ከዚህ በፊት በሰራቸው “ምርት 3 ሽህ፣ ጤዛ፣ ሳንኮፋ፣ ቡሽ ማማ” እና በሌሎችም ፊልሞቹ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኝው ሐይሌ ገሪማ አሁን

ደግሞ “የጡት ልጅ” የሚል ፊልም ለመስራት ዝግጅቱን አጠናቆ አድናቂዎቹን “ኑ የፊልም ስራው ተባባሪ ሁኑ” እያለ ነው።

“የጡት ልጅ” በሰው ልጆች ሰባዊ መብት ዙሪያ የሚያጠነጥን በተለይም በቀያዊ ወይም አለማቀፋዊ ሃይሎች ሳይበገሩ የማፍቀር መብት ዙሪያ የሚያጠነጥን እንደሆነ ‘ኢንዲጎጎ’ በተሰኝው ለፊልሙ መስሪያ ያግዝ ዘንድ ገንዘብ የሚሰባሰብበት ድረገዕ የሰፈረ ጽሁፍ ያትታል።

የፊልሙ የጽሁፍ ስራ ከሰባት አመት በፊት ያለቀ ቢሆንም ያለፉትን አመታት ለፊልም ስራው የሚሆነ ገንዘብ በማፍላለግ እንደጠፋ የሚገልጸው ይህው ጽሁፍ ፊልሙን በጋራ ለመስራት ያስችል ዘንድ አምስት መቶ ሽህ ብር የተገኘ ቢሆንም ይህንኑ የሚያክል ገንዘብ ካልተገኘ ግን ዋጋ እንደማይኖረው ይገልጻል።

ፊልሙ ጣልያን ኢትዮጵያን ከወረረች ፳ አመታት በሗላ በአስራ ዘጠኝ ስልሳዎቹ የሆነን ታሪክ የሚያወሳ ሆኖ አይናለም የተባለች የ፩፫ ዓመት ልጃገረድ ትምህርቷን እንደምትከታተልና ጥሩ ኑሮ እንደሚኖራት ቃል ተገብቶላት በጉዲፈቻነት ሃብታም ለሆነ የዳኛ ቤተሰብ እንደተሰጠችና ከዚህ በተቃራኒው ግን ለቤት ሰራተኝነት መዳረጏን፤ የቀጣሪዎቿ ጭካኔና ቅርብ ክትትል ባይለያትም ጥላሁን የተባለ የፖሊስ አባልን አግኝታ ፍቅር ላይ መወደቋን፤ ጥላሁን ከነበረችበት ሁኔታ እንድትወጣ ቢረዳትም ከአመታት በሗላ በሌላ የማይጋፉት ግለሰብ እጅ ወድቃ እንዳገኛት የሚተርክ ነው።

ለፊልሙ ስራ የሚውለው መዋጮ ከአምሰት የአሜሪካን ዶላር ጀምሮ በየደረጃው የሚጨምር ሲሆን የሁሉም ሰው አስተዋጽዖ ዋጋ እንዳለው ሐይሌ ገሪማ ይገልጻል። በተለይም ወሬውን ላልሰሙት ሁሉ በማሰማት በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ።

ሐይሌ ገሪማ ከፍተኛ በጀት ተይዞላቸው የሚሰሩና የላቀ ተቀባይነት ያመጡ እንደ ‘ጤዛ’ አይነት ፊልሞችን በመስራት ያገኝውን ልምድ ለመጠቀም በማቀዱ እንጅ ፊልሙ ከትያዘለት ፩ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚያስወጣ ሊሆን ይችል ነበር ይላል።

“የጡት ልጅ” የሚለውን የፊልም ስራ በገንዘብ ለመርዳት ከዚህ ቀጥሎ በተጠቀሰው ድረገጽ ይጠቀሙ።

https://www.indiegogo.com/projects/yetut-lij-a-film-by-haile-gerima#/story ወይም igg.me/at/hailegerima

በክሬዲት ካርድ መክፈል ለማይችሉ ደግሞ የሚከተሉት አማራጮች ተጠቅሰዋል።

  • Paypal

paypal@yetutlij.com

  • Check

Positive Productions Inc.
2714 Georgia Ave. NW
Washington, DC 20001

ይህ ጽሁፍ እስከተሰናዳበት ሰዓት ድረስ ሁለት መቶ ሰማኒያ ሰዎች ያዋጡት ፫፩ ሽህ ፯፯፭ ብር (ሰላሳ አንድ ሺሀ ሰባት መቶ ሰባ አምሰት

ብር) የተዋጣ ሲሆን መዋጮውን እስክሚቀጥሉት ፰ ቀናት ድረስ ማድረግ ይቻላል። እስከአሁን ድርስ የተዋጣው የታቀድውን ፮ (ስድስት) በመቶ ብቻ ቢሆንም የፊልሙ ስራ በተዋጣውም ብር ቢሆን ሊጀመር እንደሚችል ተገልጷል።

ጥያቄው “በአንድ ሳምንት ውስጥ ምን ያህል የሐይሌ ገሪማን እቅድ እንቀርበው ይሆን?” የሚል ነው።

Leave a Reply