ሁላችሁም ተነሱ፥
ዐሥር ሻማ ለኩሱ፥
ሰኔ 1ላይ ደማቸውን ላፈሰሱ፥
አጥንታቸውን ለከሰከሱ።
ለዴምክራሲና ነጻነት፥
ለፍትህና ለዕኩልነት፥
ሳይገድሉ ለተገደሉ፥
በከፈሉት ታክስ በጥይት ለተቆሉ፥
ደማቸው በውሻ ለተላሰው፥
የምንዘክራቸው ዛሬ ነው።
በመለስ ዜናዊ መመርያ፥
በአጋዚ ጦር መሳርያ፥
ደረታቸው ተነድሎ፥
አንጎላቸው ተፈንቅሎ፥
በስናይፐር ለተፈጁ፥
በየቀዬው በየደጁ፥
ገዳዮች ቢረሷቸው፥
ህዝባችን አይዘነጋቸው።
ድምጻቸው በመነጠቁ፥
ተስፋቸው በመሰረቁ፥
ለዛ ነው የወደቁ።
እናት ምድር ኢትዮጲያ፥
የሰማዕታት መንሃርያ።
ከስልሳሰባት አንስቶ፥
እስከዘጠና ሰባት ተሰልቶ፥
ስንቶች ረገፉ በገዢዎች፥
በወንበር አፍቃሪዎች።
ሰኔ ዐንድ ጨለማዋ፥
መራር ኮሶ ጽዋዋ፥
ልንረሳሽ ስልማንችል፥
ህሊናችን ስለማይችል፥
እንዘክርሻለን በየጓዳው፥
እስኪያከትም መራር ፍዳው፥
በአደባባይ እስክትዘከሪ ድረስ፥
ዕንባችን እስኪታበስ፥
ውድ ህይወታቸውን ላጡ፥
ደረታቸውን ለአረር ለሰጡ፥
ለክቡራን ሰማዕታት፥
ሻማ እንለኩስ በአንድነት።
የማትቀረዋ ነጻነት፥
ስትመጣ የለቱ ዕለት፥
በሰገነት ላይ ሆነን እስክናወራ፥
በየቤታችን ሻማ እናብራ!!!ለሰኔ1/1997ዓም ሰማዕታት መታሰቢያ ተጻፈ!
ደረጀ በጋሻው(pen ethiopian)
ምድር ወገብ (ከንዓን)
ዐሥር ሻማ ለኩሱ፥
ሰኔ 1ላይ ደማቸውን ላፈሰሱ፥
አጥንታቸውን ለከሰከሱ።
ለዴምክራሲና ነጻነት፥
ለፍትህና ለዕኩልነት፥
ሳይገድሉ ለተገደሉ፥
በከፈሉት ታክስ በጥይት ለተቆሉ፥
ደማቸው በውሻ ለተላሰው፥
የምንዘክራቸው ዛሬ ነው።
በመለስ ዜናዊ መመርያ፥
በአጋዚ ጦር መሳርያ፥
ደረታቸው ተነድሎ፥
አንጎላቸው ተፈንቅሎ፥
በስናይፐር ለተፈጁ፥
በየቀዬው በየደጁ፥
ገዳዮች ቢረሷቸው፥
ህዝባችን አይዘነጋቸው።
ድምጻቸው በመነጠቁ፥
ተስፋቸው በመሰረቁ፥
ለዛ ነው የወደቁ።
እናት ምድር ኢትዮጲያ፥
የሰማዕታት መንሃርያ።
ከስልሳሰባት አንስቶ፥
እስከዘጠና ሰባት ተሰልቶ፥
ስንቶች ረገፉ በገዢዎች፥
በወንበር አፍቃሪዎች።
ሰኔ ዐንድ ጨለማዋ፥
መራር ኮሶ ጽዋዋ፥
ልንረሳሽ ስልማንችል፥
ህሊናችን ስለማይችል፥
እንዘክርሻለን በየጓዳው፥
እስኪያከትም መራር ፍዳው፥
በአደባባይ እስክትዘከሪ ድረስ፥
ዕንባችን እስኪታበስ፥
ውድ ህይወታቸውን ላጡ፥
ደረታቸውን ለአረር ለሰጡ፥
ለክቡራን ሰማዕታት፥
ሻማ እንለኩስ በአንድነት።
የማትቀረዋ ነጻነት፥
ስትመጣ የለቱ ዕለት፥
በሰገነት ላይ ሆነን እስክናወራ፥
በየቤታችን ሻማ እናብራ!!!ለሰኔ1/1997ዓም ሰማዕታት መታሰቢያ ተጻፈ!
ደረጀ በጋሻው(pen ethiopian)
ምድር ወገብ (ከንዓን)