ያደረጋችሁት ታላቅ ተጋድሎም ታሪክ ጊዜውን ጠብቆ በራሱ ሂደት ፍርድ የሚሰጥ እንደሆነ ኣምናለሁ፤ በምርጫ አለመሸነፍና ማሸነፍ ብቻ ኣላማና ግቡ ለሆነው የኢሃዴግ ኣገዛዝ አሸንፌያለሁ የሚለውን ግቡን ያሳካ መስሎ ቢታየውም የህዝብን ልብና ፍቅር በምንም ምድራዊ ሃይል ማሸነፍ እንደማይችል እስከሚረዳው ድረስ የሰላማዊ ትግሉን ለመቀጠል ያላችሁ ጽናት የሚያኮራ ነው ፥ በህይወት እያላችሁ ለውጡን ላታዩ ትችላላሁ፥  የዲሞክራሲ ወላጆች ያውም እንደኛ ሃገር ፍጹም ኣምባገነን ገዢ ባለበት መስዋእትነታቸው የበዛ ነው፥ በመገደል  በመታሰር  በመሰደድና  በተለያዩ አካላዊ ጉዳቶች ከሚገለጸው የከፋው የትውልዱንና የህብረተሰቡን ኣእምሮ በማደንዘዝ መግደል የከፋው ነው፥ ይህ ደግሞ በሃገራችን እየታየ ነው፥

ለዚህ ደግሞ ፖለቲካውን የሚጫወቱት ወገኖችና ግንባር ቀደም መሪዎች ተጨባጩን ሁኔታ መገምገምና ከጊዜው ጋር የሚመጥን የሃይል ኣሰላለፍና ተጫዋቾችንም በተገቢው ስፍራቸው ማስቀመጥ የወቅቱ ጥያቄና ከሁሉ በፊት ግን ምን ኣይነት ኣደረጃጀት የሚለው ቀዳሚ ዪመስለኛል ። ፪፬ ኣምታት ልምድ ዪህን በሚገባ ኣስይቶናል ፤ በብሄረስብ መደራጀት ወቅቱ የጠየቀው ነበር፥ ተገቢም ነበር ምክንያቱም ፖለቲካው በህብረተሰቡ ውስጥ የሚሰራ ስራ በመሆኑ ከህብረተሰቡ ጥያቄ ኣንጻርና በተለዪም ለራሱ ስልጣን ሲል ወያኔ ኢሃዴግ የብሄረሰብን ጥያቄ ለጥጦ ለጥጦ ወደ ዘር ፖለቲካ ባይቀይረው ጥያቄው የእኩልነት ጥያቄ ነው፥፥ ለዚህ ድግሞ እኩልነት ይጎለናል የሚል የህብረተሰብ ክፍል ከጀርባው የሚያሰልፈውን ህብረተሰብ ኣነሳሽ የፖለቲካ ኣጀንዳና ማታገያ ዘዴ መፍጠሩ የግድ ነው፥ የመድረክ ኣባል የፖለቲካ ድርጅቶችንም የማየው ከዚህ ኣኩዋያ ነው፥ ዛሬ ተጨባጩ ያ ኣይደለም ፤ እውነቱን ለመናገር የወያኔ ኢሃዴግ ፕሮፓጋንዳ ከዚህ ዘሎኣል፤ በተግባር ውስጥ ውስጡን የብሄረሰብን ጉዳይ ለፖለቲካ ሃይሎቹ መከፋፈያ ይጠቀምበት እንጂ በኣደባባይ ህብረተሰቡን የሚሰብኩበት የሚቀሰቅሱበት ስለ ትልቋ ኢትዮጵያ ሆኖኣል፤፤ ዛሬ የወያኔ ኢሃዴግ ኣባል ድርጅቶች ኣንዱ ከኣንዱ በማይለይበት ሁኔታ በጋራ የኣምባገነኑ ስርአት የተዋሃደ አካል ናቸው፤ የመድረክ ኣባል ድርጀቶች ይህንን በሚገባ የተገነዘቡት ይመስለኛል፤ በየኣካባቢው ማነው ገዳዩ ማነው ኣሳሪው የሚለውን ህዝብም የሚያውቅ ይመስለኛል፤ ለዚህም ነው የመድረክ ኣባል ድርጅቶች ለሚቀጥለው ኣምስት ኣመትም ኣሁን ባሉበት ኣደረጃጀት መቀጠላቸው ፈቀቅ የማያደርግ የፖለቲካ ጉዞ ነውና ዪታሰብበት የምንለው፥

