December 22nd, 2014 

ገዢው ፓርቲ ሕወሃት/ኢሕአዴግ የእምነት ነጻነትን በመጋፋት ፣ ታቦት ቢወጣበትና የጥቅምት በዓል በሚከበርበት በባህር ዳር የመስቀል አደባባይ “ልማት” በሚል ስም ለባለሃብቶች ቦታዎች ሊሰጥ ማሰቡን ተከትሎ ሕዝቡ ለአስተዳደሩ ብሶቱን በደብዳቤ ለማስገባት፣ በቦታው ሄዱ ለማነጋገር ቢሞክር፣ ለሕዝብ ጥያቄ ደንታ የሌላቸው የሕወሃት/ኢሕአዴግ ባለስልጣናት፣ ቦታውን ለባላሃብቶች ለመስጠት በመወሰናቸው፣ ሕዝቡ የእምነት ነጻነቱን ለማስከበር ባለስልጣናት ዉሳኔያቸዉን እንዲቀለብሱ ለማድረግ፣ በራሱ አነሳሽነት ፣ በሺሆች በመሆን ሰለፍ መዉጣቱ ይታወቃል።

ሆኖም በሰላም የወጣው ሕዝብ ላይ ተኩስ የከፈቱት ደህንነቶች ከአምስት ያላነሱ ዜጎችን የገደኩ ሲሆን፣ በርካታዎችን አቁስለዋል። በአገሪቷ በሙሉ መዋቅር ያለው አንድነትለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፣ በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎችን የሚያካድ እንደሆነ የሕዝብ ግንኑነት ክፍላ ሃላፊው አቶ አስራት አብራሃም የጌልጹ ሲሆን፣ ሰላማዊ ሰልፉም የሚጀመረው በባህር ዳር ከተማ እንደሆነ ለማወቅ ትችሏል። “ የመጀመሪያው ሰላማዊ ሰልፍ የወንድሞቻችንና የእህቶቻቸን ድም ባለፈው ሳምንተ በፈሰሰባት ባህርዳር ከተማ ይሆናል” ያሉት አቶ አስራት ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምጹንም እንደሚያሰማ ያላቸውም እምነት ገልጸዋል።

በባህር ድር የሚደረገውን የሚሊዮሞች ድምጽ ሰልፍ መኢአድ ከአንድነት ጋር በጋራ የሚሰራ፣ የቅድመ ዉህደት ስምምነትም ያደረገ እንደመሆኑ ይቀላቀላል የሚል እምነት ያለ ሲሆን፣ በሰማያዊ በኩል ግን ብዙ የሚታወቅ ነገር የለም።

የአንድነት ፓርቲ ከመኢአድ ጋር በመተባበር ከአዲስ አበባ ዉጭ ከተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች መካከል በአይነቱም ሆነ ብብዛት ደማቅ ሰላማዊ ስለፍ በባህር ዳር ማድረጉ ይታወሳል። በወቅቱ ወደ ሶስት መቶ ሺህ ከሚጠጋ የከተማዋ ነዋሪ ወደ 80 ሺህ የሚሆነው በሰልፉ መገኘቱ የሚታወስ ነው። በወቅቱ የተደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማስታወስ የሚከተለውን ይመልከቱ

Leave a Reply