5/19/15

 

ሜካፕ ተቀቢ፤ ፋሽን ልበሺ አትበሉኝ፡፡ ፌስ ቡክ ላይ ልወዳደር አልመጣሁም፡፡ የአስተሳሰብ ለውጥ እንዲመጣ የበኩሌን ሸር ላድርግ ብዬ ነው፡፡ እሱም ብዙ ነገሮች እራሴንም ሰለነኩኝ ነው፡፡ ምንአልባት እራስ ያልተነካ ሌላውን ለመረዳት አዳጋች ሊሆን ይችላል፡፡ እምነትን ሰው ቢመሰክርልህ የምታየው የመስካሪውን ስራ ስለሆነ አትቀበልም፡፡ ግን የእምነቱ ባለቤት የሆነው እግዚአብሄር መኖሩን እንዲመሰክርልህ ተመኝ፡፡ በአገራችን የኢንፎርሜሽን ሁኔታ መደነጋገርን አምጥቶብናል፡፡ ይህም ፕሬስ እንደልቡ ነጻ ቢሆን ኖሮ የማይሸሽ ኢንፎርሜሽን አቅራቢ በኖረህ ነበር፡፡ አዳሜ ስሙን እና መልኩን ደብቆ ፌስ ቡክ ላይ ቁጭ ብሎ፤ እኔን በመልኬእና በስሜ የቀረብኩትን ህገወጥ እና ሞራል የለሽ ነገር እንድናገር አይጠብቅ፡፡ ኢትዮጲያ የምትለወጠው አስተሳሰባችን ሲቀየር ነው፡፡ ካልሆነ ወታደሩም ከኛው የወጣ ነው፡፡ መሪውም ከእኛ ነው፡፡ በሁሉም ቦታ የኛን ባህሪ ነው የምታየው፡፡ በዚህም የተነሳ በአገሬ ጥሩ ሰውም አልኮራም፤ እሱ የተወጣው የእራሱን ነው፡፡ በአገሬ መጥፎም ሰው አላፍርም፡፡ ይህም የሚያሳየው የግሉን ባህሪ ነው፡፡ እኔ የምኮራውም የማፍረውም እራሴ በሰራሁት ስራ ነው፡፡ የሌላው መጥፎም ጥሩም እኔን አይወክለኝም፡፡ ለውጥ ስል ከእራሴ መጀመር አለብኝ፡፡

የምበላው ምግብ እንጂ የምመለከተው አልፈልግም፡፡ ፖለቲከኞችንም የምታየው የሚያቀርቡልህ ነገር ሁሉ መረዳትህን ተመርኩዞ ውይም አጥንተውህ ነው፡፡ ስለዚህ አመዛዝን፤ እና ከክፋት ተቆጠብ፡፡ ጉቦ አትብላ አትክፈል፡፡ ነጋዴም በመስኮት ደርድሮ የማትገዛውን የሚያቀርቡልህ፤ ከመጎምጀትህ እንደምትገዛ ስለሚያውቁ ነው፡፡ አዎ አሳፋሪ ነው፤ ህዝብን በፖሊስ እንዲጠበቅ ለማድረግ፤ ግን ዛሬ ታዲያ ፖሊስ እና ወታደር ምን ሰርቶ ይብላ፡፡ ድንበር የሚገፋ አገር እንደድሮው የለም፡፡ ወደህ ካለቀክለት ማንም ድንበሩን አውቆአል፡፡ ተሻግሮ ገብቶም መሬትን መግዘት ችሎአል፡፡ ይህ በየትኛውም አለም የሚደረግ የዘመኑ ሁኔታ ሆኖአል፡፡ እሚፈለገው አገር አይደለም እህል የሚያፈራ መሬት ሆኖአል፡፡ ዛሬ መሬት ለእርሻ በአለም ላይ ይፈለጋል፡፡ የኢትዮጲያን ምድር ጎመን እንኩዋን ተክለህ ሳትበላበት፤ ድንግል ነው እያልክ የኮራህበትን፤ ዛሬ ድንግልን ሊያገባ ሀብታም ሰፍ ቢል አይግረምህ፡፡ ድሮም ድንግል ገንዘብ ላለው አልያም ለጉልበተኛ ነው፡፡ እኔ እምናገር እውነት ላይሆን ይችላል፡፡ ግን ወዳጄ ሆይ፤ ሰው የሚናገረው በውስጡ የሚያስበውን የእራሱን እውነት ነው፡፡ በዚህ የተነሳ አትቆጣው አትጩህበኝ፤ ግን በአንተ ውስጥ የእሱ እውነት እውነት ካልሆነ የአንተን አውጣው እና ተማመን፡፡ ይህን ነው ፈረንጅ ዲሞክራሲ የሚለው፡፡ ወዳጄ ሆይ ጆሮህን ሳይሆን ውስጥህን ኮርኩረው፡፡ እኔም ድፍን ቅል አልያም ጥቁር ድንጊያ ላልሆን ምዬ ልሰማህ ቀርቤአለሁእና፡፡

ጸጉሬን ቀለም የምቀባው፤ እድሜዬ የማይታይህ ከሆነ ነው፡፡ እድሜዬ ግን ለማየት አይን አለሕ ግንዛቤ አለህ፤ በዚህም አንተ ማዘር ብለህ መዘለፍህ ወይም ማክበርህን አትተወውም፡፡ እኔም እሱን ነው የምፈልገው፤ እስከሽበቴ የሚቀበለኝን፡፡ ታዲያ ወዳጄ ልንገርህ፤ የኢትዮጲያ ህዝብ 90% ገበሬ ነው፡፡ የሚያርሰውም በእጁ እና በበሬ ነው፡፡ ግና አለምን ልትቀልብ የምትችል መሬት ይዘን ትራክተር ያለውን አናስገባም ማለት፤ እሱም የማይሆን መሆኑን እያዬነው ነው፡፡ ታዲያ ይህንን ፍራ፤ ፖለቲካው ለገበሬው ቁም ነገር የሚሰራበትን መንገድ ፈልግ እንጂ፤ ባለትራክተር አይግባ ማለት በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ነው፡፡ በአለም የመጣውን የወደፊት የምግብ እጥረት እንጂ ብዙውን ያሳሰበው ወርቅ እና ነዳጅ አይደለም፡፡ ሰው ሳይበላ ሾፌር አይሆንም እና፡፡ ስለዚህ እኔ የምለው አንድ ነገር ነው፡፡ ለአገርህ ገበሬ እንዳይፈናቀል ሳይሆን የሚገባውን ዋጋውን እንዲቀበል፤ ልጁ እንዲማርለት፤ የሚኖርበት እንዲኖረው ፤ እንዲታከም ደግሞም ጠግቦ እንዲበላ እና የግብርናውም ተካፋይ እንዲሆን የፖለቲካ ስራ ሳትቡዋቀሱ በጋራ ስሩ እንጂ፡፡ የኢትዮጲያ ገበሬ 90% በሆነበት አገር ገበሬ አይፈናቀልም ለማለት፤ ታዲያ ለማልማት መሬት ከየት ይምጣ በማለት መረዳቴን እርምት ታደርጉ ዘንድ እነሆኝ አስተሳሰቤን ይዠ ቀርቤአለሁ፡፡ ባዩሽ ነኝ

Bayush Abebe's photo.

Leave a Reply