
ከቅርብ ቀናት በፊት ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር የምታደርገው ስምምነት ድብቅነት ላይ ያለኝን ስጋት ገልጨ ነበር።ነገሩ እንዳልኩት ነው።በኢትዮጵያ፣ሱዳን እና ግብፅ መካከል በቅርቡ ይደረጋል የተባለው ስምምነት ላይ የግብፅ እና ሱዳን መንግሥታት ከምሁራን፣የፓርላማ አባላት፣የፖለቲካ ሰዎች እና ህዝቡ ጋር እየተወያዩ ነው።የግብፅ መንግስት በዝርዝር እንዲጠና ለአጥኚዎች ሰጥቷል።
ኢትዮጵያ ከ7 የማይበልጡ ሰዎች በሚስጥር ይዘው በስማችን ሊፈራረሙ ላይ ታች እያሉ ነው።ለአባይ ገንዘብህን እንጂ ሀሳብህን የማይቀበለው ስርዓት ”8100” ላይ እንድትደውል እና ብርህን እንድትሰጥ እንጂ በእኛ እና በልጅ ልጆቻችን ላይ የሚፈርድ ስምምነት ሲፈራረም ስለ ውሉ ይዘት አይነግርህም።
99% የእኔ ነው ለሚለው ፓርላማም አያማክርም።በሌላ ሀገር የእዚህ አይነት በትውልድ እና በሉአላዊነት ላይ የሚፈርድ ስምምነት ሲደረግ ከፓርላማ የቀደመ ማን ይወያያል? ግብፆች በደስታ ከበሮ እየደለቁ ነው።ከጥናቱ በኃላ ግን ምን እንደሚሉ አይታወቅም።
– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/5403#sthash.0JnOO9AF.dpuf