• ለዓመታዊው ስብሰባ በወጣው መርሐ ግብር መሠረት ፓትርያርኩ፣ በዛሬው የበዓለ ጰራቅሊጦስ የጠቅላላ ጉባኤው ማጠቃለያተገኝተው አባታዊ መመሪያ እና ቃለ ምዕዳን በመስጠት ማሰናበት ነበረባቸው፤
  • መርሐ ግብሩንም እንዲያውቁት ከብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ጀምሮ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተደጋጋሚ እየተላኩ እንዲነግሯቸው ተደርጎ ነበር፤
  • አማሳኞች፣ ‹‹ጠቅላላ ጉባኤው በፓትርያርኩ አይታወቅም፤ የፓትርያርኩን ስም ለማጥፋት እና በፓትርያርኩ ላይ ለማሳመፅ የተጠራ ነው›› የሚል የተሳሳተ መረጃ ለመንግሥት በመስጠት ለማሳገድ ተሯሩጠው ነበር፤
  • የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች የፀረ ሙስና እና ፀረ ኑፋቄ ንቅናቄ የተጋድሎ ነጥቦች የጠቅላላ ጉባኤው የጋራ አቋም መግለጫ አካል ኾነው ወጥተዋል!!!
በክዋኔ ላይ (Happening now) ጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ከቀኑ 11:29eotc ssd pouring out to patriarch palace00eotc ssd pouring out to patriarch palace01eotc ssd pouring out to patriarch palace
በሰንበት ት/ቤቶች ሀገር አቀፍ አንድነት ፬ኛ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ መደምደሚያ በፀረ ሙስና እና ፀረ ኑፋቄ የጋራ አቋሞች ተጠናክረው የወጡት ተሳታፊዎች ፓትርያርኩን ለማነጋገር በመዝሙር ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ሲያመሩ

Leave a Reply