ትናንት ኰሓ ከተማ አለፍ ብለህ የምትገኘው እግሪ ሓሪባ ለመጀመርያ ግዜ ጎበኘሁ። ሁኔታው ልብ ይሰብራል። ህዝቡን ከልቡ ለሚወድ ሰው ሁኔታው አይቶ ልቡ ደም ታነባለች።እና እንዲህ የሚል ድምዳሜ ደርሻለሁ። ህወሓት መፈጠር አልነበረባትም! ለትግራይ ህዝብ ሲባል ህወሓት የምትባል ድርጅት በ1967 መረገዝ አልነበረባትም። እንደ አጋጣሚ ከተረገዘች ደግም በባህላዊ ይሁን በህከምና ሽሉ ከትግራይ ህዝብ ማህፀን በእንጭጩ ማስወረድ (abortion) መደረግ በተገባ ነበር።

ባልተከሰተ ነገር በቁጭት መነጋገሩ ይቆይልንና በተጨባጭ ነገር እስኪ እንነጋገር። በነገራችን ላይ ከዛ በፊት ከጥቂት ዓመታት,በፊት ከአብርሃ ደስታ ጋር በሃሳብ የተጋጨንበትና አሁን የኔ ስህተት መሆኑ የገባኝ አንድ ነገር ልንገራቹህ። ይህ ሃሳብ በፌስቡክም ለቆት ነበር። እኔና አብርሃ የተከራከርነው ግን በዩንቨርሲቲ ግቢ ካፍቴርያ ሻይ እየጠጣን ነው። አንድ ካድሬ አስተማሪ ጓደኛዬ አብርሃ ደስታ ሲያልፍ ጠራውና አብረን ሻይ እየጠጣን ማውራት ጀመርን ።ወሬያችን ስለአስተዳደራዊ ግድፈቶች ነበር። ጥሩ እየተግባባን ቆይተን ድንገት አብርሃ “እነ መለስ በረሃ የወጡት እኮ ለስልጣን ሲሉ እንጂ ለትግራይ ህዝብ ሲሉ አይደለም ” አለ። ካድሬው አስተማሪ ረጋ,ብሎ ለማስረዳት ሲሞክር ገረመኝ። እንደዎትሮው ስሜታዊ አለመሆኑ ነገሩ ያመነበት መስሎ ታየኝ። እኔ በበኩሌ ከረር ባለመልኩ የአብርሃን ሀሳብ ተቃወምኩት። ወያኔዎች የተበላሹት ስልጣን,ከያዙ በኋላ,ነው መጀመርያ,ትምህርታቸው አቋርጠው በረሀ እንዲወጡ ያደረጋቸው ግን ያኔ የነበረው ጨቋኝ ስርዓትና ያለህዝብ ፍላጎት ስልጣን የያዘ ወታደራዊ መንግስት ነው ብዬ ተናገርኩ። ነገሩ አሁን ከፃፍኩት በላይ ስሜታዊ ሁኜ የተናገርኩት አብረሀ ደስታ በፌስቡክ ፅሁፉ ካወቅኩት ጀምሮ ,የትግራይ,ህዝብ ብርሀን ነውና የሱ በእምነት ደረጃ ትንሽ መሳሳት በምናደርገው ትግል ዋጋ ያስከፍለናል ብዬ በሌላ አገላለፅ ለሱ ካለኝ ክብር የተነሳ ነው።

አሁን መልሼ ሳስበው ግን የአብርሃ ደስታ ሀሳብ ትክክል መሆኑ ለማመን ተገድጃለሁ። ሁለተኛ ወያኔ ነን ብለው ራሳቸው,የሰየሙ ተማሪዎች በረሃ,የወጡት ለትግራይ ህዝብ አንድም ለኢትዮጵያ ህዝብ ብለው አልነበረም። ስለዚህ የአስራ ሰባት ዓመት ትግሉ አስፈላጊ አልነበረም። ደርግ በስልጣኑ ከመጣህበት ይገድለሀል። ወያኔዎች ወደ ወንበራቸው ከተመለከትክ ይገድሉሀል። ፍትህ በማስፈኑና ሙስናን በመቆጣጠር በንፅፅር ደርግ ይሻላል። የትና የት! ደርግ በሀገር ጉዳይ አይደራደርም። ህወሓት በሀገርና,በህዝብ ጉዳይ የገንዘብ,ትርፍ,የሚያገኝበት,ከሆነ ይደራደራል። ደርግ የተማረ ሰው የሚያግዘው,ቢያገኝ እሱ ቢገዛ,ይሻል,ነበር።

