MAY 22, 2015
የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ሚያዚያ 1/2007 ዓ.ም በብአዴን ኢህአዴግ ስርዓት የተለጠፈውን የምረጡኝ መቀስቀሻ ፖስተር በማየት ለውጥ ለማያመጣ ስርዓት አንመርጥም እያሉ እየቀደዱት መሆናቸውን ምንጮቻችን ገለፁ፣ በጎንደር ከተማ ቀበሌ 04 በወያኔ ኢህአዴግ የተለጠፈውን የምርጡኝ መቀስቀሻ ፖስተር በማየት ለውጥ ለማያመጣ ስርዓት አንመርጥም በማለት እየቀደዱት መሆናቸውን የገለፀው ይህ መረጃ በህብረተሰቡ ተግባር የተናደዱት የስርዓቱ ካድሬዎች ምንም አይነት ወንጀል ላልፈፀመ ዜጋ አንተነህ የለጠፍነውን ፖስተር የቀደድከው እያሉ በማሰር ተግባር ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ታውቋል፣ የደረሰን መረጃ ጨምሮ-የወያኔ ኢህአዴግን ፖስተር ቀድዳችኋል ተብለው በስርዓቱ ታጣቂዎች ከታሰሩት ውስጥም። ታደሰ ታፈሰ፤ አቶ ጫቅሌና ሌሎችም በርካታ ዜጎቻችን የሚገኙባቸው በእስር ቤት እየተሰቃዩ እንደሚገኙና ህብረተሰቡ ደግሞ በላዩ ላይ እያወረደ ያለውን ግፍ ለማስቆም ለሚመለከታቸው አካላት እያደረገ ያለው አቤቱታ ምንም አይነት ውጤት እንዳላመጣለት ከምንጮቻችን ያገኘውነው መረጃ አመለከተ፣ በተመሳሳይ በደብረብርሃንና ደሴ ከተሞች በየቀበሌው የተለጠፈ የብአዴን/ኢህአዴግን የምረጡኝ መቀስቀሻ ፖስተር ቀለም በመቀባትና በማበላሸት ልማት ይሁን እድገት ለማያመጣ ስርዓት አንመርጥም በማለት ተቃውሞአቸውን በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከቦታው አክለው አስታውቀዋል፣