ሥርዓቱ ባሳለፍነው ሳምንት ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል አስቀድሞ የታወቀውን የህወሓት/ኢህአዴግ የምርጫ ድራማ በማካሄድ፤ ሕዝብን ተስፋ በማስቆረጥና ግፉን አሜን ብሎ በመቀበል፤ ቀደም ሲል ሲያደረግ የነበረውን ሀገር የማፈራረስ ሂደትና የሕዝብን ስቃይ የሚያበዛ አገር በቀል የአፓርታይድ አገዛዝ ለቀጣይ አምስት አመታት ለማስቀጠል የሚያስችለውን ህጋዊ ሽፋን በማመቻቸት ላይ በሚገኝበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፤ አገር አድን የምክክር ጉባዔ በማድረግ በሕዝብ ተቀባይነትና ታማኝነት ያለው ሁሉን አቀፍ የአማራጭ ኃይል በማቋቋም ትግሉን በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠል ወቅታዊና አስቸኳይ ነው።
ከላይ በመግቢያው ላይ የተዘረዘሩት ድርጅቶች፤ ከተለያዩ አክቲቪስቶችና ታወቂ ግለሰቦች ጋር በመሆን ከጁላይ 2-3 የምክከር ጉባዔ በጋራ ያዘጋጃሉ። የጉባዔውን ውጤት ለማሳወቅ ሕዝባዊ ስብሰባም ይዘጋጃል። የመሰብሰቢያ ቦታ፤ ዝርዝር ፕሮግራሞችና ተያያዥ እንቅስቃሴዎችን በተከታታይ እንደምናሳወቅ ከወዲሁ መግለጽ እንወዳለን።
ስለዚህ፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የፓለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ መኅበራት፣ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆናችሁ ወጣቶች፤ በሀገራችን ነፃነት ሠላም እኩልነትና ፍትኅ ይሰፍን ዘንድ የምትተጉ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ አዘጋጆች፣ የፓልቶክ ክፍሎች፣ ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች፣ ምሁራንና የሀገር ሽማግሌዎች፣ የእምነት አባቶች፤ እንዲሁም ለሀገር ደህንነት ተቆርቋሪ የሆናችሁ ዜጐች በሙሉ፤ የሚገነባው የተባበረ አማራጭ ኃይል ባለቤት እንደመሆናችሁ መጠን የሂደቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆን፤ በሀገራችን ነፃነት እውን እንዲሆን በሚደረገው ወሳኝ ሕዝባዊ ትግል ውስጥ የበኩላችሁን አስተዋፅዖ ታበረክቱ ዘንድ፤ እንዲሁም በሕዝባዊ ስብሰባው ላይ ንቁ ተሳትፎ እንድታደርጉ አደራ እያልን በአክብሮት ሀገራዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ይህ አደገኛ የቁልቁለት ጉዞ እንዲገታ በጋራ እንቁም!
የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (SHENGO)
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት (ENTC)
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት (UEM-PMSG)
የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ (EYNM)
ግንቦት 22፤ 2007 (May 30, 2015)