(ኢ.ኤም.ኤፍ) ነገሩ የሆነው በኢትዮጵያ ደቡብ ክልል ውስጥ ነው:: አቃቤ ህግ በአባት እና በ3 ልጆቻቸው ላይ ክስ መስርቶባቸዋል:: የክሱ ጭብጥ እንደሚያስረዳው ከሆነ “መለስ እንኳን ሞተ” በሚል “ሃሰተኛ ወሬ አሠራጭታችኋል:” የሚል ነው:: እዚህ ላይ ልብ በሉ… ከሳሾቹ እንዳሉት ከሆነ ‘መለስ ዜናዊ በመሞቱ ሰዎች የተሰማቸውን ስሜት ገልጸዋል’ ተብሏል… ይህ አባባል ታዲያ እንዴት የሃሰት ወሬ ከማሰራጨት ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ግልጽ አይደለም::
ሃሰተኛ ወሬ ማለት ያልሆነውን ነገር ሆነ ብሎ ማውራት ነው:: ለምሳሌ በዚያን ወቅት ጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊ ሞተው ሳለ “አልሞቱም” ሲሉ የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን እና ሚዲያው… በ’ርግጥ የሃሰት ወሬ ሲያሰራጩ ነበር:: አሁን እንደምናየው ግን ‘የሃሰት ወሬ አሰራጭታችኋል’ ተብለው የተከሰሱት የመለስ ዜናዊ ሞት ያላሳዘናቸው ሰዎች ናቸው:: ለመሆኑ አንድ የማይወዱት ሰው ሲሞት “እንኳን ሞተ” ብሎ ማለት የሃሰት ወሬ ማሰራጨት ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው? አለማዘንስ እንዴት ወንጀል ይሆናል?
እንዲህ ያለውን ዜና የምናቀርበው …ፍትህ በኢትዮጵያ ውስጥ የደረሰበትን አሳዛኝ እና አሳፋሪ ደረጃ ለማሳየት ጭምር ነው:: የነገሩን አሳሳቢነት ለመመዘን እንዲያስችልዎ እራስዎን በተከሳሾች ቦታ ያስቀምጡ እናም በመለስ ዜናዊ ሞት ባለማዘንዎ “ሃሰተኛ ወሬ አሰራጭተዋል” ተብለው ሲከሰሱ ይታይዎ:: ለማንኛውም ጉዳዩ ለታሪክ ምስክር ይሆን ዘንድ በወቅቱ በተከሳሾች ላይ የቀረበውን የክስ ቻርጅ ለህትመት አቅርበነዋል::
ለሞተ ሰው አለማዘን እንደ ወንጀል ተቆጥሮ በደቡብ ያገራችን ክልል እስከ 6 ወር የሚደርስ እስራት የተፈረደባቸው እንዳሉ ሁሉ በሰሜን ጎንደር ውስጥ በመተማ ከተማ ውስጥ… የመለስ ዜናዊ ሞት እንደተሰማ ” እንኳንም ሞተ፣ ተገላገልን” በማለት በመጠጥ ቤቶችና የተለያዩ ቦታዎች ደስታቸውን ገልጠዋል ” ተብለው ከ120 በላይ ሰዎች በተመሳሳይ ክስ ተወንጅለው እስር ቤት መወርወራቸው ሪፖርት ባልተጠናከረባቸው ሌሎች ክልሎች ተመሳሳይ ጥቃት የተፈጸመ መሆኑ ይታወሳል።
January 5, 2015 at 5:15 AM