፪፨ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ኣሁን ባለው ሁኔታ የተካረረ ኣካሄዱ ለማንም የማይበጅ መሆኑን ብዙዎች የተናገሩትና መድረክም ኣሳሳቢነቱን የተረዳው ይመስለኛል፥ ከዚህ የተካረረ ፖለቲካ መውጣት የሚቻለው ደግሞ በተደጋጋሚ መድረክም ሆነ ሌሎች የፖለቲካ ድርጀቶች ሃላፊነት በሚሰማው ስሜት ብሄራዊ መግባባትን እየጮሁበት ይገኛሉ፥ እንደ ኣንድ የሃገሩ ችግር እንደሚያሳስበው ኢትዮጵያዊ ዛሬ ያለውን ዘርፈ ብዙ የኢትዮጵያ ፖለትካ ችግር ለመፍታት ዋና ኣማራጭ ይሄ ኣስተሳሰብ ሊገፋበት እንደሚገባ ኣምናለሁ ፥ ችግሩ ግን ባላቤት ያጣ ኣጀንዳ ዪመስለኛል፤ ሁሉም ያወራዋል እንጂ ለተግባራዊነቱ የሚያስፈልጉትን ሁኔታዎች በድፍረት የገፋበት የለም ፥ ስርአቱ ፈቃደኛ ኣይደለም ወይም መግባባት የሚቻለው ስራቱ ላይ ኣስገዳጅነት ያለው ሃይል ሲፈጠር ነው በሚሉ መሸፋፈኛ ሃረጎች ወይም ኣጀንዳው የተንበርካኪነት መስመር ነው በሚሉ ኣመለካከቶች ተደባብሶ ይገኛል፥ ስለዚህም መድረክ ኣጀንዳውን ከማቅረብ ኣልፎ ለተግባራዊነቱ ባለቤት ሊሆን የሚችል የፖለቲካ ኣመለካከት ያለው ስብስብ ይመስለኛል፥ ስለሆነም በዚህ ጉዳይ ላይ ተቃዋሚውን ሃይል ሊያሰባስብ የሚችልና ገዢውንም ፓርቲ ሊያስገድ ድ የሚችል የኣፈጻጸም ሃሳብ ቀርጾ መንቀሳቀስ ያለበት ይመስለኛል፥  በዚህ ጉዳይ ያመኑ ኢትዮጵያውያኖችን የሚያሰባስብ መድረክ መፈጠር የወቅቱ ኣጣዳፊ ተግባርና በባለቤትነትም መድረክ ሃላፊነቱን ሊወስድ ይችላል ብዬ ኣምናለሁ፥፥ በሚቻለው ሁሉ በውጭው ያለ በርካታ ኢትዮጵያዊ የሃሳቡ ደጋፊ እንደሆነና የሚያስፈልገውንም ድጋፍ እንደሚሰጥ ተስፋ ኣደርጋለሁ፥፥

ለምታደርጉት ሁሉ ከጎናች ሁ በርካታ ኢትዮጵያኖች ኣሉና በርቱ፤ ረዥም ጊዜ ቢወስድም ዲሞክራሲያዊ ስራት ግንባታን ጀምራችኋልና ግፉበት ፥ግባችሁ ምርጫ ባይሆንም ምርጫውም የዲሞክራሲ ግንባታ መገለጫ ነውና በርቱ፥ ኣምባገነኖች ምንም ያህል እድሜያቸው ቢረዝም ውድቀታቸው ኣይቀሬ ነውና ለተተኪው ትውልድ የጀመራችሁን በጎ ጎዳና ኣስተላልፎ ማለፍን እንደድል ቁጠሩት፥፥

መልካም የስራ ጊዜ ይሁንላችሁ!

http://www.medrekonline.org/

Leave a Reply