ቴዎድሮስ ታደሰ
ሳዱላዬ ነይ አልቦሽን አርገሽ አልቦሽን አርገሽ
በጥልፉ ቀሚስ አምረሽ ተውበሽ
አምረሽ ተውበሽ !

የሚል ድንቅ ዘፈን አለው ። ሳዱላ የልጅ ፣-አገረድነት ምልክት ሲሆን ፣ ልጃገረዶች ( ቆንጆዎች ) ባል እስቲ ( ኪ ) ያገቡ ድረስ ፣ ከማኸል ራስ የጠጉር ( ብግዕዝ ጸጉር ) አሻራ በሚበቅልበት ላይ ያለውን ጠጉር ፣ በብር ( ጠገራ ብር ቅርጥ ወይም ቅርጽ ) ወይም ክበብ ዕይነት የሚላጩት ሳዱላ ይባላል ። ይህም ልጅት ሳዱላ ተላጨች ፣ ወይም ተቀነበበች ፣ ወይም ተቦቀረች ይባላል ። ታዲያ ወሴፋውና ወሬዛው እርስ በእርሳቸው የሚግባቡበት ባህላዊ ምልክት ሲሆን ፣ ባጭሩ አሁን በዘመነኛው ስርዓት ባለትዳሮችን ካላገቡ ለመለየት ይጠቅም ዘንድ የጋብቻ ቀለበት ከማድረግ ጋ አንድ አይነት ነገር ነው ማለት ነው ።

ዛሬ ስለ ሳዱላ ያወራሁት ያለ ነገርም አይደለም ። እንደው ባጋጣሚ ከአንድ ሰው ጋ ( ከልጅነት እስከ እውቀት አብሮኝ ካደገ ሰው ጋ ) እግር ጥሎኝ አንድ ቦታ ተገናኝቼ ነበር ። ታዲያ ይሄ ሰው የወያኔን ስርዓት አምርሮ የሚጠላና ፣ የምጥፋቸው ጥሁፎች እጅግ የሚማረኩት እና አንጀቱን የሚያርሱት እንደሆኑ ከነገረኝ በሁዋላ አንድ ጥያቄ ጠየቀኝ ።

ሄኖክ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ፣ በይበልጥም በእስላም ኦሮሞዎች ላይ ወያኔ እያደረሰ ያለው በደል ፣ ከንግግሩ ገትቼ ከቻለ ወያኔን በጥሬው ከሚጠራው ከነመፍቻው ይጠራቸው ዘንድ ጠየኩት ። “መፍቻው ምንድን/” ነው አለኝ “አታውቅም እንዴ! ወያኔ የሚለው ከበደላቸው አንጻር በቂ ሆኖ ስላላገኘነው ከፊት ገላጭ ጨምረንለታል” አልኩት ። “እኮ ገላጩ ምንድን ነው!?” አለኝ ? “የትግሬ -ወያኔ ( ምክንያቱም የተሻለ ሆኖ ስላገኘነው ብቻ ሳይሆን ፣ እንዲያስተላልፍ የምንፈልገውም ጠጣር መልዕክት ስለያዘ )” ። ወዲያው ተስማማ እና ንግግሩን ቀጠለ ።
የትግሬ ወያኔ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለው በደል ይህ ነው የሚባል አይደለም ፣ በተለይም በኦሮሞ ብሔሮች ላይ ( በይበልጥ ደሞ ሙስሊም ኦሮሞዎች ላይ ) ታዲያ ይሄ የተበዳይነት ስሜት ይህ ነው የማይባል ቁጥር ያለው የኦሮሞ ወጣት ኢትዮጵያዊ አይደለንም የሚልበት ደረጃ ላይ ከመድረስ አልፎ ፣ በአደባባይ ኢ- አካልነቱን እየገለጸ ይገኛል ። ቀጠለ ” ልክ ነው ለማለት ፈልጌም አይደለም ግን ጃዋር መሐመድ ከዚህ አይነት አመለካከት ውስጥ የወጣ ነው ፣ የኦነግ አመራሮች ከእንደዚህ አይነት የ ሁልጊዜ ተጨቁዋኝነት አመለካከት ውስጥ ነው የወጡት ፣ ይሄ ነገር ሳስበው በጣም ያስፈራኛል ፣ የሀገሬ የወደፊት ዕጣ ምን እንደሚመስል ሳስበው በጣም ይጨንቀኛል ፣ አብዛኛው በሚባል መልኩ ( አብዛኛው የኦሮሞ ልጅ ከኢትዮጵያ መገንጠል ይፈልጋል ፣ በፊት ለፊት ስለ አንድነት የምሰብቀው እንኩዋ ውስጥ ውስጡን ስርዓቱ ላይ አቂሞዋል ፣ ስለ ቀደመው ስርዓትም ያለው ጥላቻ ይሄ ነው የሚባል አይደለም ፣ አንዳንድ አማራ ተኮር የሆኑ ድርጅቶች እና ማራዊነት አቀንቃኞች ( በነገራችን ላይ ሄኖክ አንተንም ከዛ ውስጥ የሚመድቡህ ጥቂት አይደሉም ) እያሰራጩ ያለው የንቀት ፖለቲካ ሊያበቃ የሚችለው እኛም እንደ ዔርትራ ስንገነጠል ነው ይላሉ ፣ ስለ መልካ- ምድራዊ አቀማመጡም ሆነ ስለ ሀሳባቻው ይቻላልነት አስበው የሚያውቁም አይመስለኝም ፣ ግን በኢትዮጵያዊነት የተሰላቹ ይመስለኛል እና ይሄ ያሳስበኛል አለኝ ።