ወደ ዋናው ጉዳይ ስገባ የጣብያ እግሪ ሓሪባ ህዝብ በአንድ ድምፅ ወደ ከተማ መግባት አንፈልግም በማለቱ በመንግስት አሰቃቂ ብቀላ ተካሂዶበታል። ት /ቤቶች ተዘግተዋል። ማንኛውም የመንግስት መሰረታዊ አገልግሎቶች ከተቋረጡ ድፍን ዓመት አለፋቸው። ህፃናቶችና ጎልማሳዎች መማር አቋርጠዋል። የነበረው ጤና,ጣብያ ተዘግቶዋል። እግሪሓሪባ,ውስጥ ያሉት ህፃኖቶች በተለይ ካለፈው ዓመት ወዲህ የተወለዱ ምንም ዓይነት ክትባት አያውቁም። ውድ አንባቢዎቼ እየነገርኳቹህ ያለሁት ትላንት ራሴ ህጄ ያረጋገጥኩትና በሃያ አንደኛው ክፍለዘመን በኢትዮጵያ: ትግራይ: እንደርታ ወረዳ: በህወሓት ምክንያት እየተፈፀመ ያለ ግፍ እንጂ ባለፉት ክፍለዘመናት በነገስታት የተፈፀመ ታሪክ አይደለም። እናቶች ህክምና መውለድ ባለመቻላቸው እየሞቱ ያሉበት ሁኔታ ነው,ያለው። ባየሁት ልብ የሚሰብር ሁኔታ እስካሁን አንገቴን እንደደፋሁ ነው። በሌሎች የትግራይ አካባቢዎች ተመሳሳይ ሁኔታ ሲያጋጥም ወያኔ እንዴት እንደሚፈታው አውቃለሁ። አሁን ህወሓት በእንደርታ ህዝብ ላይ የባሰ ንቀትና ጥላቻ እንዳላቸው ለመገንዘብ ችያለሁ። እናንተ የህወሓት አመራሮች የሂትለር አምሳያዎች ሆይ የእንደርታ ህዝብ የቀደማይ ወያኔ መነሻ መሆኑን የረሳቹሁት መሰለኝ። አንገቱ ደፍቶ ይቆይና አንዴ ከተነሳ,ግን በዋዛ,እንደማይለቃቹህ የገባቹህ አይመስለኝም። የሰብዓ እንደርታ ህዝብ የዋህ እንጂ ሞኝ አይደለም!

ባለፈው ግዜ በእግሪ ሓሪባ የመንግስት ፀጥታ አስከባሪዎች ባለመኖራቸው ከሌሎች አካባቢ ሌቦችና ዘራፊዎች ገብተው ነበር። የእግሪ ሓሪባ ህዝብ ግን በሚያስደንቅ ሁኔታ ዘራፊዎቹ በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ በዱላ እየዠለጠ እግራቸው ስባብሮ እያነከሱ ወደ ኰሗ ከዛ ወደ መጡበት እንዲመለሱ አድርገዋል። ህዝቡ ዘራፊዎቹን ለመንግስት ያላስረከበው ከላይ እንደገለፅኩት ከመንግስት ጋ,የከረረ ጥል ውስጥ ስላለ ነው።

ጋዜጠኞቻችን ስለነዚህ ህዝቦች ለአንድ ቀን እንኳ ለማቅረብ ተስኖአቸው,ለአርባኛው ዓመት ግን እየዘፈኑና እየጨፈሩ ነው። ዝቃጮች። አባይ ወልዱ የሚሉት ሰውዬ ይህን ያህል ጅል አይመስለኝም ነበር። ለማንኛውም የካቲት 11 ሲደርስ ከእግሪ ሓሪባ ህዝብ ላሳልፈው አስቤያለሁ። ሌሎች የህወሓት ተቃዋሚዎችም እኔ ጋ ብትመጡ ደስ ይለኛል። በነገራችን ላይ ኰሓ ያገኘሁት አንድ የመንግስት ሰራተኛ እንደነገረኝ ወደ እግሪ ሓሪባ,ገብተው የነበሩት ዘራፊዎች በወያኔው መንግስት የተላኩ ናቸው አለኝ። ሊሆን ይችላል።

የህወሓት ፍፃሜ የተቃረበ ይመስላል!!

Leave a Reply