ከቢላል አበጋዝ፡ ዋሽግቶን ዲሲበዚህ ሰሞን ሁለት አገራት ህዝባዊ ምርጫ አካሂደዋል። አንዱ የእውነት ሌላው የቅጥፈት። የእግር ኳስ ፍቅራችንን እንደያዝነው በምርጫው ሰሞን በስፓኙ እና ኢትዮጵያ ምን ሆነ? እስቲ እናወዳድር።

ምኞቴ ወደፊት ኢትዮጵያ ስፔኝን ገጥማ መጀመሪያ የህዝብ ምርጫን ጥሩ አድርጋ በመደገስ ቀጥሎ በእግር ኳስ ስታቸንፍ ማየት ነው። የግር ኳስ የምትወዱ ምኞቴን ተጋሩ። በግር ኳስ ከመዝናናት የበለጠ የመቶ ሚሊዮናችንን ህይወት፤የአገራችችን ዕድል ወሳኝ ጉዳይ በዚህ ሰሞን ተካሂድዋል። በስፓኝ ዛሬ ያለው ዲሞክራሲ ብዙ ክፍያ ተከፍሎበታል።በኢትዮጵያም አባት አርበኞቻችን ጣሊያንን እየተዋጉ ሳለ(ሁለተኛ የዓለም ጦርነት)ሪፑብሊክ የመመስረት እልማቸውን አብስረው ስለነበር።ምሳሌ እነ ደጃዝማች ታከለ ወ/ሀዋርያት፡ከዚያ አንስተን ብናሰላው ዘመኑ ረጅም ነው።የኢትዮጵያው እንዲያውም አንድ ትውልድ የወደመበት፤የዛሬው ወጣት ተስፋ የቆረጠበት ፡መሪር ዓመታት ያለፉበት።

የጽሁፉ ዓላማ እዲያው ዝም ተብሎ ስፓኝን ከፍ ለማድረግ ሳይሆን በሁለቱ አገሮች የሆነውን ባጭሩ ለማሳየት ነው። በስፓኝ ከሁሉም በላይ በስልጣን ያለው የጠ/ሚኒስትር ማሪያኖ ራሆይ መንግስት ስልጣን ሲይዝ የስፓኝ የኑሮ ውድነትን አሻሽላለሁ በሚል ቃል ገብቶ ኋላ በሙስና መጋለጡ የህዝቡን ሙሉ ድጋፍ አሳጥቶታል።የራሆይ ፓርቲ፡ፖፑላር ፓርቲ የተሰኘው ብዙ መቀመጫዎች ተቀምቷል። የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ሰው አስጠንቷቸው እንዳሉት “ዲሞክራሲ ባህል ነው”። እርግጥ ነው ጊዜ የሚፈጅ እድገት ነው። ቢሆንም የኢትዮጵያ ህዝብ ያሚያሳየውን የፖለቲካ ብስለት ለተመለከተ ይህ ዲሞክራሲ የሚባል ስልጣኔ ለኢትዮጵያ ህዝብ ቶሎ እንደገባው ማየት አይቸግርም።ለምርጫ ሲሰለፍ ስርዓቱ፤እድሉን ሲያገኝ የውይይት ተሳትፎው ከስፓኝ ወይም ከማንም አያንስም።የኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር ዳዴ እያስኬደው እንዳለ በባለጌ ድፍረት ቢናገርም።በዚህ የተነሳ ዳኛው በህወያት\ኢህአዴግ ላይ ፍጹም ቅጣት ምት በየነዋል።

ስፓኝ እና ኢትዮጵያ እሩቅ ለሩቅ ቢሆኑም የሁቱም አገሮች ወይም ማንም ህዝብ ለመብቱ ቀናተኛ ነውና ጎን ለጎን ብናያቸው በዚህ ረገድ ስተት አይሆንም። ወያኔ ኢሀዴግ ውጤቴን ዝቅ አረጋችሁ ብሎ ሊኮንን ይችላል።እንደለመደው ሁማን ራይት ዋችንም (የሰው መብት ተከራካሪ ድርጅት)ግራ ቀኙን መክሰሱ የተለመደ ነው። ከአውሮፓ ግጥሚያው ለማየት የሚመጡት ዘንድሮ ገንዘብ ቸገራቸውም ብሎ የሚቀድ ነው።

በኢትዮጵያ ሰሞኑን ያለፈው የምርጫ ወግ ገና ብዙ የሚወጣ ጉድ ይኖረዋል።ስላለፉት ምርጫዎች ውስጥ አዋቂ ባካፈለን ዛሬ እየተደነቅን አይደለም? በዝርዝር ለታሪክ የሚቀርበውን እየጠበቅን የሰሞኑን ምርጫ እንወያይበት። ትምህርት ወስደን እንቀጥል።ቢያንስ ከዚህ በኋላ በሰላም የስልጣን ሽግግር የሚታሰብ ነው ? በውነት ወያኔ ኢህአዴግ ለዚህ ወግ ይደርሳል።ምርጫውን መካፈል ተቃዋሚዎችን ረዳቸው? እንዴት ? እኒህን ጥያቄዎች መጋፈጥ አለብን። የሃይማኖት ድርጅቶች ተከፋፍለው፤የብሄር ድርጅቶች የወያኔ ኢሀዴግ መሳሪያ ሆነው ወጣቱ በአንድ ጎራ ሳይሰለፍ፤በጥርጣሬ ተይዘን ወደፊት መሄድ ይቻላል ?

ወደ ጨዋታው ስንመለስ የተነሱትን ጥያቄዎች እያሰብን የቀረበውን ግጥሚያን ባጭሩ የሚያቀርብ ሰንጠረዥ እንመልከት።

እነበረከት ስሞን በጡረታ የወጡ መስለው አሻንጉሊት ተጫቃቾችን ምሳሌ ሀይለማርያም (የሟቹን መለስ ማሊያ ለብሶ የሚጫወተውን)ሬድዋን ሁሴን አሜሪካ መጥቶ ከባድ ስብራት ደርሶበት የነበረውን ከመጋረጃ ኋላ ሆነው እየዘወሩ በጫወታው ተካፍለዋል። ሺመልስ ከማል ጫት በብዛት እየቃመ ከጥቅም ውጭ በመሆኑ በዚህ ግጥሚያ አልተሰለፈም።
ይሄው እንግዲህ ደርግ ከሄደ አንስቶ ዲሞክራሲ እየተባለ ከበሮ ሲደለቅ ሃያ ዓመታት አልፋዋል።የኛስ ዲሞክራሲ ላሳር ነው። ማደግ እምቢ ያለ ድውይ ሆነ።ሸፍጥ፤ተንኮል እንዳያድግ የያዘው መልካም ነገር። እንደኔ እምነት ወያኔ ኢህአዴግ ሳይጫነቅ ህዝብን አክብሮ በሰላማዊ መንገድ የስልጣን ሽግግርን ያደርጋል ብሎ ማሰብ ሁኔታውን በቅጡ አለማስላት ነው።አምላክ የታረቃት አገራችን ወጣት ልጆችዋ ጠላትዋን ሊያጫንቁት ቆርጠል።ወያኔ ኢህአዴግ ይህን ስሙን አትጥሩባኝ ብላል።ካሁኑ ጨንቆት!

የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ! ምርጫ ከመካፈል በፊት ይህ ይቀድማል።
ኢትዮጵያ በክብር፤በአንድነት፤ተረጋግታ በነጻነት ትኖራለች።የጃዙር ቅኝ ግዛት አትሆንም!!!

Leave a Reply