===========================
የአረና-መድረክ የምርጫ ቅስቀሳ ቡዱን ገና ከጅምሩ በውቅሮ ከተማ ፖሊሶች በፓትሮል አግተው ለተወሰነ ሰአታት ካጉላሉን ብኃላ በአጽቢ ወንበርታ በማይክሮፎን ይንቀሳቀሱ ወደ ነበሩት የአረና-መድረክ የአከባቢው ተወላጆች አባላት መንገድ መንገድ እየቀሰቀስን ሄድን።ይህ የሆነበት በ 11/09 07 ሲሆን አረና-መድረክ በህዝብ ዘንድ ያለው ድጋፍ እንኳን ለኛው ለአረና አባልት ለተከራየናት መኪና ሾፌርና ረዳት ለሆኑትም በጣም ተአምር ነው የሆነባቸው ምክንያቱም አረና መድረክ በከተማ ይሁን በአርሶ አደሩም ይህን ያህል ድጋፍያለው አይመስላቸውም ነበር ።
ለዚ ማሳያ መኪና ላይ ተጭኖ የነበረ መንታርቦ ተበላሽቶብን ዴራ በምትባል ከተማ ከመኪና ወርደን በእጅ ማይክሮፎን ስንቀሰቅስ ከህዝቡ ከድጋፍ ውጪ እንኳን ክፉ ነገር አንድም መገላመጥ አልደረሰንም።
[ሊንኩ መመልከት ይችላሉ] ታድያ ይህ የህዝብ ድጋፍ ያስደነገጠው ገዢው ህወሓት የምስራቅ ትግራይ የህወሓት የፕሮፓጋንዳ ሀላፊ አቶ ደሳለኝ ታፈረ የተባለ ሰው የዛሬ ሁለት አመት አከባቢ ለነአምዶም ገብረስላሴ ፣አብርሀ ደስታና አስገደ ገብረስላሴ በአድግራትና በአጽቢ ልክ እንደ ከትናንት በስትያው ከተለያየ አከባቢ ጎረንሶች ሰብስቦ ያስደበደባቸው
እኛ ቅስቀሳችን ጨርሰን ስንሄድ በሞተር ሳይክል አድርጎ ይከታተለን የነበረ ሰው “””ዝባን ሐሳኺለ””” በሚባል አከባቢ ወደ ሚገኝ ኬላ ይሁን ወይስ ለኛ ሲባል የተዘረጋ ገመድ በመሄድ ለሚሊሻው ትእዛዝ በመስጠት[ በነገራችን ላይ ከዛ በፊት ወደ ኬላው ሳንደርስ መንገድ ላይ ድንጋይ ደርድረው አንድ በእድሜ ጠና ያሉ ሰውዬ መታወቅያ ጠየቁን] ለምን ስንላቸው ታዘን ነው አሉን እኛን ለማዘግየት መሆኑ ስለገባን ዝም ብለን አለፍን።
ኬላው ላይ አንድ [ ከለከለን ብኃላ ምልሻው እኔ ታዝዤ ነው ምን አድርግ ትሉኝአላችሁ ስለዚ አታልፉም አለን ከሚሊሻው ጋር ብዙ ተጨቃጨቅን እንግድያውስ በመጣንበት እንመለስ ብለን ስንመለስ[ ኬላው ኔትዎርክ የለውም] ጎሮምሶቹ ወደ ኬላው በማስመጣት ሊያስጨፈጭፈን እንደነበር ሁላ ነው የገባን።
ልጆቹ ገና ከዴራ የምትባል ከተማና ከሌላ ቦታ ያስመጣቸው በድንጋይ ሲወረውሩ ሾፌሩ በፍጥነት በማሽከርከር ከሞት አትርፎን መኪናዋ ግን ወደ ስምንት ሺ የሚያስወጣ ጉዳት ዶርሶባታል ።
እኛ አምልጠን ለኛ ቻው ብለውን ከሸኙን የዛ አከባቢ ተወላጆች ወደ ስምንት አባሎቻችን ተጎተዋል በተለይ ሁለቱ ኩፉኛ ተጎተዋል።የአረና ትግራይ አባላት በትግራይ እያለፉት ያለ መከራ እጅግ ብዙ ነው ግን ሊነጋ ሲል ይጨልማል ነውና አንምበረከክም።
ድል ፍትህ ላጣ ህዝብ!!!