by MINILIK SALSAWI » Today, 04:30

አንድ ያልገባኝ ነገር አለ… ወያኔ ካላፏጨ አንጮህም ማለት ነው??? ወያኔ ጠርቶ የነበረውን ምርጫ ተከትሎ በከፍተኛ ደረጃ ድምጻችንን ስለህዝብ እና ስለሃገር ስናሰማ ከረምን ድንገት የወያኔ የምርጫ ተቋም ወያኔ 100በ100 ሲለን አሁንም ጮህን ተከታታይ የትቃዋሚዎችን መግለጫዎች እና የምእራባውያን ሽሙጥ ተንተርሶ በፈንጠዚያ ላይ የነበሩ ካድሬዎች ሳይቀሩ ከድርጅታቸው ሕወሓት በወረደ ትእዛዝ ዝም አሉ …. እነሆ እስካሁን ሰአት ቄሱም ዝም መጽሃፉም ዝም… ግን ለምን?አዎ ግን ለምን ወያኔ በነፈረቀ ሰአት ሁሉ እየጠበቀን መጮኽ ዝም ሲል አብረን ቅዝቅዝ የምንለው ለምን ይሆን…. ብረት እንደጋለ መቀጥቀጥ አለበት እንደሚባለው በዚህ ወቅቱ በጋለ ሰአት ላይ ሃይላችንን በመጨመር ለለውጥ ጥልቁን ትግል ማድረግ ሲገባን ከያለንበት መበርታት ሲገባን አብረን ለሕወሓት ካድሬዎች እንደወረደው ዝም በሉ ትእዛዝ እኛም ቅዝቅዝ ማለታችን ምን ያህል ድክመታዊ ልፍስፍስነት እንደተጣበቀን እዳያሳብቅብን ያሰጋል::በትግል ሂደት ውስጥ የራስንም ድክመት ገምግሞ መፍትሄ መቀየስ አንዱ ክፍል መሆኑን አንዘንጋ::የወያኔ ካድሬዎች በተንጫጩ ሰአት ሁሉ የነሱን የማዘናጊያ ስልታቸውን እግር እግር ተከትለን አብረን ከተንጫጫን ለወያኔ እድሜ መስጠት እንጂ ትግል አይደለም…ዝም ሲሉም አይ ምንም አላሉም ዝም ብለዋል ምን እንደሚሉ እንጠብቅ ማለትም ሌላው ዝንጉነት ነው:;ለዚህ ነው የዳበረ ስልጡን ስትራቴጂ ያስፈልገናል የሚባለው::ምርጫውን ተከትሎ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ለመቀስቀስ የተቃዋሚ የለውጥ ሃይሎች መግለጫዎች ብቻ ሰፋ አድርገን ሕዝቡን ብንቀሰቅስበት ትልቅ ስራ መስራት በቻልን ነበር ሆኖም ጊዜው አረፈደም::አሁንም ሕዝቡን መቀስቀስ ማነሳሳት እና በሕዝባዊ እምቢተኝነት እና አምባገነኑን ስርአት በሚጥል አመጽ ድርሻውን እንዲወስድ ማድረግ የለውጥ ሃይሎች የትግል ግዴታ ነው::

ወያኔ ዝምታን የመረጠው አንድም ማዘናጊያ እና ጊዜን መግደያ ነው ሌላን የተቃዋሚዎችን ሃሳብ በምእራባውያን ድርድር እና ምክር ሂደቶችን ገድሎ ዝም ለማሰኘት ነው:: ወያኔ መሰሪ ነው::እያባበለ ይውጥሃል እያሳሳቀ ድንገተኛ ጎርፍ ውስጥ ከቶ የውሃ ራት ያደርግሃል::ይህንን የወያኔ እኩይ ተግባራት ካለፉት አመታት የተማርነው ስለሆነ መደጋገሙ አያስፈልግም::ወያኔ ተጨማሪ ጊዜ ለመግዛት ትንፋሽ መሰብሰቢያ የዝምታ ስልቶችን ይጠቀማል::ይህ ማዘናጊያ ነው በውስጥ ለውስጥ ስራዎቹን ከሰራ በኋላ ራሱን በድል አድራጊነት ለማውጣት ይውተረተራል ስለዚህ እኛ በወያኔ ዝምታ ሳንዘናጋ ወያኔ ባላዘነ ቁጥር አብረን ሳንጫጫ ለለውጥ ትግል መቀጣጠል ትልቁን ድርሻ መወጣት ስላለብን ሕዝብን በስፋት በመቀስቀስ እና በማስተባባር የለውጡን አብዮት ልናፈነዳው ይገባል::ብረት እንደጋለ መቀጥቀጥ አለበት::ድል የህዝብ ነው:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Leave a Reply