ገና አላደገም፣የቤትን ሙቀትና ቅዝቃዜ አላወቀም፣እንደ ማንኛውም ህፃን አልጋ ለይ አልተወለደም፣እናቱም አራስ ሆና እንደ ሴቶቹ እንኳን ማርያም ማረችሽ አልተባለችም
ብቻ ምድር እንደፈጠረችው እዚች የቆምኩባት ምድር ለይ የዛሬ ሁለት አመት በላስቲክ ከለላነት ተፈጠረ።
እናቱ ህይወት ትባላለች ልደታ ከቤተክርስቲያኗ ፊትለፊት የሚገኝ አስፓልት ዳር በላስቲክ መኖሩያዋን ከልላ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ነበረች።
ያው መቼም ህይወት ለአንዱ ስትሞላ ለአንዱ ጎደሎ አይደለች ይሄው ይሄን አንድ ህፃን ልጅም ገና ሳያድግ ህይወት ጎዶሎ ሆናበት በእንቅርት ለይ ጀሮ ደግፍ እንዲሉ ያችን ምስኪን እናቱን አምሮ በሽተኛ አድርጋ ጭራሽ እናት እያለው እናት አልባ ሆኖ በልደታ አስፖልት ለይ ሲብከነከን ማየት እንዴት ያማል መሠላችሁ አዎ ያማል ዝም ብሎ ያገኘውን ሰው ሁሉ ባባ ብሎ ይስማል እኔም በእዚህ ጨቅላ አንድ ፍሬ ልጅ በተኮላተፈ አንደበቱ ባባ ተብዬ ጉንጬን ስሳም የምር ውስጤ ነው የተነካው ዛሬ ድህነቴን እዚህ ጋ ጠላሁት፣ዛሬ ማጣቴን እዚህ ጋ እረገምኩት፣ምክንያቱም ለእዚህ ጨቅላ ልጅ የሚሆን ሀቅም አጥቼ ለእዚያች በተፈጠረባት አስፓልት ለይ ተወት አድርጌው መምጣቴ የምር በጣም ያማል፣ዛሬ ልደታ ፊት ለፊት የሚገኙ የታክሲ ሾፌሮችን ጥሎለት ዳቦ በልቶ ይደር እንጂ በህፃንነት እድሜው ግን የእናት ፍቅር፣ወንድሜ ልጄ ብሎ የሚይዘው ሰው አለመኖሩ ግን ይሰቀጥጣል።
በልደታ ቤተክርስቲያን ይሄን ልጅ ከጠቆመኝ እና በእሱ አስተባባሪነት ለእናቱ በሶስት መቶ ሀምሳ ብር ቤት ተከራይተውላት ካስቀመጧት ከዘማሪ ዲያቆን ፋሲል ጋር ብዙ ተጨዋወትን ይሄን ልጅ ለማሳደግ ፍላጎት ቢኖረውም ሀቅም እንደሌለው እያሰበ አጫወተኝ።
አዎ ሁላችንም አቅም አልባዎች ነን ይሄኔ ግን ሰዎች ያስፈልጉናል።
ለእዚህ ልጅ ፍቅር ሰጥተው የሚያሳድጉት ቤተሰቦች ያስፈልጉታል።
ስለዚህ ፈቃደኛ ሆኖ እኔ አሳድገዋለሁ፣የሚል ካለ ልጁን ብትወስዱት በእግዚያብሄር ዘንድ ትልቅ ዋጋ ይኖራችኋል።
መቼም እናንተ የፌስቡክ ወዳጆቼ የሚጨክን ልብ እንደሌላችሁ ስለማምን ይሄን ልጅ ታሳድጉት ዘንድ እናንተን ለመለመን ይሄው የውስጠቴን ሀዘን ለእናንተ ላካፍል ወደድኩ።
አደራ ገንዘብ ልከን እንርዳው እንዳትሉኝ እኔ የምፈልገው ገና በጨቅላነቱ የተነፈገውን የቤተሰብ ፍቅር ቤታችሁ ወስዳችሁ በሞቀው ሳሎናችሁ ፍቅር ትሰጡት ዘንድ ብቻ ነው።
አድጎም ነገ ታላቅ ሰው ሆኖ ብድራችሁን ከፋይ ይሆን ይሆናል።
@ለበለጠ መረጃ በ 0911418256/0911075424 ዘማሪ ዲያቆን ፋሲል ብላችሁ ደውሉለት
Waltengus Abneh's photo.

Leave a Reply