(ኢ.ኤም.ኤፍ) ትላንት በጬርቆስ እና በመገናኛ አካባቢ የነበረው አፈሳ ዛሬም ቀጥልሏል።
በሸጎሌ መንደር ነዋሪዎችና በቀበሌ 31 አዲሱ ሚካኤል ነዋሪዎች በትላንትናው እለት የሰማያዊን ፓፍሌት በመቀበላቸው ለሊቱን በፖሊስ ቁም ስቅላቸውን ሲያዩ ያደሩ ሲሆን ከ20 በላይ የሆኑ ወጣቶችም በለሊት ታፍሰው ተወስደዋል።በትላንትናው ዕለት የሰማያዊ ቀስቃሾች በአካባቢው ቅስቀሳ ያካሄዱ ሲሆን በወቅቱ የተበተነውን ሰማያዊ ፓርቲን የሚያስተዋውቅ ፓንፍሌት የተቀበሉ ወጣቶች በወቅቱ ፖሊስ ከእጃቸው ላይ እየቀማ የቀደደ ሲሆን በህጉ መሰረት ከ12፡00 ሰዓት በኋላ የምርጫ ቅስቀሳ የተከለከለ ቢሆንም የኢህአዲግ ካድሬዎች እስከ እኩለ ለሊት ሲቀሰቅሱ ቆይተዋል።

በተያያዘም ካድሬዎቹ ቤት ለቤት በመዞር በዛሬው ዕለት ለኢህአዲግ የሻማ ማብራት ፕሮግራም ሁሉም ነዋሪ እንዲወጣ እያዘዙ ሲሆን የጥሪውን ወረቀት አልቀበልም ያሉትን ነዋሪዎች እያስፈራሩ የተወሰኑ ወጣቶችንም በፖሊስ አሳፍሰዋቸዋል።
ይህ በንዲህ እንዳለ የሚሊየኖች ድምፅ ጋዜጣ አምደኛ የነበረው ወጣት ቴዎድሮስ ፀጋ ሱልልታ አካባቢ ከቀኑ 7፡30 ላይ በፖሊስና በደህንነቶች ታፍኖ ወደ አካባቢው የሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ መወሰዱን በስፍራው የነበሩ ምንጮች ገለፁ፡፡
ወጣት ቴዎድሮስ በሱልልታ ነዋሪ ከመሆኑ በተጨማሪ በወረዳ 4 የመድረክ ተወካይ የሆኑት አቶ አለሙ ጎቤቦ ታዛቢ እንደሆነ ይታወቃል፡፡