ወዳጄ ያነሳው ነጥብ ሃሳቤን አንድ የታሪክ ጥግ ሄዶ ወዘተው ። እ ኤ አ በ አቶ ቫን ቢስ ማርክ ፊት አውራሪነት ከ 1884 እስከ 1885 አፍሪካን ለመቀራመት ባወጡት ጥናት መሰረት አውሮጳውያን በወቅቱ በአፍሪካ እምቅ የተፈጥሮ በረከት ላይ ከመጎምዥታቸው አንጻር ያወጡት አፍሪካን በሃገራቶች የመከፋፈል ስርዓት አንድም ቅድመ ጥናት ያልተደረገበት እና ፍጹም ቅርጫዊ እንደነበር ታሪክ ይዘክራል ።

በአውሮፓውያኖች በወቅቱ የተደረጉት የሃገራቱ የክልል አከላከል እና ወስንተኛ ችካሎች ካለ ምንም ቅድመ እውቀት የተደረጉ ነበሩ ። ” The key consideration was to prevent conflict among Europeans over the African territories (as the memories of the European wars of the
18th-19th century were still alive ” አውሮፓዊያኑ አፍሪካን ለመቀራመት እጅግ ተቻኩለው ስለነበረ ፣ ቀድመው ወደ አፍሪካ ከላኩዋቸው አሳሾች (explorers) ፣ የመልካምድር ጥናት አጥኝዎች (geographers) ፣ ሚስዮናዎች ( missionaries) የሚመጣውን መልስ እንኩዋ ሊጠብቁ ጊዜ አልነበራቸውም ። በወቅቱ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት ሎርድ ሴልስ-በርይ ስለ አፍሪካ ቅርሚያ እንዲህ ነበር ያሉት ” we have been engaged in drawing lines upon maps where no white man’s feet have ever tord; we have been giving away mountains and rivers and lakes to each other, only hindered by the small impediment that we never knew exactly where the mountains and rivers and lakes were” ” ከዚህ ቀደም አንድም ነጭ ባልረገጣቸው የአፍሪቃ መልካ ምድሮች ላይ የክፍፍል መስመር በማስመር ተጠምደን ነበር ፣ ተራሮችንን፣ ወንዞችን እና ሃይቆችን ስንከፋፈል ነበር ፣ ታዲያ ብቸኛ ማነቆ የነበረው ፣ ወንዞቹ ፣ ተራሮቹ እና ሃይቆቹ በትክክል የት እንዳሉ አናውቅም ነበር ” ብለዋል ። ይሄ የ-በዘፈቀደኝ ወራራ እና ቅራሞት ያመጣቸው ጣጣዎች ታዲያ እጅግ ብዙ ነበሩ ። እንደ ምሳሌ የዛሬዋ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ( ያያኔው ኮንጎ ፍሪ ስቴት ) ከ ቤልጅየሙ ንጉስ ልዮፖልድ ግዛት አንጻር በጣም ትልቅ የነበረበት ምክንያት የ ባርያ ንግድ እና ነጻ ንግድ ይካሄድበት ቦታ ስለነበር ነው ። በተጨማሪም በጊዜው የነበሩት አውሮፓውያን ወራሪዎች የወረሩት ቦታ ቅድመ ጥናት ያልተደረገበት ስለነበረ ተደጋጋሚ ፣ የቦታ እንካ ! ውሰድ ! መልስ! አምጣ! ጭቅጭቅ እና መገባበዝ ያመጣውም ጥፋት ይህ ነው የሚባል አልነበረም ። ለምሣሌ በ ወቅቱ በ ኮንጎ ነጻ ሀገር ( ኮንጎ ፍሪ ስቴት ( ነጻ ባትሆንም ቅሉ ) የነበረው ካታንጋን ጨምሮ የማስተዳደር ሁናቴና የካታንጋን በተፈጥሮ ሀብት መደለብ ( መበልጸግ) ተከትሎ በ ቤልጅየሙ ንጉስ ልዮፖልድ ጥያቄ ወደ ቤልጅየም ግዛት ሀገር መጠቃለል ለዚህም ልዮፖልድ ለ ኮንጎ ፍሪ ስቴት ናሪ ኪዉሉን Niari-Kwilu መስጠት ሊጠቀሱ የሚችሉ ጉዳዮች ናቸው ። ታዲያ ይሄ በወራሪዎች ጊዜ በአቦ ሠጥ የተካለሉት የአፍሪካ ሀገሮች ፣ አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሃገራት ነጻነታቸውን ካገኙ ወዲያ እናዚያ ባህላዊ መሰረት የሌላቸውን አከላለሎች ባለመቀበል ነጻ በወጡ የአፍሪቃ ሀገሮች አዲስ የድንበር ጸብ አፍሪካ አሁን ለደረሰችበት ውጥንቅጡ የወጣ የማያልቅ ነጻ የመወጣት እና ነጻ የማውጣት ትግል ውስጥ እንድትገባ አድርጎዋታል ። ታዲያ ሀገራችን ኢትዮጵያም ወራሪውን የጣልያን ኃይል መክታ ( እንደውም አንበርክካ ) ብትመልስም ፣ ከጦርነቱ በፊት በንጉሥ ምኒልክ የክተት ሰራዊት ጥሪ ላይ አልሳተፍም ያሉ አንዳንድ ሃገረ ግዛቶች ላይ የወሰዱት እርምጃ ( በግሌ በጡት መቁረጡ እና መሰል አፈ ታሪኮች አልስማማም ) ዛሬ ከሚገባው በላይ ተራግቦና ፣ ይበልጡንም ጎልብቶ ወይም ( scale up ) ተደርጎ ፣ በብሄሮች ፣ በህዝቦች እና በ ክልላት መሃከል ያለውን ቂመኝነት እንዲወልድ ምክንያት ሆኖዋል ። በተጨማሪም አውሮፓውያኖቹ በቅድመ ወራራው ጊዜ ሱማሊያን ስያካልሉ ባደረጉት ስህተት እንደምሳሌ Somali tribes were split between three different European colonies, while Ethiopia also got a slice. As a result, nowadays besides Somalia a large portion of Somalis occupy Northern Kenya, the Ogaden region in Ethiopia, as well as Eritrea and Djibouti. Three long-lasting wars in our sample have (partly at least) been driven by the desire of Somalis in Ethiopia, Djibouti, and Kenya to become part of Somalia. መሆኑን እንረዳለን ። የ ኢትዮ -ዔርትራ ጦርነትም ከዚህ ፈቅ የሚል አይደለም ፣ ይበልጡንም አብዛኛው የአፍሪካ ሃገራት ነጻ በወጡበት ሰሞን የዔርትራ ወጣቶች ምንም ታሪካዊ እንድምታ በሌለው ሁኔታ ፣ የዔርትራን ከኢትዮጵያ ነጻ የማውጣት ጥያቄና ፣ የብረት ትግሉን መጀመርም ከዚሁ ጋ ተያይዞ የሚታይ ነው ። ለምሳሌ ጋምቢያ ሴነጋልን ደቡና ሰሜን በመክፈሉዋ ከማዕከላዊ መንግስቱ የራቀው አካል የራስን በራስ ማስተዳደር ጥያቄ ማቅረቡ የፈጠረው ግጭት ፣ በማሊና ቦርኪናፋሶ መሃከል በ አጋሸር ሰርጥ ( Agacher Strip) ምክንያት የተደረጉ ግጭቶች እና ወዘተ የዚህ ሁሉ ስህተተኛ የወራሪዎች የ ካርታ መስመሮች ናቸው ።

