ራሳቸው በሚወዳደሩበት ምርጫ ያልመረጡ የመጀመሪያው የፓርቲ መሪ ሆኑ

 እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. May 24, 2015)፡-

በኢህአዴግ ተቃዋሚነት የብዙዎች ድጋፍ እንዳላቸው የሚታመነው የኦፌኮ (የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ) ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ዛሬ በተካሄደው ምርጫ ድምጻቸውን መስጠት (መምረጥ) አለመቻላቸው ታወቀ። ዶ/ር መረራ ፓርቲያቸውን ወክለው በተወለዱበት የጉደር ከተማ ተወዳዳሪ ቢሆኑም፤ ለራሳቸውም ይሁን ለሌላ ሰው ድምጻቸውን የሚሰጡበትን የምርጫ ካርድ በሰዓቱ ባለማውጣታቸው ዛሬ መምረጥ ሳይችሉ ቀርተዋል።

ዶ/ር መረራ የምርጫ ካርዳቸውን በሰዓቱ ሳይወስዱ ለመቅረታቸው የሰጡት ምክንያት፤ በምርጫ ሥራዎች ተወጥረው ስለነበር የምርጫ ካርዳቸውን ኺደው የሚወስዱበት ጊዜ በማጣታቸው መሆኑን ገልጠዋል። ዶ/ር መረራ ጉዲና በ2007ቱ የምርጫ ክርክር ጥሩ የሕዝብ ድጋፍ እንዳገኙ ይታመናል፤ ዶክተሩ ከዚህ በፊት ከገዥው ፓርቲ ጋር በተደረጉት የምርጫ ክርክሮች በሚያደርጉት ንግግር የብዙኀኑን አንጀት በማራስ ይታወቃሉ።

ኢህአዴግ ደርግን አባርሮ ሥልጣን በእጁ ከጨበጠ 24 ዓመታት ውስጥ የዘንድሮው ምርጫ2007፣ 5ኛው ሲሆን፣ በከፍተኛ የፖለቲካ አመራር ላይ ከተቀመጡ ግለሰቦች፤ በተለይም የፓርቲ መሪዎች ውስጥ የምርጫ ካርዳቸውን ባለመውሰዳቸው ምክንያት ራሳቸው በሚወዳደሩበት ምርጫ ላይ ድምጻቸውን ሳይሰጡ በማለፍ የመጀመሪያው የፖለቲካ ፓርቲ መሪ ዶ/ር መረራ ጉዲና ሳይሆኑ እንደማይቀሩ ይታመናል።

Ethiopia Zare

Leave a Reply