አፍሪቃ

                 የአልሸባብ ከፍተኛ መሪ እንደሆነ የሚነገርለት ዛካሪያ ኢስማይል አህመድ ሔርሲ ሶማሊያ ውስጥ መማረኩን ዛሬ አንድ የሶማሊያ የደኅንነት ሹም አስታወቁ።ዘካሪያን ይዞ ላቀረበ አለያም ያለበትን ለጠቆመ 3 ሚሊዮን ዶላር ወሮታ እንደሚከፈል ቀደም ሲል ተጠቅሶ ነበር። ከአልሸባብከፍተኛ አመራር አንዱ የሆነው ዛካሪያ ኢስማይል ሶማሊያ ጌዶ ውስጥ መያዙን ይፋ ያደረጉት የደኅንነት ሹም ለጋዜጠኞችመግለጫ ለመስጠት ፈቃድ ስለሌላቸው ስማቸው እንዳይጠቀስ መፈለጋቸውም ተዘግቧል። ባለሥልጣኑ ዛካሪያ ኢስማይልሊያዝ የቻለው በዩናይትድ ስቴትስ የጦር አውሮፕላን ጥቃት ከተገደለው የአሸባብ ከፍተኛ መሪ አህመድ ጉዳኔ ታማኞች ጋርበመቃረኑ ሳይሆን እንዳልቀረ ግምታቸውን ገልጠዋል። የአሸባብ ቡድን እስካሁን በዚህ ላይ ምላሽ አልሰጠም። የዩናይትድስቴትስ መንግሥት ከዛሬ 2 ዓመት በፊት ዛካሪያ ኢስማይልን ጨምሮ 8 የአልሸባብ ባለሥልጣናት የሚገኙበትን ለጠቆመ 33ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገብቶ ነበር። አልሸባብ የተሰኘው የሶማሊያ ታጣቂ ቡድን መዲና ሞቃዲሾ ውስጥ የነበረውንይዞታ ከማጣቱም ባሻገር የሶማሊያ እና የኬንያ ስጋት በመሆን ተወስኗል ሲል አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ልደት አበበ

Leave a Reply