፡፡ ወጣቶቹ ኢትዮጵያን አያውቋትም፤ ነገር ግን መንግስትየሚያደርገው አንድ ነገር ነው፣ ህዝቡ የሚያስበው ሌላ ነገር ነው፡፡

መንግስት በቴሌቪዥን የሚየሳየውና ህዝቡ የሚመኘውና የሚያስበው ሌላ ነው፡፡ እስከቅርብ ጊዜ የኤርትራ ኦርቶዶክስቤተክርስቲያን ከኢትዮጵያ ብትለያይም በድብቅ ወጣቶቻቸውን ለትምህርት ወደ ቤጌምድር (ጐንደር) ይልኩ ነበር፡፡የኢሳያስን መረጃ በማየት ድምዳሜ ላይ መድረስ አይቻልም፡፡ ኤርትራዊውን ማን አገኘው፡፡ የተለየን ነን የሚል አቋምየት ነው ያለው? በኤርትራ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ምን ያህል አለ ለሚለው መልስ ለማግኘት ድንበሩ መፍረስ አለበት፡፡ለሁለቱ ህዝቦች መፍትሔ የሚሆነው በኤርትራ በኩል እየተጠየቀ ያለው ድንበር ሲሰመር ሳይሆን ከደርግ ሽንፈት በኋላየተሰመረው መስመር ሲፈርስ ነው፡፡

ትናንት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቋንቋ፣ እውቀት እና የጋራ ህልውና በሚል የውይይት መነሻ ጥናትአቅርበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ትምህርት ላይ ጥናቶችን አድርገዋል፡፡ ዕይታዋ ምንድን ነው?

ዋና ጥናቴ እሱ ነው፡፡ ትምህርት በጣም ተዳክሟል፡፡ የተዳከመው በሁለት ምክንያት ነው ብዬ አስቀምጣለሁ፡፡ አንዱያለዕቅድ መስፋፋቱ ነው። የሚፈለጉ ህንፃዎች፣ አስተማሪዎች፣ መፃሕፍቶች ሳይሟሉ እንዲሁ ሠፍቷል፡፡ ሌላው ዋነኛምክንያት የቋንቋ ጉዳይ ነው፡፡ እንግሊዝኛ ቋንቋ አያዋጣንም፡፡ በራስ ቋንቋ መማር የህልውናና የመበት ጥያቄ ነው፡፡

ዜግነትዎ ከየትኛው ነው?

ስዊድናዊ ነኝ፡፡

www. addisadmassnews.com

Leave a Reply