
ቅዳሜ 08 / 09 / 2007 ዓ/ም በዓረና መድረክ በመቐለ ማዘጋጃ ቤት ኣዳራሽ የተጠራ የህዝብ ስብሰባ የተሳካና ሁሌ በዓረና-መድረክ ታላቅ ህዝባዊ ድጋፍ ኣንጀታቸው እርር የሚሉ ህወሓቶችም ድንጋጤኣቸው ለከት ኣጥተውለት ያሳበዳቸው መድረክ ሁኖ ኣልፏል።ስብሰባው የተከፈተው በትጥቅ ትግሉ የተሰዉ ሰማእታትና በሊብያ በኣይ ኤስ ኣይ ኤስ ለታረዱ ወገኖቻችን የኣንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ ነበር።
በስብሰባው የዓረና-መድረክ ኣማራጭ ሃሳቦች፣ የገዢው ፓርቲ ድክመቶች፣ ዓረና-መድረክ ያሉት ምርጥ ምርጥ የመፍተሄ ሃሳቦች ቀርበዋል። ህወሓትም ካድሬዎችዋን ልካ ከፍተኛ ተሳትፎ ኣድርጋለች።
ከህዝብ ከቀረቡ ሃሳቦች ህወሓት የምትባል የድሮ ድርጅት ኣሁን እንደሞተች፣ እንደጠፋች፣ ኣሁን ያለችው ህወሓት ከድሮዋ ህወሓት በፍፁም የማይገናኙና የኣሁንዋ በድሮዋ ህወሓት ስም ለመነገድ እየሞከረች ያለችው ፎርጅድ (ቓንጫ መርዓት፣ ኣሻንጉሊት) እንደሆነች ታላላቅና ወጣት ተሳታፊዎች ድምዳሜ የደረሱበት ሁኔታ በግልፅ ቋንቋ ገልፀዋል።
ህወሓት ስብሰባው እንዳይ ሳካ መጀመርያ ከሰዓት ሰልፍ እንደሚያደርጉ በመኪና የቀሰቀሱ ቢሆኑም ህዝቡ ለዓረና-መድረክ ቅስቀሳ ያሳየው ታላቅ ድጋፍ በመደንገጣቸው ከምሽቱ 2 ስዓት ጀምረው ቤት ለቤት እየዞሩ ሰለማዊ ሰልፉና ስብሰባው ለጥዋት እንደተቀየረና ማንኛውም ኑዋሪ የግድ መገኝት እንዳለበት ኣዘው ነበር።
ይህ ሁሉ ኣድርገው ህዝቡ ወደ ስብሰባው መጣና ኣንጀታቸው ቅጥል፣ እርር ፣ ድብን ኣሉ።
የህወሓት የቀበሌ ካድሬዎችም በኣዳራሹ መግብያ በር ኣጠገብ ሁነው የገባው እየመዘገቡ፣ ፎቶ ግራፍ እያነሱ ዋሉ።
በስብሰበው ላይ የዓረና-መድረክ ኣማራጭ ፖሊሲዎች በሚገባ ወደ ተሳታፊው እንዲደርሱ ተደርገዋል።
ህወሓቶች ምክሬን ተቀበሉ። ህዝቡ በጣም ጠልቷቹሃል። ስለዚህ የህዝብ ድምፅ ለመቀበል ተዘጋጁ፣ መድረክም ለሰራችሁት ጥፋት ሁሉ ይቅር ሊላቹና በሚመሰርተው ሃገራዊ እርቅ የሚመሰረት መንግስት ኣካል ያደርጋችኋል። ይህ ሲባል ከሁሉም ሰላማዊ ተቃዋሚ ድርጅቶች፣ ከትጥቅ ትግል የሚመረጡ ወገኖች፣ በውስጥና በውጭ ኣገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምሁራን የተውጣጣና የሽግግር መንግስት ኣካል ትሆናላቹ።
ኣለበለዝያ እንደለመድነው ኮሮጆ ዘርፈን በስልጣን እንቆያለን የሚል ቅዠት ካላቹህ ግን ለናንተም ጥሩ ኣይደለም፣ ለሃገሪቷም ኣይጠቅምም።
የትግራይ ህዝብ ግን ምርጫው በግልፅ ቋንቋ ዓረና-መድረክ እንደሆነ እየተናገረ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ በመቀሌ የተልጠፉ የዓረና ተወዳዳሪዎች ፎቶ በህወሃት ሰዎች እየተላጡ እና እየተቀደዱ ናቸው። ይህም የህወሃት ሰዎች ምን ያህል ያልሰልጠኑ እና የፖለቲካ ንቃታቸው ኋላ ቀር መሆኑን አምላክች ሆኗል። ይህን በተመለከተ ከትግራይ የደረሰን ዘገባ እንዲህ ይላል።
- በህወሃት ሰዎች የተቀደደው የምርጫ ቅስቀሳ ፖስተር (የህወሃት ሰዎችን አለመሰልጠን አመላካች ነው)
የዓረና መድረክ የእጩ ተወዳዳሪዎች ምስል የያዙ ፖስተሮች በህወሓት የወረዳ ካቢኔ ኣባላት፣ ካድሬዎች፣ ፖሊሶችና የኮብልስቶን በመስራት ላይ ያሉ ወጣቶችና በህፃናት ኣማካኝነት እየተቀደደ ነው። የምርጫ ህጉ የተወዳዳሪዎች ፖስተር መቅደድ በህግ የሚያስጠይቅና የሚያስቀጣ ቢሆንም ህወሓት ግን በህጉ ተገዢ ለመሆን ፍቃደኛ ልጦን ኣልቻለችም።
ህወሓት በተግባርዋ የህዝብ መሳቅያ ሁና ፍርሃትዋ ምን ያህል እንደሆነ በትዝብት ላይ ወድቃለች። ይህ የህወሓት የፖስተር ቀደዳ ተግባር ለኮረጆ ቀደዳ እንደ የኣቋም መፈተኛ ልምምድ ሊታስብ ይችላል። እነሱ የፈለጉት ህገወጥ ተግባር ሲሰሩ እኛ ደግሞ የህዝባችን ልብ፣ ድጋፍና ማገር እያገኘን እንጎመራለን።
ዓረና መድረክ እምዲህ ያስደነገጣቸው ምክንያት በመላ ትግራይ የምርጫ ታዛቢዎች መልምሎ ኣዘጋጅቶ በማቅረቡ ነው። ለታዛቢዎቻችን የእስራት፣ የማስፈራራትና ዛቻ በኣስተዳዳሪዎች እየደረሰባቸው ነው።
የፖሊስ ስራውና ሃላፊነቱ በኣግባቡ ኣለመወጣት ምርጫው ወዳልሆነ ኣቅጣጫ እየወሰደው ይገኛል።