ታዲያ ወደ ኢትዮጵያ ኦሮሞች ስመጣ አንድም ታሪካዊ ስሜት የሚሰጥ ምክንያት አጣሁ ፣ የየጁን ጉልበት ፣ የደብረታቦሩን ጉግሳን ( የ ከለቻው ጌታ ) እና ወዘተ ስመለከት አንድም ታሪካዊ ኩነት አጣሁበት። አንዳንዴ ኤርትራን እንደ ምሳሌ በመውሰድ የይቻላል ትምህርት የቀሰምን ፣ ሳዱላዎች መሆን ያማረን ቅዤታሞች እና ብዥታሞች የሆን ይመስለኛል ። አዎ አንዳንዴ ኦሮሚያን ለመገንጠል ማሰብ ሳዱላ ለመሆን ማሰብ ይመስለኛል ፣ የትግሬ ወያኔ እና ፈጣሪዎቻቸው ዔርትራውያኖች በቀደዱት ቦይ ዝም ብሎ መጉዋዝ ይመስለኛል ፣ ከታሪክ መማር አለመቻል ይመስለኛል ፣ አቅምን አለማወቅ ይመስለኛል ፣ ሀገርን ከመሃል በመቀንበብ ነጻ ለመሆን ማሰብ አውሬነት ይመስለኛል ፣ ነጻነት ጭንቅላት ውስጥ እንጂ መልካምድር ላይ አለመኖሩን አለማወቅ ይመስለኛል ፣ ነጻነት ፈልገው የተገነጠሉት የ ቀይባህር ውሃ ሲበላቸው እንጂ ሲያድጉ አላየንም ፣ ምክንያቱም ተገነጠሉ እንጂ ነጻ አልሆኑም ! አንዳንዴ ኤርትራ ጥሩ መማሪያ ትሆነን ዘንድ ነው የተገነጠለችው እላለሁ ፣ ከሚያዙ ከሚነዙባት ሀገር ተገንጥለው ዛሬ ማር እየቆረጡ እንዳልሆነ እያየን ነው ። አክሊሉ ሀብተወልድ በሕይወት ቢኖሩ ” ልጆቼ ይህንን መከራ እንዳታዩ ስል ነበር የተንገላታሁት ” ብለው አባታዊ አስተያየታቸውን በሰጡዋቸው ነበር ። ኦሮምያን ሳስብ ግን ብዙ ትዝ የሚሉኝ ፣ የምሞትላቸው ውብ ትዝታዎች አሉኝ ፣ በተጨማሪም ሊገነጥሉ የሚፈልጉት ኦርሞነት ላይ ሼር አለኝ ! ሳዱላነት አያምርባችሁም ! አልኩት ! ሰማኝ ግን ይሰማማ አይሰማማ አላውቅም ! በእውነት አላውቅም ግን ብዙ የሚያስፈሩ ሆዳምነቶች ፣ ብዙ የሚያስፈሩ ጥቁርነቶች ፣ ብዙ የሚያስፈሩ ማሃይምነቶች ይታዩኛል ፣ ይሸቱኛል ፣ በጣም ብዙ !

Leave a Reply